የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 7/07 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ሐምሌ 9 የሚጀምር ሳምንት
  • ሐምሌ 16 የሚጀምር ሳምንት
  • ሐምሌ 23 የሚጀምር ሳምንት
  • ሐምሌ 30 የሚጀምር ሳምንት
  • ነሐሴ 6 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
km 7/07 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

ሐምሌ 9 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 2 (4)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በገጽ 4 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የሰኔ 1 መጠበቂያ ግንብ እና የሰኔ 2007 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።

15 ደቂቃ:- እውነተኛ ደስታ የሚያስገኘው ምንድን ነው? በግንቦት 15, 2006 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 28-29፣ በአንቀጽ 11 እና 12 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ተድላን በማሳደድ ወይም በሰብዓዊ ሥራ ከመጠመድ ይልቅ መላ ሕይወቱ በአገልግሎት ላይ እንዲያተኩር ላደረገ አንድ አስፋፊ አጭር ቃለ መጠይቅ አድርግ። መንፈሳዊ ግቦችን መከታተል የመረጠው ለምንድን ነው? እንዲህ ማድረጉስ ደስታ ያስገኘለት እንዴት ነው?

20 ደቂቃ:- የጥያቄ ሣጥን። በጉባኤ ሽማግሌ የሚቀርብ። አንቀጾቹን አንድ በአንድ እያነበብክ አብራራ። በሰኔ 2005 ንቁ! መጽሔት ገጽ 19 እና 20 ላይ “ማታለልና ራስን መደበቅ” እንዲሁም “በኢንተርኔት ከሚሆን ይልቅ ፊት ለፊት መገናኘቱ ይመረጣል” በሚሉት ንዑስ ርዕሶች ሥር የሚገኙትን አንዳንድ ሐሳቦች ጨምረህ አቅርብ።

መዝሙር 65 (152) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሐምሌ 16 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 7 (19)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

20 ደቂቃ:- የጉባኤውን ሰላምና ንጽሕና መጠበቅ። የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ ከተባለው መጽሐፍ ከገጽ 144 እስከ 150 ንዑስ ርዕስ ድረስ ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ።

15 ደቂቃ:- “በመጠበቂያ ግንብ ላይ የተደረጉ አስደሳች ለውጦች!”*

መዝሙር 26 (56) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሐምሌ 23 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 55 (133)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርቱንና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ። በገጽ 4 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የሰኔ 15 መጠበቂያ ግንብ እና የሐምሌ 2007 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።

20 ደቂቃ:- እርስ በርሳችሁ በእንግድነት ተቀባበሉ። በጥር 15, 2005 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 21-23 ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። በእንግዳ ተቀባይነታቸው ለታወቁ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች አጭር ቃለ ምልልስ አድርግ። የእንግዳ ተቀባይነት መንፈስ ለማሳየት ጥረት ያደረጉት እንዴት ነው? እንግዳ ተቀባዮች በመሆናቸው እነርሱም ሆኑ ቤተሰባቸው ምን በረከቶችን አግኝተዋል?

15 ደቂቃ:- ውጤታማ መግቢያዎችን መዘጋጀት። በማመራመር መጽሐፍ ገጽ 9 አንቀጽ 1 እና 2 ላይ ተመሥርቶ ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። በነሐሴ ወር የምናበረክተውን ጽሑፍ እንዴት ለሰዎች ማስተዋወቅ እንደምንችል የሚያሳዩ ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።

መዝሙር 47 (112) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ሐምሌ 30 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 88 (200)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የሐምሌ ወር የአገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው።

15 ደቂቃ:- የራስን ጥቅም መሠዋት የይሖዋን በረከት ያስገኛል። በኅዳር 15, 2005 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 8-9 ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር።

20 ደቂቃ:- “በፈተና የሚጸና ሰው ደስተኛ ነው።”* በአንቀጽ 3 ላይ ስትወያዩ አድማጮች ጠንካራ እምነት መገንባታቸው፣ ድንገት ፈተና ባጋጠማቸው ወቅት የረዳቸው እንዴት እንደሆነ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ። አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎችን ቀደም ብለህ ልታዘጋጅ ትችላለህ።

መዝሙር 6 (13) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

ነሐሴ 6 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 45 (106)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።

15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

20 ደቂቃ:- “በተደጋጋሚ የምንሄደው ለምንድን ነው?”* በአንቀጽ 5 ላይ ስትወያዩ እውነትን ከመስማታቸው በፊት ተቃዋሚ የነበሩ ወይም ፍላጎት ያልነበራቸው ቢሆንም ለእውነት ፍላጎት እንዲያድርባቸው ያደረጋቸው ምን እንደሆነ እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።

መዝሙር 93 (211) እና የመደምደሚያ ጸሎት።

[የግርጌ ማስታወሻዎች ]

አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ