የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 9/07 ገጽ 3
  • የጥያቄ ሣጥን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የጥያቄ ሣጥን
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ‘በተገቢው ጊዜ ምግብ’ እያገኘህ ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • በክፍል 2 ሥር የሚገኙ ተጨማሪ መረጃዎች
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • በክፍል 1 ሥር የሚገኙ ተጨማሪ መረጃዎች
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • በክፍል 4 ሥር የሚገኙ ተጨማሪ መረጃዎች
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
km 9/07 ገጽ 3

የጥያቄ ሣጥን

◼ አንዳንድ የይሖዋ ምሥክሮች በቅዱሳን መጻሕፍት ላይ ምርምር ለማድረግ ወይም እርስ በርስ ለመከራከር የሚያቋቁሟቸው ቡድኖች ‘በታማኝና ልባም ባሪያ’ ዘንድ ተቀባይነት አላቸው?—ማቴ. 24:45, 47 የ1954 ትርጉም

በፍጹም የላቸውም። ይሁን እንጂ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ጥቂት የድርጅታችን አባላት ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በተያያዙ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ምርምር ለማድረግ የሚያስችሏቸውን የራሳቸውን ቡድኖች አቋቁመዋል። አንዳንዶች የአዲስ ዓለም ትርጉምን ትክክለኛነት መመርመር ስለፈለጉ የራሳቸውን ቡድን አቋቁመው መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈባቸው የዕብራይስጥና የግሪክኛ ቋንቋዎች ላይ ጥናት ማካሄድ ጀምረዋል። ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ተያያዥነት ባላቸው ሳይንሳዊ ጉዳዮችም ላይ ምርምር ያደርጋሉ። ሐሳባቸውን ለመለዋወጥና በዚያ ላይ ለመከራከር የሚያስችሉ ድረ ገጾችንና ቻት ሩሞችን የከፈቱ ከመሆኑም በላይ ስብሰባዎችን አካሂደዋል፤ እንዲሁም ጽሑፎችን አሳትመዋል። ይህንንም ያደረጉት የደረሱባቸውን ግኝቶች ለሌሎች ለማሳወቅ ብሎም በክርስቲያናዊ ስብሰባዎቻችንና በጽሑፎቻችን ላይ በሚቀርቡት ትምህርቶች ላይ ተጨማሪ ሐሳቦችን ለማከል ስለፈለጉ ነው።

በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የይሖዋ ሕዝቦች በጉባኤ፣ በወረዳ፣ በልዩና በአውራጃ ስብሰባዎች እንዲሁም የይሖዋ ድርጅት በሚያወጣቸው ጽሑፎች አማካኝነት በቂ የሆነ መንፈሳዊ መመሪያና ማበረታቻ እያገኙ ነው። ይሖዋ፣ ሕዝቦቹ በሙሉ “አንድ ልብ፣ አንድ ሐሳብ” እንዲኖራቸው እንዲሁም ‘በእምነት ጸንተው’ መቀጠል ይችሉ ዘንድ በቅዱስ መንፈሱና በቃሉ ውስጥ በሚገኘው እውነት አማካኝነት የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ እያቀረበ ነው። (1 ቆሮ. 1:10፤ ቈላ. 2:6, 7) ሁላችንም በዚህ በመጨረሻ ዘመን ይሖዋ ለሚያቀርብልን መንፈሳዊ ዝግጅቶች አመስጋኞች እንደሆንን ምንም ጥርጥር የለውም። በመሆኑም “ታማኝና ልባም ባሪያ” ከሚሰጠው አመራር ውጭ የሚታተሙ ጽሑፎች፣ የሚደረጉ ስብሰባዎች እንዲሁም የሚከፈቱ ድረ ገጾች ፈጽሞ ተቀባይነት የላቸውም።—ማቴ. 24:45-47 የ1954 ትርጉም

ግለሰቦች የማሰብ ችሎታቸውን ተጠቅመው ምሥራቹን የመስበኩን ሥራ ለመደገፍ ማሰባቸው የሚያስመሰግናቸው ነው። ይሁን እንጂ በተናጠል የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ በሚገኘው ጉባኤው አማካኝነት እያከናወናቸው ካሉ ነገሮች ትኩረት የሚሰርቅ መሆን አይኖርበትም። በመጀመሪያው መቶ ዘመን ሐዋርያው ጳውሎስ “መጨረሻ ለሌለው የትውልዶች ታሪክ ራሳቸውን አሳልፈው እንዳይሰጡ እዘዛቸው። እነዚህ ነገሮች በእምነት ከሆነው ከእግዚአብሔር ሥራ ይልቅ ክርክርን ያነሣሣሉ” በማለት ክርስቲያኖች አድካሚ በሆኑና ጊዜን በሚያባክኑ ርዕሰ ጉዳዮች እንዳይጠመዱ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር። (1 ጢሞ. 1:3-7) ሁሉም ክርስቲያኖች “ከንቱ ከሆነ ክርክርና ከትውልድ ሐረግ ቈጠራ፣ ከጭቅጭቅና ስለ ሕግ ከሚነሣ ጠብ” ለመራቅ ጥረት ማድረግ ይኖርባቸዋል። ምክንያቱም እንዲህ ማድረግ “ዋጋ ቢስና ከንቱ ነው።”—ቲቶ 3:9

ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትና ምርምር ማድረግ የሚፈልጉ ክርስቲያኖች ቅዱሳን ጽሑፎችን ጠለቅ ብሎ ማስተዋል፣ “ቅዱሳን መጻሕፍት ሁሉ በአምላክ መንፈስ አነሳሽነት የተጻፉና ጠቃሚ ናቸው” በተባሉት እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በሆኑት በዳንኤል፣ በኢሳይያስና በራእይ መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ትንቢቶችን በሚያብራሩ ሌሎች ጽሑፎች እንዲጠቀሙ እናበረታታቸዋለን። እነዚህ መጻሕፍት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥናት ለማድረግ ብሎም ለማሰላሰል የሚረዱ በርካታ ትምህርቶችን ይዘዋል። በመሆኑም እነዚህን ጽሑፎች በማንበብ የአምላክን ‘ፈቃድ እውቀትና መንፈሳዊ ጥበብ መረዳት’ እንችላለን፤ ይህ ደግሞ ‘ለጌታ እንደሚገባ በመኖር በሁሉም ደስ እንድናሰኘው’ ያስችለናል። ከዚህም በላይ ‘በመልካም ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራን አምላክን በማወቅ እያደግን’ እንድንሄድ ያደርገናል።—ቈላ. 1:9, 10

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ