የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 1/08 ገጽ 7
  • ማስታወቂያዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማስታወቂያዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
km 1/08 ገጽ 7

ማስታወቂያዎች

◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች ጥር:- እውቀት ወይም ነቅተህ ጠብቅ!፤ የካቲት:- ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው?፤ መጋቢት:- ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? እና ሚያዝያ:- መጽሔቶች።

◼ የመጋቢት ወር አምስት ቅዳሜና እሁዶች ስላሉት ረዳት አቅኚ ለመሆን አመቺ ነው።

◼ ከየካቲት ጀምሮ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች የሚያቀርቡት አዲሱ የሕዝብ ንግግር “አስጨናቂ ሁኔታዎች ሲያጋጥሟችሁ እርዳታ ማግኘት የምትችሉት ከየት ነው?” የሚል ጭብጥ ይኖረዋል።

◼ ጉባኤዎች በዚህ ዓመት ቅዳሜ፣ መጋቢት 22 ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ለሚከበረው የክርስቶስ ሞት መታሰቢያ በዓል ተገቢውን ዝግጅት ማድረግ ይገባቸዋል። ምንም እንኳ ንግግሩን ቀደም ብሎ መጀመር የሚቻል ቢሆንም የመታሰቢያው ቂጣና ወይን ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት መዞር የለበትም። በአካባቢያችሁ ፀሐይ ሙሉ በሙሉ የምትጠልቅበትን ትክክለኛ ሰዓት ጠይቃችሁ ተረዱ። እያንዳንዱ ጉባኤ ራሱን ችሎ የመታሰቢያ በዓሉን ለማክበር ጥረት ማድረግ ይኖርበታል። ይሁንና እንዲህ ማድረግ ሁልጊዜ ይሳካል ማለት አይደለም። የጉባኤ ስብሰባዎቻቸውን በአንድ የመንግሥት አዳራሽ የሚያደርጉ በርካታ ጉባኤዎች ካሉ ከመካከላቸው አንዳንዶቹ ለዚያ ምሽት ሌላ መሰብሰቢያ ቦታ ማግኘት ይችሉ ይሆናል። ሁሉም እርስ በርስ በመጨዋወት ከዝግጅቱ ሙሉ ጥቅም ማግኘት እንዲችሉ ለማድረግ ሲባል፣ ከተቻለ ሁለት ጉባኤዎች በተከታታይ በሚያደርጓቸው ስብሰባዎች መካከል ቢያንስ የ40 ደቂቃ ልዩነት እንዲኖር ሐሳብ እናቀርብላችኋለን። ተሳፋሪዎችን ማውረድንና መጫንን ጨምሮ ለተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴና ለመኪና ማቆሚያ ቦታም ትኩረት መስጠት ይገባል። ለጉባኤው የተሻለ የሚሆነው ዝግጅት የትኛው እንደሆነ የሽማግሌዎች አካል መወሰን ይኖርበታል።

◼ በ2008 በሚከበረው የመታሰቢያው በዓል ሰሞን የሚሰጠው ልዩ የሕዝብ ንግግር መጋቢት 31, 2008 በሚጀምረው ሳምንት ውስጥ ይቀርባል። የንግግሩ ርዕስ “የሰውን ዘር ለመግዛት ብቃት ያለው ማን ነው?” የሚል ነው። በዚያ ሳምንት የወረዳ የበላይ ተመልካች ጉብኝት ወይም የወረዳ አሊያም የልዩ ስብሰባ ያላቸው ጉባኤዎች ልዩ የሕዝብ ንግግሩን በቀጣዩ ሳምንት ማቅረብ ይችላሉ። በየትኛውም ጉባኤ ልዩ የሕዝብ ንግግሩን መጋቢት 31 ከሚጀምረው ሳምንት በፊት መቅረብ አይኖርበትም።

◼ የጉባኤ ጸሐፊዎች በጉባኤያችሁ ያለ እያንዳንዱ የዘወትር አቅኚ በጉባኤው ፋይል ውስጥ የዘወትር አቅኚ የሹመት ደብዳቤ (S-202) እንዳለው አረጋግጡ። በፋይል ውስጥ የማይገኝ ከሆነ ቅርንጫፍ ቢሮውን መጠየቅ ትችላላችሁ።

◼ አዲስ የደረሱን ጽሑፎች:- እንግሊዝኛ:- የውዳሴ መዝሙር በኤምፒ 3፣ የአዲስ ዓለም ትርጉም በኤምፒ 3፣ አምላክን የሚያስከብር ግብ ላይ ለመድረስ ተጣጣሩ በዲቪዲ።

◼ በድጋሚ የደረሱን ጽሑፎች:- አማርኛ:- የቤተሰብ ደስታ፣ ታላቅ ሰው፣ ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ፣ በደስታ ኑር፣ ትራክት ቁ. 19 (ይህ ዓለም ከጥፋት ይተርፍ ይሆን?)፣ ትራክት ቁ. 21 (በቤተሰብ ኑሮ ተደሰት)፣ ትራክት ቁ. 27 (መከራና ሥቃይ ሁሉ በቅርቡ ይወገዳል)፣ ቀለል ባለ ቻይንኛ:- ክርኤተር፤ እንግሊዝኛ:- ኦል ስክሪፕቸርስ፣ ክርኤሽን፣ አዋጅ ነጋሪዎች፣ የውዳሴ መዝሙር (ትልቁ)፣ ከታላቁ አስተማሪ ተማሩ፣ ባለማጣቀሻው መጽሐፍ ቅዱስ (Rbi-8)፣ ሮድ ቱ ላይፍ፤ ኦሮምኛ:- ትራክት ቁ. 15 (ሰላም በሰፈነበት አዲስ ዓለም ውስጥ የሚገኝ ሕይወት)

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ