የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
ማሳሰቢያ:- የመንግሥት አገልግሎታችን የአውራጃ ስብሰባ በሚደረግባቸው ወራት በእያንዳንዱ ሳምንት በአገልግሎት ስብሰባ ላይ የሚቀርቡ ክፍሎችን ፕሮግራም ይዞ ይወጣል። ጉባኤዎች “ክርስቶስን ተከተሉ!” በተሰኘው የአውራጃ ስብሰባ ላይ ለመገኘት እንደ አስፈላጊነቱ ማስተካከያዎችን ማድረግ ይችላሉ። የሚቻል ከሆነ የአውራጃ ስብሰባው ሊደረግ አንድ ሳምንት ሲቀረው በምታደርጉት የአገልግሎት ስብሰባ ላይ በዚህ ወር የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ከወጡት ምክሮችና ማሳሰቢያዎች ውስጥ ጉባኤያችሁን የሚመለከቱትን ለመወያየት 15 ደቂቃ መመደብ ትችላላችሁ። የአውራጃ ስብሰባውን ካደረጋችሁ ከአንድ ወይም ከሁለት ወር በኋላ ደግሞ አስፋፊዎች ከስብሰባው ለአገልግሎት ጠቃሚ ሆኖ ያገኟቸውን ሐሳቦች ለመከለስ እንዲችሉ በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ከ15 እስከ 20 ደቂቃ መድቡ። (ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት የሚለውን ክፍል መጠቀም ትችላላችሁ።) ክለሳውን ማቅረብ የሚኖርበት የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ነው። አድማጮች በአውራጃ ስብሰባው ላይ ያገኙትን ትምህርት በአገልግሎታቸው ተግባራዊ እያደረጉ ያሉት እንዴት እንደሆነ ወይም ተግባራዊ ለማድረግ ምን ዝግጅት እንዳደረጉ ጠይቃቸው።
መስከረም 10 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 97 (217)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በሚቀጥለው ሳምንት በነሐሴ 2007 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የተመሠረተ ክፍል እንደሚቀርብ አስታውሳቸው። በገጽ 4 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የነሐሴ 1 መጠበቂያ ግንብ እና የነሐሴ 2007 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። በሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ላይ አስፋፊው የሚያስተዋውቀው አንዱን መጽሔት ብቻ ቢሆንም ሌላኛውንም አያይዞ ያበረክታል።
15 ደቂቃ:- የጥያቄ ሣጥን። አንድ ሽማግሌ ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት ያቀርበዋል። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ የተጠቀሱ ጥቅሶችን አንብብና ተወያዩባቸው።
20 ደቂቃ:- “ኢየሱስ የተወውን ምሳሌ ተከተሉ።”* አድማጮች በሌሎች መልካም ምሳሌነት እንዴት እንደተጠቀሙ እንዲናገሩ ጋብዝ።
መዝሙር 53 (130) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መስከረም 17 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 83 (187)
5 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
20 ደቂቃ:- “ክርስቲያናዊ ክብርን በማንጸባረቅ ክርስቶስን ተከተሉ።”* በነሐሴ የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 5 ላይ በሚገኘው ርዕስ እንዲሁም “የአውራጃ ስብሰባ ማሳሰቢያዎች” ከሚለው ርዕስ ሥር በተወሰዱ አንዳንድ አስፈላጊ ነጥቦች ላይ ተመሥርቶ በጉባኤው ጸሐፊ በውይይት የሚቀርብ።
20 ደቂቃ:- ዓለም አቀፍ የወንድማማች ኅብረት። የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ምዕራፍ 16 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ።
መዝሙር 56 (135) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
መስከረም 24 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 70 (162)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ።
15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
20 ደቂቃ:- በጥቅምት ወር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ይበልጥ ማወቅ ትፈልጋለህ? በሚለው ትራክት ተጠቀሙ። በጥቅምት ወር የምናበረክተው መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶችን ነው። ፍላጎት ያለው ሰው ካጋጠመን ጥናት ለማስጀመር ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ይበልጥ ማወቅ ትፈልጋለህ? በሚለው ትራክት መጠቀም እንችላለን። ማግኘት የሚቻል ከሆነ አስተናጋጆች ትራክቱን ለእያንዳንዱ ተሰብሳቢ ካደሉ በኋላ ስለ ትራክቱ በአጭሩ ተወያዩ። የቤቱን ባለቤት መጀመሪያ በምናነጋግርበት ዕለት አሊያም በተመላልሶ መጠየቅ ወቅት ትራክቱን በሙሉ ወይም በከፊል ልንወያይበት እንደምንችል ግለጽ። በገጽ 4 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የነሐሴ 15 መጠበቂያ ግንብ እና የመስከረም 2007 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ የቤቱ ባለቤት መጽሔቶቹን መውሰድ ስላልፈለገ አስፋፊው ትራክት ሰጥቶት ሲሄድ የሚያሳይ ይሁን። ሁለተኛው ሠርቶ ማሳያ ደግሞ የቤቱ ባለቤት መጽሔቶቹን ከተቀበለው በኋላ አስፋፊው ትራክቱን ያበረክትለትና በገጽ 5 ላይ የሚገኘውን ሐሳብ ያወያየዋል፤ ከዚያም በሚቀጥለው ጊዜ በገጽ 6 ላይ የሚታየውን አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተባለውን ብሮሹር ሊያመጣለት እንደሚችል ይነግረዋል።
መዝሙር 100 (222) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ጥቅምት 1 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 20 (45)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የመስከረም ወር የአገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው።
15 ደቂቃ:- ያለፈው ዓመት የአገልግሎት እንቅስቃሴያችን ምን ይመስል ነበር? የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ጉባኤው ባከናወናቸው መልካም ነገሮች ላይ ትኩረት በማድረግ ያለፈውን የአገልግሎት ዓመት እንቅስቃሴ ይከልሳል። ለተደረጉት መልካም ነገሮች አመስግናቸው። በያዝነው የአገልግሎት ዓመት ጉባኤው ትኩረት አድርጎ ሊሠራባቸው የሚገቡ አንድ ወይም ሁለት ነጥቦችን ጥቀስ። አቅኚዎች ያከናወኑትን ትጋት የታከለበት ሥራ በመጥቀስ አመስግናቸው። አገልግሎት ያቆሙ አስፋፊዎችን ለመርዳት የተደረገው ጥረት ያስገኘውን መልካም ውጤት ተናገር።
20 ደቂቃ:- “አገልግሎታችንን ለማስፋት ጥረት እናድርግ።”* አገልግሎታቸውን ማስፋት የቻሉ ወንድሞችና እህቶች የሰጧቸውን አንዳንድ ሐሳቦች ጨምረህ አቅርብ። እንዲሁም አገልግሎታቸውን ይበልጥ ለማስፋት የሚያስችሏቸውን አጋጣሚዎች ለማግኘት ጥረት ማድረጋቸውን የቀጠሉት እንዴት እንደሆነ እንዲናገሩ ጋብዝ። ሐሳብ የሚሰጡ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎችን አስቀድመህ ልታዘጋጅ ትችላለህ።
መዝሙር 2 (4) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
[የግርጌ ማስታወሻዎች ]
አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው።