የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 5/07 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ግንቦት 14 የሚጀምር ሳምንት
  • ግንቦት 21 የሚጀምር ሳምንት
  • ግንቦት 28 የሚጀምር ሳምንት
  • ሰኔ 4 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
km 5/07 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

ግንቦት 14 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 67 (156)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በገጽ 4 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የሚያዝያ 1 መጠበቂያ ግንብ እና የሚያዝያ 2007 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።

20 ደቂቃ:- በጉባኤም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የመንግሥቱን ሥራ መደገፍ። የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ምዕራፍ 12 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ።

15 ደቂቃ:- “ለደከመው ብርታት ይሰጣል።”* ጊዜ በፈቀደልህ መጠን አድማጮች ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ በተጠቀሱ ጥቅሶች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ አድርግ።

መዝሙር 22 (47) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ግንቦት 21 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 57 (136)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የጥያቄ ሣጥኑን ከልስ።

15 ደቂቃ:- ሌላ ቋንቋ መማር ትችላለህ! በመጋቢት 2007 ንቁ! መጽሔት ከገጽ 10-12 ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። ምሥራቹን የማስፋፋት ግብ በመያዝ ሌላ ቋንቋ መማር ያለውን ጥቅም ጎላ አድርገህ ተናገር።

20 ደቂቃ:- “ለአምላክ ቃል ጥብቅና ትቆማላችሁ?”* በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 143 እና 144 ላይ ከሚገኙት ሣጥኖች ውስጥ አንዳንድ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ።

መዝሙር 90 (204) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ግንቦት 28 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 21 (46)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ። አስፋፊዎች የግንቦት ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በገጽ 4 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የሚያዝያ 15 መጠበቂያ ግንብ እና የግንቦት 2007 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።

20 ደቂቃ:- በሰኔ ወር ክርኤተር አሊያም ለቤተሰብ ደስታ የተባሉትን መጻሕፍት አበርክቱ። እነዚህ መጻሕፍት በአሁኑ ጊዜ ያላቸውን አንዳንድ ጠቃሚ ገጽታዎች ጥቀስ፤ እንዲሁም ለክልላችሁ ተስማሚ የሆኑ አቀራረቦችን በመጠቀም እያንዳንዱን መጽሐፍ እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን አድማጮች እነዚህን መጻሕፍት ለሚያውቋቸው ሰዎች ወይም ለቤተሰባቸው አባላት በማበርከት ያገኟቸውን ጥሩ ውጤቶች እንዲናገሩ ጋብዝ።

15 ደቂቃ:- ከአገልግሎት የተገኙ ተሞክሮዎች። ረዳት አቅኚዎችና አስፋፊዎች በመጋቢት፣ በሚያዝያና በግንቦት ወራት የአገልግሎት እንቅስቃሴያቸውን ከፍ ለማድረግ ተግተው በመሥራታቸው ምክንያት ያገኟቸውን ተሞክሮዎች ተናገር። እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስጀመር ግብ በመያዝ መጽሔት ያበረከቱላቸውን ሰዎች ተከታትለው በመርዳት ያገኟቸውን ተሞክሮዎች እንዲናገሩ ጋብዝ። አንድ ወይም ሁለት ተሞክሮዎች በሠርቶ ማሳያ እንዲቀርቡ አድርግ።

መዝሙር 8 (21) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሰኔ 4 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 59 (139)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።

15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

20 ደቂቃ:- “ልጆቻችሁ ይሖዋን እንዲያወድሱ አስተምሯቸው።”* አንቀጽ 4ን ስትወያዩ ከሐምሌ 2005 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 3 ላይ አንዳንድ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ።

መዝሙር 75 (169) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

[የግርጌ ማስታወሻዎች ]

አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ