የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 24—ኤርምያስ
    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው፣ ጥራዝ 15
    • ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት

      36 በመንፈስ አነሳሽነት የተነገረው ይህ ትንቢት ሙሉ በሙሉ ገንቢና ጠቃሚ ነው። ይህ ነቢይ የተወውን የቆራጥነት ምሳሌ ተመልከት። ከአምላክ በራቀው ሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያልነበረውን መልእክት ሲያውጅ አልፈራም። ከክፉዎች ጋር ለመወዳጀት ፈቃደኛ አልነበረም። የይሖዋ መልእክት አጣዳፊ መሆኑን በመገንዘብ ራሱን ለይሖዋ ሥራ ሙሉ በሙሉ ከማቅረቡም በላይ በዚህ ሥራ እስከ መጨረሻው ገፍቶበታል። የአምላክ ቃል በአጥንቱ ውስጥ እንደ ረመጥ እሳት እንደሆነበት እንዲሁም ሐሴትና የልብ ደስታ እንደሰጠው ገልጿል። (ኤር. 15:16-20፤ 20:8-13) እኛም ለይሖዋ ቃል እንደዚህ ዓይነት ቅንዓት እናሳይ! እንዲሁም ባሮክ ኤርምያስን እንደረዳው ሁሉ እኛም ከአምላክ አገልጋዮች ጎን በታማኝነት በመቆም እንደግፋቸው። የሬካባውያን ልባዊ ታዛዥነትና አቤሜሌክ ስደት ላይ ለነበረው ነቢይ ያሳየው ደግነት ግሩም ምሳሌ ይሆኑናል።—36:8-19, 32፤ 35:1-19፤ 38:7-13፤ 39:15-18

      37 ወደ ኤርምያስ የመጣው የይሖዋ ቃል ቅንጣት ታህል ዝንፍ ሳይል ፍጻሜውን አግኝቷል። ይህ ደግሞ ይሖዋ ትንቢት ለመናገር ባለው ችሎታ ላይ ያለንን እምነት እንደሚያጠነክርልን ምንም ጥያቄ የለውም። ለምሳሌ ያህል ኤርምያስ ራሱ በሕይወት እያለ ፍጻሜያቸውን ያገኙትን ትንቢቶች ተመልከት:- የሴዴቅያስ መማረክና የኢየሩሳሌም መጥፋት (21:3-10፤ 39:6-9)፣ የንጉሥ ሰሎም (ኢዮአካዝ) ከሥልጣን መውረድና በምርኮ እያለ መሞት (ኤር. 22:11, 12፤ 2 ነገ. 23:30-34፤ 2 ዜና 36:1-4)፣ የንጉሥ ኢኮንያን (ዮአኪን) በምርኮ ወደ ባቢሎን መወሰድና (ኤር. 22:24-27፤ 2 ነገ. 24:15, 16) የሐሰተኛው ነቢይ የሐናንያ በአንድ ዓመት ውስጥ መሞት (ኤር. 28:16, 17)። እነዚህና ሌሎች ትንቢቶች በሙሉ ይሖዋ አስቀድሞ እንደተናገረው ፍጻሜያቸውን አግኝተዋል። ከጊዜ በኋላ የተነሡት ነቢያትና የአምላክ አገልጋዮችም የኤርምያስን ትንቢቶች እውነተኛና ጠቃሚ ሆነው አግኝተዋቸዋል። ለምሳሌ ያህል፣ ዳንኤል ኢየሩሳሌም ባድማ ሆና የምትቆየው ለ70 ዓመታት እንደሆነ ከኤርምያስ ጽሑፍ ተገንዝቦ የነበረ ሲሆን ዕዝራም በ70ው ዓመት መጨረሻ ላይ የኤርምያስ ቃል ፍጻሜውን እንዳገኘ ጠቅሷል።—ዳን. 9:2፤ 2 ዜና 36:20, 21፤ ዕዝራ 1:1፤ ኤር. 25:11, 12፤ 29:10

      38 ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ሆኖ የጌታ እራት በዓልን ባቋቋመበት ወቅት፣ አዲሱን ቃል ኪዳን አስመልክቶ ኤርምያስ የተናገረው ትንቢት ፍጻሜውን እንዳገኘ ጠቁሟል። የኃጢአት ይቅርታ ስለሚያገኙበትና የይሖዋ መንፈሳዊ ሕዝብ በመሆን ስለሚሰበሰቡበት ኪዳን ሲናገር “በሚፈሰው ደሜ የሚመሠረት አዲስ ኪዳን” በማለት ጠርቶታል። (ሉቃስ 22:20፤ ኤር. 31:31-34) መንፈሳዊ ልጆች በመሆን በዚህ አዲስ ቃል ኪዳን ውስጥ የሚታቀፉት ኢየሱስ ከእርሱ ጋር በሰማይ እንዲገዙ የመንግሥት ቃል ኪዳን የገባላቸው ሰዎች ናቸው። (ሉቃስ 22:29፤ ራእይ 5:9, 10፤ 20:6) ይህ መንግሥት በኤርምያስ ትንቢት ውስጥ በርካታ ጊዜያት ተጠቅሷል። እምነት የለሿን ኢየሩሳሌምን በተመለከተ ያ ሁሉ ፍርድ ቢነገርም ኤርምያስ የሚከተለውን የተስፋ ብልጭታ ፈንጥቆ ነበር:- “‘እነሆ፤ ለዳዊት፣ ጻድቅ ቅርንጫፍ የማስነሣበት ጊዜ ይመጣል፤ እርሱም ፍትሕንና ጽድቅን የሚያደርግ፣ በጥበብ የሚገዛ ንጉሥ ይሆናል’ ይላል እግዚአብሔር።” አዎን፣ “እግዚአብሔር [“ይሖዋ፣” NW] ጽድቃችን” የሚባል ንጉሥ ይነሳል።—ኤር. 23:5, 6

      39 ኤርምያስ “ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር፣ ለማስነሣላቸውም ለንጉሣቸው፣ ለዳዊት ይገዛሉ” በማለት እንደገና ስለ መቋቋምም ተናግሯል። (30:9) በመጨረሻም፣ የዳዊትን ዘር ለማብዛትና “በዙፋኑ ላይ የሚነግሥ ዘር” እንዲኖር ለማድረግ “በዚያ ዘመንና በዚያ ጊዜ፣ ከዳዊት ቤት ጻድቅ ቅርንጫፍ አበቅላለሁ” በማለት እስራኤልንና ይሁዳን በተመለከተ ይሖዋ የተናገራቸውን መልካም ቃላት ገልጿል። (33:15, 21) ቀሪዎቹ ከባቢሎን እንደተመለሱ ሁሉ የዚህ ጻድቅ “ቅርንጫፍ” መንግሥትም በምድር ሁሉ ላይ ፍትሕንና ጽድቅን ማስፈኑ ምንም አያጠራጥርም።—ሉቃስ 1:32

  • የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 25—ሰቆቃወ ኤርምያስ
    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው፣ ጥራዝ 15
    • የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 25​—⁠ሰቆቃወ ኤርምያስ

      ጸሐፊው:- ኤርምያስ

      የተጻፈበት ቦታ:- በኢየሩሳሌም አቅራቢያ

      ተጽፎ ያለቀው:- 607 ከክ. ል. በፊት

      በመንፈስ አነሳሽነት ከተጻፉት መጻሕፍት አንዱ ለሆነው ለዚህ መጽሐፍ የተሰጠው ስያሜ በጣም ተስማሚ ነው። መጽሐፉ፣ የባቢሎኑ ንጉሥ ናቡከደነፆር በ607 ከክርስቶስ ልደት በፊት ኢየሩሳሌምን ሲያጠፋ አምላክ በመረጣቸው ሕዝቦቹ ላይ የደረሰው መከራ ያስከተለውን ጥልቅ ሐዘን የሚገልጽ የሐዘን እንጉርጉሮ ነው። መጽሐፉ በዕብራይስጥ ኤህከሃህ! ተብሎ ተሰይሟል። ይህን ስያሜ ያገኘው የመጽሐፉ መክፈቻ ከሆነው ከመጀመሪያው ቃል ሲሆን “እንዴት!” የሚል ትርጉም አለው። የግሪክ ሰብዓ ሊቃናት ተርጓሚዎች መጽሐፉን ትሬኖይ ብለው የጠሩት ሲሆን ይህም “ሙሾ፣ የሰቆቃ

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ