የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
ጥቅምት 8 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 26 (56)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በገጽ 8 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የመስከረም 1 መጠበቂያ ግንብ እና የመስከረም 2007 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። በሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ላይ አስፋፊው የሚያስተዋውቀው አንዱን መጽሔት ብቻ ቢሆንም ሌላኛውንም አያይዞ ያበረክታል።
20 ደቂቃ:- የይሖዋን ድርጅት የሙጥኝ ብላችሁ ኑሩ። የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ በተባለው መጽሐፍ ምዕራፍ 17 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ።
15 ደቂቃ:- ፈጣሪህን ለማክበር መንፈሳዊ ግቦች አውጣ። በሐምሌ 15, 2004 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 21-23 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ወንድሞች ስላወጧቸው መንፈሳዊ ግቦችና እነዚህ ግቦች ላይ ለመድረስ እያደረጉት ስላለው ጥረት እንዲናገሩ ጋብዝ። ሐሳብ የሚሰጡ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎችን አስቀድመህ ልታዘጋጅ ትችላለህ።
መዝሙር 5 (10)
ጥቅምት 15 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 31 (67)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።
20 ደቂቃ:- እውነት በምታስተምራቸው ሰዎች ልብ ውስጥ ፍሬ እያፈራ ነው? በየካቲት 1, 2005 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 28-30 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በተባለው መጽሐፍ ውስጥ የሚገኙት ጥያቄዎች የተዘጋጁበት መንገድ በተማሪው ልብ ውስጥ ያለውን ነገር እንድናስተውል የሚረዳን እንዴት እንደሆነ የሚያሳዩ አንዳንድ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ። ምዕራፍ 1 አንቀጽ 19ን፣ ምዕራፍ 2 አንቀጽ 4ን፣ ምዕራፍ 3 አንቀጽ 24ን እና ምዕራፍ 4 አንቀጽ 18ን እንደ ምሳሌ መጠቀም ትችላለህ። አስፋፊዎች ይህ መጽሐፍ ያሉትን የተለያዩ ገጽታዎች በጥሩ ሁኔታ እንዲጠቀሙበት አበረታታቸው።
15 ደቂቃ:- ታስታውሳለህ? በነሐሴ 15, 2007 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 19 ላይ ተመሥርቶ ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ።
መዝሙር 64 (151)
ጥቅምት 22 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 78 (175)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ። በገጽ 8 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የመስከረም 15 መጠበቂያ ግንብ እና የጥቅምት 2007 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
20 ደቂቃ:- እንደ ብርሃን ልጆች ኑሩ። በንግግርና በቃለ ምልልስ የሚቀርብ። ከዚህ ዓለም ጨለማ የወጣን ከመሆኑም ባሻገር ይሖዋ በሚሰጠው ብርሃን ለመመራት ወስነናል። (ኤፌ. 5:8, 9) ይህ ደግሞ ዓላማ ያለው የተሻለ ሕይወት እንድንመራ አስችሎናል። (1 ጢሞ. 4:8) ይህ ብርሃን ተስፋም ፈንጥቆልናል። (ሮሜ 15:4) ከይሖዋ ጋር ጥሩ ዝምድና ለመመሥረትና ይህንንም ጠብቀው ለማቆየት በሚያደርጉት ጥረት ከባድ ችግሮች አጋጥመዋቸው ማሸነፍ ለቻሉ ሁለት ወይም ሦስት አስፋፊዎች ቃለ ምልልስ አድርግ። ወደ እውነት ሲመጡ ምን ችግሮች አጋጥመዋቸዋል? ችግሮቹን ማሸነፍ የቻሉትስ እንዴት ነው? በአሁኑ ወቅት ሕይወታቸው የተሻለ የሆነው በምን መንገድ ነው? በእውነት ውስጥ ጸንተው እንዲቀጥሉ የረዳቸው ምንድን ነው? ሁሉም ከይሖዋ ጋር የመሠረቱትን ዝምድና በየጊዜው እንዲያጠናክሩና ይሖዋ ለገለጠላቸው እውነት ያላቸውን ከፍተኛ አድናቆት በተግባር እንዲያሳዩ በማበረታታት ክፍልህን ደምድም።—2 ጴጥ. 1:5-8
መዝሙር 21 (46)
ጥቅምት 29 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 17 (38)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የጥቅምት ወር የአገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በኅዳር ወር የሚበረከተውን ጽሑፍ ከተናገርክ በኋላ አንድ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
15 ደቂቃ:- “የንቁ! መጽሔት ልዩ እትም በኅዳር ወር ውስጥ ይበረከታል!”* የኅዳር ወር የንቁ! መጽሔት እትምን በአጭሩ ከልስ። ከዚያም በጥያቄና መልስ ተወያዩበት። አንቀጽ 3ን ስትወያዩ ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆነ አቀራረብ በመጠቀም የኅዳር 2007 ንቁ! መጽሔት ሲበረከት የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ሠርቶ ማሳያው፣ አስፋፊው ውይይቱን ከመጨረሱ በፊት በቀጣዩ ጊዜ ለሚያደርጉት ውይይት መሠረት ሲጥል የሚያሳይ ይሁን።
20 ደቂቃ:- “ለድሆች ተስፋ ፈንጥቁላቸው።”* አንቀጽ 2ን ስትወያዩ ከጥቅምት 2003 ንቁ! ከገጽ 14-15 ላይ አንዳንድ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ።
መዝሙር 83 (187)
ኅዳር 5 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 67 (156)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ:- በአምላካዊ ጥበብ አማካኝነት ልጆቻችሁን ከጥቃት መጠበቅ የምትችሉት እንዴት ነው? በጥር 1, 2005 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 23-27 ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር።
20 ደቂቃ:- “እርስ በርስ ለመበረታታት የሚያስችል ዝግጅት።”* ተጓዥ የበላይ ተመልካቹ ጉባኤውን በጎበኘበት ወቅት እንዴት ማበረታቻ እንዳገኙ ለይተው እንዲጠቅሱ አድማጮችን ጋብዝ። ሐሳብ የሚሰጡ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎችን አስቀድመህ ልታዘጋጅ ትችላለህ።
መዝሙር 30 (63)
[የግርጌ ማስታወሻዎች ]
አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው።