የቲኦክራሲያዊ አገልግሎት ትምህርት ቤት
ክለሳ የካቲት 25, 2008 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከጥር 7 እስከ የካቲት 25, 2008 ድረስ ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል። [ማሳሰቢያ፦ ከጥያቄው ቀጥሎ መልሱ የሚገኝበት ጽሑፍ ካልተጠቀሰ መልሱን ለማግኘት በግልህ ምርምር ማድረግ ይኖርብሃል።—የአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 36-37ን ተመልከት።]
የንግግር ባሕርይ
1. አድማጮቻችን የምናነበውን ጥቅስ ትርጉም እንዲረዱ ምን ማድረግ ያስፈልገናል? እንዲህ ማድረግ የሚኖርብንስ ለምንድን ነው? [be ገጽ 228 አን. 1-2]
2. ንግግራችን የአድማጮቻችንን ግንዛቤ የሚያሰፋ መሆኑ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ይህን ማድረግ የምንችለውስ እንዴት ነው? [be ገጽ 230 አን. 3-5፣ ሣጥኑ]
3. ምርምር ማድረግ ንግግራችን ይበልጥ ግንዛቤ የሚያሰፋ እንዲሆን የሚያስችለው በምን መንገዶች ነው? [be ገጽ 231 አን. 1-3]
4. አድማጮች የሚያውቋቸውን ጥቅሶች ይበልጥ ትምህርት ሰጪ አድርገን ለማቅረብ ምን ማድረግ እንችላለን? [be ገጽ 231 አን. 4-5]
5. የምናነበውን ጥቅስ ከጉዳዩ ጋር እያገናዘብን ማብራራት አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? [be ገጽ 232 አን. 3-4]
ክፍል ቁ. 1
6. የማቴዎስ ወንጌል በዋነኝነት የተጻፈው ለአይሁዳውያን መሆኑን የሚጠቁመው ምንድን ነው? [bsi08-1 ገጽ 4 አን. 6-7]
7. ከመድረክ የሚተላለፉ ትምህርቶችን ለመቀበል ልባችንን ማዘጋጀት የምንችለው እንዴት ነው? (2 ዜና 20:33 የ1954 ትርጉም) [be ገጽ 13 አን. 4 እስከ ገጽ 14 አን. 4]
8. ወላጆች ልጆቻቸው “መዳን የሚገኝበትን ጥበብ” እንዲቀስሙ ለማሠልጠን ምን ማድረግ ይችላሉ? (2 ጢሞ. 3:15) [be ገጽ 16 አን. 3-4]
9. የማቴዎስ ወንጌል የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶችን ፍጻሜ ጎላ አድርጎ የሚገልጸው እንዴት ነው? [bsi08-1 ገጽ 5 አን. 32]
10. የማቴዎስ ወንጌል ኢየሱስን ተስፋ የተደረገው መሲሕና ንጉሥ እንደሆነ አድርጎ ይገልጸዋል፤ የማርቆስ ወንጌል ኢየሱስን የሚገልጸው እንዴት ነው? [bsi08-1 ገጽ 7 አን. 7-8]
ሳምንታዊው የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. በቁጣ ገንፍሎ መናገር ንዴትን አምቆ ለረጅም ጊዜ ከመያዝ የበለጠ ከባድ ኃጢአት ነው? (ማቴ. 5:21, 22 NW) [w08 1/15 “የይሖዋ ቃል ሕያው ነው—የማቴዎስ መጽሐፍ ጎላ ያሉ ነጥቦች”]
12. ክርስቲያኖች ‘ጤናማ ዓይን’ መያዝ የሚችሉት እንዴት ነው? (ማቴ. 6:22, 23) [w06 10/1 ገጽ 29]
13. ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን “ይህ ሁሉ ገብቷችኋል?” በማለት የጠየቃቸው ምን ነገር ሊያስገነዝባቸው ፈልጎ ነው? (ማቴ. 13:51, 52) [w08 1/15 “የይሖዋ ቃል ሕያው ነው—የማቴዎስ መጽሐፍ ጎላ ያሉ ነጥቦች”]
14. ኢየሱስ፣ የፈወሳቸውን ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ “ማንነቱን ለማንም እንዳይናገሩ” ያዛቸው የነበረው ለምንድን ነው? (ማቴ. 12:16) [w87 5/15 ገጽ 9፤ cl ገጽ 93-94]
15. ኢየሱስ ‘በምንሰፍርበት መስፈሪያ እንደሚሰፈርልን’ የተናገረው ሐሳብ ምን ትርጉም አለው? (ማር. 4:24, 25) [w80 6/15 ገጽ 12፤ gt ምዕ. 43]