ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች የካቲት:- ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው?፤ መጋቢት:- ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?፤ ሚያዝያና ግንቦት:- መጽሔቶች።
◼ የመጋቢት ወር አምስት ቅዳሜና እሁዶች ስላሉት ረዳት አቅኚ ሆኖ ለማገልገል አመቺ ነው።
◼ ጸሐፊውና የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሁሉንም የዘወትር አቅኚዎች የአገልግሎት እንቅስቃሴ መመርመር ይኖርባቸዋል። የሰዓት ግባቸው ላይ መድረስ ያልቻሉ አቅኚዎች ካሉ ሽማግሌዎቹ እርዳታ መስጠት የሚቻልበትን መንገድ መቀየስ ይኖርባቸዋል።