የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 11/07 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ኅዳር 12 የሚጀምር ሳምንት
  • ኅዳር 19 የሚጀምር ሳምንት
  • ኅዳር 26 የሚጀምር ሳምንት
  • ታኅሣሥ 3 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
km 11/07 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

ኅዳር 12 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 43 (98)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በገጽ 4 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የጥቅምት 1 መጠበቂያ ግንብ እና የጥቅምት 2007 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። በሁለቱም ሠርቶ ማሳያዎች ላይ አስፋፊው የሚያስተዋውቀው አንዱን መጽሔት ብቻ ቢሆንም ሌላኛውንም አያይዞ ያበረክታል።

15 ደቂቃ:- “አዲስ የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም” ወይም “አዲስ የልዩ ስብሰባ ቀን ፕሮግራም” በሚለው ርዕስ ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። (ጉባኤያችሁ ከሁለቱ ስብሰባዎች በቅድሚያ የሚያደርገውን መርጠህ ለዚያ ስብሰባ የተዘጋጀውን ክፍል አቅርብ፤ ሌላኛው ክፍል በሌላ ጊዜ ይቀርባል።) ስብሰባው የሚደረግበት ቀን የሚታወቅ ከሆነ ተናገር።

20 ደቂቃ:- “እንደ ጥበበኞች ኑሩ።”* ጊዜ በፈቀደልህ መጠን አድማጮች ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ በተጠቀሱት ጥቅሶች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ።

መዝሙር 81 (181)

ኅዳር 19 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 100 (222)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በታኅሣሥ ወር የሚበረከተውን ጽሑፍ ከተናገርክ በኋላ ጽሑፉን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ አንድ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።

15 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

20 ደቂቃ:- “ወደኋላ አትበሉ!”* አንቀጽ 5ን ስትወያዩ ጥናቶቻቸው ወደ እውነት የመጡላቸው አስፋፊዎች ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ። ጥናቶች እድገት እንዲያደርጉ በሚያስችል መንገድ ጥናቱን መምራት የሚክስና አስደሳች የሆነው እንዴት ነው? ሐሳብ የሚሰጡ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎችን አስቀድመህ ልታዘጋጅ ትችላለህ።

መዝሙር 23 (48)

ኅዳር 26 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 76 (172)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ። አስፋፊዎች የኅዳር ወር የአገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። በገጽ 4 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የጥቅምት 15 መጠበቂያ ግንብ እና የኅዳር 2007 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።

15 ደቂቃ:- ፍቅራችሁን ማስፋት ትችላላችሁ? በጥር 1, 2007 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 9-11 ላይ ተመሥርቶ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር።

20 ደቂቃ:- እናንት ወጣቶች—ይሖዋን ማመስገን የምትችሉት እንዴት ነው?* በሰኔ  15, 2005 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 26-28 ከአንቀጽ 15-19 ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። ለአንቀጾቹ የቀረቡትን ጥያቄዎች ተጠቀም። አንቀጽ 18ን ስትወያዩ ወጣቶች በትምህርት ቤታቸው ውስጥ ለተማሪዎች ወይም ለአስተማሪዎች እንዴት እንደመሠከሩ እንዲናገሩ ጋብዝ።

መዝሙር 35 (79)

ታኅሣሥ 3 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 34 (77)

15 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። የጥያቄ ሣጥኑን አቅርብ።

15 ደቂቃ:- በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ሰዎች በረከት የሚሆኑ ተማሪዎችን የሚያሠለጥን ትምህርት ቤት። በኅዳር 15, 2006 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 10-13 ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። በአገልጋዮች ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ለተካፈሉ በጉባኤያችሁ የሚገኙ ሽማግሌዎች ወይም የጉባኤ አገልጋዮች አጭር ቃለ ምልልስ አድርግ። ትምህርት ቤቱ የተሻሉ ወንጌላውያን፣ እረኞችና አስተማሪዎች በመሆን ረገድ የረዳቸው እንዴት ነው? ብቃቱን የሚያሟሉ ወንድሞች በአገልጋዮች ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት የመሠልጠን ግብ እንዲያወጡ አበረታታ።

15 ደቂቃ:- “የመንግሥቱን ተስፋ ለሌሎች እንናገራለን።”* ጊዜ በፈቀደልህ መጠን አድማጮች ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ በተጠቀሱ ጥቅሶች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ አድርግ።

መዝሙር 39 (86)

[የግርጌ ማስታወሻዎች ]

አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ