የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
ሰኔ 11 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 24 (50)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በገጽ 4 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የግንቦት 1 መጠበቂያ ግንብ እና የግንቦት 2007 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
15 ደቂቃ:- የአምላክን ቃል ለማስተማር በሚገባ የታጠቁ። በየካቲት 15, 2002 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 24-28 ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። አንዳንድ ክርስቲያኖች ጥናት ለመምራት ብቁ እንደሆኑ ስለማይሰማቸው ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት እንዲጀምሩ ለመጋበዝ ያመነታሉ። ይሁን እንጂ ይሖዋ በቃሉ፣ በቅዱስ መንፈሱና በድርጅቱ አማካኝነት አገልጋዮቹ እንድንሆን ብቁ ያደርገናል። ግባችን ጽሑፍ ማበርከት ብቻ አይደለም። ሰዎችን ለማስተማር ጥረት ማድረግ ይኖርብናል። (ማቴ. 28:19, 20) አስፋፊዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስጀመር ግብ እንዲኖራቸው አበረታታ።
20 ደቂቃ:- ሁሉንም ነገር ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት። የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ በሚለው መጽሐፍ ምዕራፍ 13 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ።
መዝሙር 61 (144) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሰኔ 18 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 97 (217)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎችና ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች።
20 ደቂቃ:- መጽሐፍ ቅዱስ ልጆችህን ለማሰልጠን ይረዳህ ይሆን? በሰኔ 15, 2004 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 4-7 ላይ ተመሥርቶ አንድ ሽማግሌ በውይይት ያቀርበዋል።
15 ደቂቃ:- “ራሳችንን ለይሖዋ አገልግሎት በማቅረባችን ደስተኞች ነን!”* ጊዜ በፈቀደልህ መጠን አድማጮች ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ በተጠቀሱ ጥቅሶች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ አድርግ።
መዝሙር 37 (82) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሰኔ 25 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 2 (4)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን የምሥጋና ደብዳቤ አንብብ። በገጽ 4 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የግንቦት 15 መጠበቂያ ግንብ እና የሰኔ 2007 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
15 ደቂቃ:- ከምንም ነገር የላቀ ውርሻ። በሰኔ 15, 2004 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 8-10 ላይ ተመሥርቶ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር።
20 ደቂቃ:- “በተከፈተልህ ‘ታላቅ የሥራ በር’ መግባት ትችላለህ?”* ለአንድ ወይም ለሁለት የዘወትር አቅኚዎች አጭር ቃለ ምልልስ አድርግ። የዘወትር አቅኚ ለመሆን ሲሉ ምን ማስተካከያዎችን አድርገዋል? ምን በረከቶችንስ አገኙ?
መዝሙር 58 (138) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ሐምሌ 2 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 87 (195)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የሰኔ ወር የአገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በሐምሌ ወር የሚበረከተውን ጽሑፍ ከተናገርክ በኋላ አንድ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
15 ደቂቃ:- መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት—ምሥራቹን ለመስበክ የሚያስችል ውጤታማ መንገድ። የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ በሚለው መጽሐፍ ገጽ 101-102 ላይ ተመሥርቶ ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። መደበኛ ባልሆነ መንገድ ለመመሥከር የሚያስችሉ አንዳንድ ተግባራዊ መንገዶችን ተናገር። አድማጮች መደበኛ ባልሆነ መንገድ በመመሥከር ያገኟቸውን አበረታች ተሞክሮዎች እንዲናገሩ ጋብዝ።
20 ደቂቃ:- “‘ብዙ ፍሬ ማፍራታችሁን’ ቀጥሉ።”* አንቀጽ 4ን ስትወያዩ ከየካቲት 1, 2003 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 21 ላይ “‘በመጽናት ፍሬ ማፍራት’ የሚቻለው እንዴት ነው?” ከሚለው ሣጥን ውስጥ አንዳንድ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ።
መዝሙር 16 (37) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
[የግርጌ ማስታወሻዎች ]
አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው።