ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች
በአማን፣ በሰበታና በሆለታ የመንግሥት አዳራሾች ተሠርተዋል፤ እነዚህን ጨምሮ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የሚገኙት የመንግሥት አዳራሾች ብዛት 112 ደርሷል።
በመስከረም 2007 16 የአቅኚዎች አገልግሎት ትምህርት ቤት ክፍሎች የተካሄዱ ሲሆን በድምሩ 385 አቅኚዎች በትምህርት ቤቱ ተካፍለዋል።
በመስከረም ወር የዘወትር አቅኚዎች ቁጥር ለመጀመሪያ ጊዜ ከ1,000 በላይ መድረሱ አስደስቶናል፤ በዚህ ወር የነበረን አጠቃላይ የአቅኚዎች ቁጥር 1,076 ነው።
“ክርስቶስን ተከተሉ” በሚል ጭብጥ ባደረግናቸው 20 የአውራጃ ስብሰባዎች ላይ በድምሩ 14,687 የደረሰ ከፍተኛ የተሰብሳቢዎች ቁጥር የነበረ ሲሆን የተጠማቂዎችም ብዛት 338 ነበር።
በዚህ ወር ከሚወጣው እትም ጀምሮ በኦሮምኛ ቋንቋ የሚዘጋጀው መጠበቂያ ግንብ ባለ ሙሉ ቀለም ይሆናል። የጥናት እትሙ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ከሚዘጋጀው ጋር አንድ ዓይነት ነው። በተጨማሪም የሚበረከተው እትም በየሦስት ወሩ ይወጣል።
በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ 56፣ በናዝሬት ሦስት እንዲሁም በአርባ ምንጭ፣ በድሬዳዋ፣ በጅማና በሻሸመኔ ሁለት ሁለት ጉባኤዎች ይገኛሉ።