የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 6/07 ገጽ 2
  • ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
km 6/07 ገጽ 2

ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች

◼ ቀጥሎ የተጠቀሱት የመንግሥት አዳራሾች ግንባታ ተጠናቋል:- ጮመን (ፊንጫ አካባቢ)፣ ዳኒሳ (ጊንጪ አካባቢ)፣ ኤዶ ኪንዱ (ቦዲቲ አካባቢ)፣ እነማይኩዌ (ጊምቢ አካባቢ)፣ ኮራ (ጊንጪ አካባቢ)፣ ሻምቡ፣ ወሊሶ እና በአዲስ አበባ ደግሞ ጌጃ/ልደታ። እነዚህን ጨምሮ የመንግሥት አዳራሾቻችን ብዛት በአጠቃላይ 109 ደርሷል።

◼ “መዳናችን ቀርቧል!” በሚል ጭብጥ ባደረግናቸው አሥራ ስምንት የአውራጃ ስብሰባዎች ላይ በድምሩ የተገኘው ከፍተኛው የተሰብሳቢዎች ቁጥር 14,736 ነበር። ይህ አኃዝ ከዚህ ቀደም ከነበረን ከፍተኛ የተሰብሳቢዎች ቁጥር 9 በመቶ ጭማሪ አለው። በዚህ ስብሰባ ላይ 331 አስፋፊዎች ተጠምቀዋል።

◼ ተሻሽሎ የተዘጋጀውን ባለ ጠንካራ ሽፋን መማሪያ መጽሐፍ በመጠቀም በታኅሣሥ ወር በድምሩ 277 አቅኚዎች በአቅኚዎች አገልግሎት ትምህርት ቤት ተካፍለዋል። ከእነዚህም መካከል 159 የሚሆኑት ተሞክሮ ያካበቱ አቅኚዎች ሥልጠናውን የወሰዱት ለሁለተኛ ጊዜ ነበር።

◼ በአሁኑ ጊዜ ከአገልጋዮች ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት የተመረቁ 45 ወንድሞች በክልላችን ውስጥ ያገለግላሉ። ከእነዚህ መካከል አንዳንዶቹ ያገኙትን ሥልጠና በጥሩ ሁኔታ በመጠቀም በተጓዥ የበላይ ተመልካችነትና በቤቴል በማገልገል ላይ ይገኛሉ። ከግንቦት ጀምሮ በናይሮቢ፣ ኬንያ ለሚካሄደው 20ኛው ክፍል ተጨማሪ ወንድሞችን ለመላክ ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው።

◼ በቤቴል አምስተኛውን የትርጉም ቡድን ለማቋቋም በሂደት ላይ እንገኛለን። ይህ ቡድን የሲዳማ የትርጉም ቡድን ሲሆን ከአማርኛ፣ ከኦሮምኛ ከትግርኛና ከወላይትኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች በተጨማሪ በርካታ ተናጋሪ ባለው በዚህ ቋንቋ መንፈሳዊ ምግብ ለማቅረብ ጥረት የሚያደርግ ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ