ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች፦ መስከረም:- ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?፤ ጥቅምት:- መጽሔቶች እና ትራክት ቁጥር 26 (ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ይበልጥ ማወቅ ትፈልጋለህ?)፤ ኅዳር:- ነቅተህ ጠብቅ!፤ ታኅሣሥ:- ታላቅ ሰው ወይም ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው?
◼ የመስከረም ወር አምስት ቅዳሜና እሁዶች ስላሉት ረዳት አቅኚ ለመሆን አመቺ ነው።
◼ በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች የአስፋፊዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ገጽ 104 አንቀጽ 1 ላይ የሚገኘውን መመሪያ ማስታወሳችን ጥሩ ይሆናል። ይህ አንቀጽ በተመደብንበት የአገልግሎት ክልል ውስጥ ብቻ በማገልገል ለወንድሞቻችንም ሆነ በአገልግሎት ክልሉ ውስጥ ለሚኖሩት ሰዎች አሳቢነት ማሳየት እንደምንችል ይገልጻል። (1 ቆሮ. 14:40) በተለይ በአንድ የመንግሥት አዳራሽ የሚጠቀሙ የተለያዩ ጉባኤዎች ባሉበት አካባቢ ይህን ማድረግ በጣም አስፈላጊ ነው። አንድ ጉባኤ የሚሰበሰብበት የመንግሥት አዳራሽ ከጉባኤው የአገልግሎት ክልል ውጭ ከሆነና ጉባኤው በአንዳንድ ምክንያቶች የተነሳ የስምሪት ስብሰባውን በዚያ ለማድረግ ከወሰነ በዚህ ጉባኤ የሚገኙ አስፋፊዎች የመንግሥት አዳራሹ ያለበት ሰፈር ክልላቸው ስላልሆነ በዚያ አካባቢ አገልግሎት መጀመራቸው ተገቢ ላይሆን ይችላል። እንዲህ ያለ ጥንቃቄ ማድረጋችን ወንድሞችና እህቶች በአካባቢው የሚኖሩ ሰዎችን በተደጋጋሚ የሚያነጋግሩበትን አጋጣሚ ያስቀራል፤ ይህ ደግሞ ያ አካባቢ የሚገኝበትን ክልል ለወሰዱ ወንድሞች አገልግሎት አስቸጋሪ እንዳይሆንባቸው ያደርጋል።
◼ ጉባኤዎች በሚቀጥለው ወር ከሚልኩት የጽሑፍ ትእዛዝ ጋር የ2007 የመጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! ጥራዞችን፣ የ2007 የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ጽሑፎች ማውጫን እንዲሁም በሲዲ የተዘጋጀውን የ2007 ዎች ታወር ላይብረሪ ማዘዝ መጀመር ይኖርባቸዋል። የ2007 ዎች ታወር ላይብረሪ የተዘጋጀው ለተጠመቁ የጉባኤው አባላት ሲሆን ይህንንም ማግኘት የሚቻለው በጉባኤ በኩል ብቻ መሆኑን አስታውሱ።
◼ በታኅሣሥ ወር በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ጂሆቫስ ዊትነስስ—ኦርጋናይዝድ ቱ ሼር ዘ ጉድ ኒውስ (ምሥራቹን ለመስበክ የተደራጁት የይሖዋ ምሥክሮች) የተሰኘውን ፊልም እንከልሳለን። ፊልሙን ማግኘት የምትፈልጉ ከሆነ በተቻለ ፍጥነት በጉባኤው በኩል ማዘዝ ይኖርባችኋል።
◼ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ አሊያም እሱ የወከለው ሌላ ወንድም የሰኔን፣ የሐምሌንና የነሐሴን የጉባኤ ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። የሒሳብ ምርመራው ውጤት የሚቀጥለው የሒሳብ ሪፖርት ከቀረበ በኋላ ለጉባኤው መነበብ አለበት።—ለጉባኤ ሒሳብ አያያዝ የወጣ መመሪያ (S-27) የሚለውን ተመልከት።