የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/07 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ነሐሴ 13 የሚጀምር ሳምንት
  • ነሐሴ 20 የሚጀምር ሳምንት
  • ነሐሴ 27 የሚጀምር ሳምንት
  • መስከረም 3 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
km 8/07 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ

ነሐሴ 13 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 81 (181)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በገጽ 8 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የሐምሌ 1 መጠበቂያ ግንብ እና የሐምሌ 2007 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ በዚህ የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 6 አንቀጽ 3 ላይ ከቀረቡት ሐሳቦች አንዱን በመጠቀም አስፋፊው በተመላልሶ መጠየቅ ወቅት መልስ የሚሰጥበትን ጥያቄ ሲጠይቅ የሚያሳይ ይሁን።

20 ደቂቃ:- ለቲኦክራሲያዊ ሥርዓት መገዛት የሚያስገኘው ጥቅም። የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ምዕራፍ 15 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ።

15 ደቂቃ:- “ይሖዋን በቤተሰብ ደረጃ ማምለክ።”* አድማጮች በቤተሰብ ደረጃ አንድ ላይ ማገልገላቸው ምን ጥቅም እንዳስገኘላቸው እንዲናገሩ ጋብዝ። ሐሳብ የሚሰጡ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎችን አስቀድመህ ልታዘጋጅ ትችላለህ።

መዝሙር 23 (48) እና የመደምደሚያ ጸሎት

ነሐሴ 20 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 35 (79)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ። በገጽ 8 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የሐምሌ 15 መጠበቂያ ግንብ እና የነሐሴ 2007 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።

15 ደቂቃ:- በመስከረም ወር፣ ሰዎችን በምታነጋግሯቸው በመጀመሪያው ዕለት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አስጀምሩ። በውይይት የሚቀርብ። በመስከረም ወር የምናበረክተው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ ሲሆን የቤቱን ባለቤት በምናነጋግርበት በመጀመሪያው ዕለት ከግለሰቡ ጋር ጥቂት አንቀጾችን ለመወያየት ጥረት እናደርጋለን። በጥር 2006 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ላይ የወጡትን ሐሳቦች ከልስ፤ በተጨማሪም ሰዎችን በምናነጋግርበት በመጀመሪያው ዕለት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዴት ማስጀመር እንደሚቻል የሚያሳዩ አንድ ወይም ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።

20 ደቂቃ:- “የጉባኤ መጽሐፍ ጥናት ጥቅም የሚያስገኝልን እንዴት ነው?”* አንቀጽ 5ን ስትወያዩ የተደራጀ ሕዝብ ከተባለው መጽሐፍ ገጽ 41 አንቀጽ 1 ላይ አንዳንድ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ።

መዝሙር 3 (6) እና የመደምደሚያ ጸሎት

ነሐሴ 27 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 43 (98)

5 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

20 ደቂቃ:- “ለአዲሱ የአገልግሎት ዓመት ልታወጣው የምትችለው ጠቃሚ ግብ።”* በቅርቡ በረዳት አቅኚነት ላገለገሉ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች ቃለ ምልልስ አድርግ። በፕሮግራማቸው ላይ ምን ማስተካከያ ማድረግ አስፈልጓቸዋል? ረዳት አቅኚ መሆናቸውስ ምን ጥቅም አስገኝቶላቸዋል? የምታገኝ ከሆነ፣ ቃለ ምልልስ ከምታደርግላቸው ውስጥ አንደኛው ሌሎች የቤተሰቡ አባላት ባደረጉለት እርዳታና ድጋፍ ረዳት አቅኚ መሆን የቻለ አስፋፊ ቢሆን ጥሩ ነው። አንቀጽ 9ን ስትወያዩ፣ የወረዳ የበላይ ተመልካቹ ጉባኤያችሁን የሚጎበኝበት ወቅት የሚታወቅ ከሆነ ቀኑን ተናገር።

20 ደቂቃ-: “‘ክርስቶስን ተከተሉ!’ የተባለውን የአውራጃ ስብሰባ በዓለም ዙሪያ ለማስተዋወቅ የሚደረግ ጥረት።”* አንቀጽ 3ን ስትወያዩ ከ2007 የዓመት መጽሐፍ ገጽ 7 እስከ 10 ላይ የተወሰዱ አንዳንድ ሐሳቦችን እንዲሁም ካለፈው ዓመት የአውራጃ ስብሰባ መጋበዣ ወረቀት ጋር በተያያዘ በጉባኤያችሁ የተገኙ አስደሳች ተሞክሮዎችን ጨምረህ አቅርብ።

መዝሙር 6 (13) እና የመደምደሚያ ጸሎት

መስከረም 3 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 24 (50)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የነሐሴ ወር የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው።

15 ደቂቃ:- “መብቶቻችንን ከፍ አድርገን እንመለከታለን!”* ጊዜ በፈቀደልህ መጠን አድማጮች ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ በተጠቀሱት ጥቅሶች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ።

20 ደቂቃ:- “መጽሔት የምናበረክትላቸውን ሰዎች ጥናት ማስጀመር የምንችለው እንዴት ነው?”* በአንቀጽ 2 ላይ ከቀረቡት ሐሳቦች አንዱን በመጠቀም አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። አስፋፊዎች፣ ለግለሰቡ ጥናቱ እንዴት እንደሚካሄድ ካሳዩትና ሁለት ጊዜ ካስጠኑት እንዲሁም ጥናቱ እንደሚቀጥል ከተሰማቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ብለው ሪፖርት ማድረግ እንደሚችሉ አስታውሳቸው።

መዝሙር 4 (8) እና የመደምደሚያ ጸሎት

[የግርጌ ማስታወሻዎች ]

አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ