የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 1/08 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ጥር 14 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥር 21 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥር 28 የሚጀምር ሳምንት
  • የካቲት 4 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
km 1/08 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

ጥር 14 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 22 (47)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። በገጽ 8 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የታኅሣሥ 1 መጠበቂያ ግንብ እና የታኅሣሥ 2007 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።

15 ደቂቃ:- “በአገልግሎት ላይ የምታሳልፉትን ጊዜ በሚገባ ተጠቀሙበት።”* የመስክ ስምሪት ስብሰባዎችን አበረታች በሆነ መንገድ በመምራት ረገድ ምሳሌ ለሆነ አንድ ወንድም ቃለ ምልልስ አድርግ። ስብሰባውን በተሻለ መንገድ ለመምራት ብሎም አስፋፊዎች በተቻለ መጠን አብዛኛውን ጊዜ በአገልግሎት እንዲያሳልፉ ለመርዳት ዝግጅት የሚያደርገው እንዴት ነው?

20 ደቂቃ:- ‘ንግግራችሁ ሁልጊዜ በጨው የተቀመመ ይሁን።’* አንቀጽ 2ን ስትወያዩ ዮሐንስ 4:7-15, 39ን አንብብ።

መዝሙር 38 (85)

ጥር 21 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 96 (215)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎችና ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች። በየካቲት ወር የሚበረከተውን ጽሑፍ ከተናገርክ በኋላ ጽሑፉን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ አንድ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። የካቲት 4 በሚጀምር ሳምንት በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ለሚደረገው ውይይት ሁሉም በደም ምትክ የሚሰጥ ሕክምና—የሕሙማንን መብትና ፍላጎት ማክበር የሚለውን የቪዲዮ ፊልም አይተው እንዲመጡ አበረታታ።

10 ደቂቃ:- ቅዱሳን መጻሕፍትን በየዕለቱ መመርመር የተባለውን ቡክሌት በጥሩ ሁኔታ እየተጠቀማችሁበት ነው? ቅዱሳን መጻሕፍትን በየዕለቱ መመርመር—2008 በተባለው ቡክሌት መቅድም ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ሁላችንም በየቀኑ ጊዜ መድበን የዕለቱን ጥቅስና በዚያ ላይ የተሰጠውን ሐሳብ ማንበባችን ያለውን ጠቀሜታ ተናገር። የዕለቱን ጥቅስ ስለሚያነቡበት ፕሮግራምና እንዲህ ማድረጋቸው ስላስገኘላቸው ጥቅም እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ። ሐሳብ የሚሰጡ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎችን አስቀድመህ ማዘጋጀት ትችላለህ። በ2008 የዓመት ጥቅስ ላይ አጠር ያለ ሐሳብ ስጥ።

25 ደቂቃ:- ‘ምሥራቹን በሚገባ መሥክሩ።’* (ከአን. 1-10) በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ። ፕሮግራማቸው የተጣበበ ቢሆንም ወይም የአቅም ገደብ ቢኖርባቸውም እንኳ ባለፈው ዓመት ረዳት አቅኚ ሆነው ላገለገሉ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች ቃለ ምልልስ አድርግ። ረዳት አቅኚ መሆን የቻሉት እንዴት ነበር? ምን በረከቶችን አግኝተዋል? አንቀጽ 7ን ስትወያዩ በመጋቢት፣ በሚያዝያና በግንቦት ወራት የስምሪት ስብሰባዎች የሚደረጉበትን ፕሮግራም ተናገር።

መዝሙር 79 (177)

ጥር 28 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 34 (77)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የጥር ወር የአገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ። በታኅሣሥ 15 መጠበቂያ ግንብ እና በጥር 2008 ንቁ! መጽሔቶች ላይ ተመሥርቶ ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። የሁለቱን መጽሔቶች ይዘት በአጭሩ ከተናገርክ በኋላ በክልላችሁ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ይበልጥ የሚማርከው የትኛው ርዕስ እንደሆነና ለምን እንዲህ እንዳሉ አድማጮችን ጠይቅ። አድማጮች በአገልግሎት ላይ ሊያስተዋውቁት ካሰቡት ርዕስ ውስጥ ማራኪ ሆነው ያገኟቸውን አንዳንድ ነጥቦች እንዲናገሩ ጋብዝ። ውይይት ለመጀመር ምን ጥያቄ መጠቀም ይቻላል? ከዚያስ በርዕሱ ውስጥ ያለ የትኛው ጥቅስ ቢነበብ ጥሩ ነው? የሚነበበው ጥቅስ ከርዕሱ ጋር የሚያያዘው እንዴት ነው? በገጽ 8 ላይ የሚገኙትን የናሙና መግቢያዎች በመጠቀም እያንዳንዱን መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።

20 ደቂቃ:- ‘ምሥራቹን በሚገባ መሥክሩ።’* (ከአን. 11-17) አንቀጽ 14ን ስትወያዩ የመታሰቢያው በዓል ልዩ የመጋበዣ ወረቀት ደርሷችሁ ከሆነ አንድ ቅጂ ለአድማጮች እንዲታደል አድርግ፤ እንዲሁም መጋበዣውን በክልላችሁ ለማሰራጨት የተደረጉትን ዝግጅቶች ጥቀስ።

15 ደቂቃ:- “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችሁ የመንግሥቱ ምሥራች አስፋፊዎች እንዲሆኑ እርዷቸው።”* ጊዜ በፈቀደልህ መጠን አድማጮች ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ በተጠቀሱ ጥቅሶች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ።

መዝሙር 54 (132)

የካቲት 4 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 20 (45)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የጥያቄ ሣጥን–1ን አቅርብ።

10 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

25 ደቂቃ:- “ዛሬ ነገ እያልክ ነው?” በሽማግሌ የሚቀርብ። የሕሙማን መብትና ፍላጎት በተባለው ፊልም ላይ ውይይት ለማድረግ ታስበው በተዘጋጁት ጥያቄዎች አማካኝነት በቀጥታ ውይይቱን ጀምር። መደምደሚያህ ላይ የመጨረሻውን አንቀጽ አንብብ። እንዲሁም አስፋፊዎች ለማጣቀሻ የቀረቡላቸውን በመጠበቂያ ግንብ እና በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የሚገኙትን ርዕሶች በጥንቃቄ እንዲያነቡ አበረታታ። እስከ አሁን ድረስ የሕክምና መመሪያ ካርዱን ያልሞሉ አስፋፊዎች የደም ክፍልፋዮችንና የሕክምና ዓይነቶችን በሚመለከት የራሳቸውን ውሳኔ ለማድረግ በኅዳር 2006 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ላይ የሚገኙትን ቅጾች እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ ግለጽ። እንዲሁም በቅጾቹ ላይ ያሰፈሩትን ውሳኔ እንዴት ወደ ሕክምና መመሪያ ካርዱ እንደሚገለብጡ አስረዳ። የሕክምና መመሪያ ካርዱን የሞሉ አስፋፊዎችም ቢሆኑ ቀደም ሲል ያደረጓቸውን ውሳኔዎች እንደገና ማጤንና አስፈላጊ ሆኖ ካገኙት አዲስ ካርድ መሙላት ይችላሉ።

መዝሙር 2 (4)

[የግርጌ ማስታወሻዎች]

አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ