ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት
ክለሳ ሰኔ 25, 2007 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከግንቦት 7 እስከ ሰኔ 25, 2007 ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል። [ማሳሰቢያ:- ከጥያቄው ቀጥሎ መልሱ የሚገኝበት ጽሑፍ ካልተጠቀሰ መልሱን ለማግኘት በግልህ ምርምር ማድረግ ይኖርብሃል።—የአገልግሎት ትምህርት ቤት ገጽ 36-37ን ተመልከት።]
የንግግር ባሕርይ
1. በምንናገርበት ጊዜ የሚሰማንን ጭንቀት ቀንሰን የድምፃችንን ጥራት ለማሻሻል ምን ልናደርግ እንችላለን? [be ገጽ 184 አን. 3 እስከ ገጽ 185 አን. 2]
2. በአገልግሎታችን “ከሁሉ ጋር በሁሉ ነገር እንደ እነርሱ” ልንሆን የምንችለው እንዴት ነው? (1 ቆሮ. 9:20-23 የ1954 ትርጉም) [be ገጽ 186 አን. 2-4]
3. ሌሎች ሲናገሩ በማዳመጥ ረገድ የይሖዋን ምሳሌ መኮረጅ የምንችለው እንዴት ነው? (ዘፍ. 18:23-33፤ 1 ነገ. 22:19-22) [be ገጽ 187 አን. 1-2, 5]
4. ሌሎች በመንፈሳዊ እድገት እንዲያደርጉ መርዳት የምንችልባቸው ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ መንገዶች የትኞቹ ናቸው? [be ገጽ 187 አን. 6 እስከ ገጽ 188 አን. 3]
5. ለሰዎች አክብሮት ማሳየት ሊያሳስበን የሚገባ ጉዳይ የሆነው ለምንድን ነው? [be ገጽ 190 አን. 3፣ ሣጥኑ]
ክፍል ቁጥር 1
6. የምናስተምራቸውን ሰዎች ልብ ለመንካት መጣር ያለብን ለምንድን ነው? [be ገጽ 59 አን. 1]
7. የእኛ ምሳሌነት በምናስተምራቸው ሰዎች ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራል? [be ገጽ 61 አን. 1]
8. ከሰዎች ጋር የመወያየት ችሎታችንን በቤት ውስጥ እንዴት ማሻሻል እንችላለን? [be ገጽ 62 አን. 3]
9. ቆራጥነት የታከለበት ቅንዓት ማሳየትን በተመለከተ ነቢዩ ኤርምያስ ምን ምሳሌ ትቷል? [bsi07 ገጽ 4 አን. 36]
10. የሰቆቃወ ኤርምያስ መጽሐፍ፣ ጸሐፊው ምን ዓይነት እምነት እንደነበረው ይገልጻል? አምላክ በክፉ ሰዎች ላይ የሚወስደውን ከበድ ያለ እርምጃ በመግለጽ ረገድ ጠቃሚ መጽሐፍ የሆነውስ ለምንድን ነው? [bsi07 ገጽ 5 አን. 13]
ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. በኤርምያስ 37:21 ላይ ተመዝግቦ ከሚገኘው የኤርምያስ ተሞክሮ ጋር በሚመሳሰል መልኩ ምን አስተማማኝ ተስፋ አለን?
12. ባሮክ፣ ይሖዋ ‘በሕመሙ ላይ ሐዘን እንደጨመረበትና እንዲደክም’ እንዳደረገው የተናገረው ለምን ሊሆን ይችላል? ባሮክ ለችግሩ የሰጠው የመጀመሪያ ምላሽስ ምን ነበር? (ኤር. 45:1-5)
13. ባቢሎን ሰው የማይኖርባት “ባድማ” የሆነችው መቼ ነበር? (ኤር. 50:13)
14. በሰቆቃወ ኤርምያስ 3:8, 9, 42-45 ላይ ጸሎትን በተመለከተ ምን ግልጽ የሆነ መሠረታዊ ሥርዓት እናገኛለን?
15. በሕዝቅኤል ምዕራፍ 1 ላይ የተገለጸው ሠረገላ ምን ያመለክታል?