የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 2/08 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
  • ንዑስ ርዕሶች
  • የካቲት 11 የሚጀምር ሳምንት
  • የካቲት 18 የሚጀምር ሳምንት
  • የካቲት 25 የሚጀምር ሳምንት
  • መጋቢት 3 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
km 2/08 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

የካቲት 11 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 74 (168)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በገጽ 8 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የጥር 1 መጠበቂያ ግንብ እና የጥር 2008 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።

15 ደቂቃ:- የመንግሥቱ ሰባኪዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉበት አካባቢ ተዛውረህ ማገልገል ትችል ይሆን? በሐምሌ 15, 2003 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 20 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። የተደራጀ ሕዝብ ከተባለው መጽሐፍ ገጽ 111 አንቀጽ 1 እስከ ገጽ 112 አንቀጽ 1 ላይ አንዳንድ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ። ይህን ሁኔታ በአገራችን በአሁኑ ጊዜ በመካሄድ ላይ ካለው ዘመቻ ጋር አያይዘህ አንዳንድ ሐሳቦችን ጥቀስ። የመንግሥቱ ሰባኪዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉበት አካባቢ ሄዶ ላገለገለ አስፋፊ አጭር ቃለ ምልልስ አድርግ። ምን አስቸጋሪ ሁኔታዎች አጋጥመውታል? እነዚህን ማሸነፍ የቻለውስ እንዴት ነው? ምን በረከቶችን አገኘ?

20 ደቂቃ:- አዳዲስ ክርስቲያኖች እድገት እንዲያደርጉ እርዱ። አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በታኅሣሥ 1, 2005 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 31 ላይ የሚገኙትን ለአንቀጾቹ የተዘጋጁትን ጥያቄዎች በመጠቀም በጥያቄና መልስ ተወያዩበት። አንቀጽ 18ን ከተወያያችሁ በኋላ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ተሞክሮ ካለው አስፋፊ ጋር የሚያገለግል አንድ አዲስ አስፋፊ ከቤቱ ባለቤት የተቃውሞ ሐሳብ ይሰነዘርበታል። አዲሱ አስፋፊ የሰጠው ምላሽ ጥሩ ስላልነበር የቤቱ ባለቤት ውይይቱን ለመቀጠል ፈቃደኛ ሳይሆን ይቀራል። ከሰውየው ቤት ከሄዱ በኋላ ተሞክሮ ያካበተው አስፋፊ፣ አዲሱ አስፋፊ ላደረገው ጥረት ከልብ ያመሰግነዋል፤ ከዚያም ሌላ ጊዜ ውይይቱን የሚያስቆም ሰው ሲያጋጥመው ማመራመር መጽሐፍን ተጠቅሞ እንዴት መልስ መስጠት እንደሚችል ያሳየዋል። በተጨማሪም ጥሩ ማስታወሻ እንዴት መያዝ እንደሚችል ይነግረዋል።

መዝሙር 24 (50)

የካቲት 18 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 76 (172)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።

10 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

25 ደቂቃ:- “ጠንካራ እምነት እንዳለን የሚያሳይ ማስረጃ!”* በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ። ባለፈው የአገልግሎት ዓመት ውስጥ ጉባኤው ያከናወነውን አበረታች እንቅስቃሴ በመከለስ ክፍሉን ደምድም።

መዝሙር 23 (48)

የካቲት 25 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 36 (81)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የየካቲት ወር የአገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ። የመታሰቢያውን በዓል የመጋበዣ ወረቀት በመጠቀም አንድን የቤተሰብ አባል ወይም ጎረቤት እንዴት መጋበዝ እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።

20 ደቂቃ:- “ቤዛውን በአድናቆት ማሰብ”* ጊዜ በፈቀደልህ መጠን አድማጮች ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ በተጠቀሱ ጥቅሶች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ።

15 ደቂቃ:- ወቅታዊ መጽሔቶችን ለማበርከት ዝግጅት አድርጉ። ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። የጥር 1 መጠበቂያ ግንብ እና የጥር 2008 ንቁ! መጽሔቶችን ይዘት በአጭሩ ከተናገርክ በኋላ በክልላችሁ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ይበልጥ የሚማርከው የትኛው ርዕስ እንደሆነና ለምን እንዲህ እንዳሉ አድማጮችን ጠይቅ። አድማጮች በአገልግሎት ላይ ሊያስተዋውቁት ካሰቡት ርዕስ ውስጥ ማራኪ ሆነው ያገኟቸውን አንዳንድ ነጥቦች እንዲናገሩ ጋብዝ። ውይይት ለመጀመር ምን ጥያቄ መጠቀም ይቻላል? ከዚያስ በርዕሱ ውስጥ ያለ የትኛው ጥቅስ ቢነበብ ጥሩ ነው? በገጽ 8 ላይ የሚገኙትን መግቢያዎች ወይም አድማጮች የሰጧቸውን ሐሳቦች በመጠቀም የጥር 1 መጠበቂያ ግንብ እና የጥር 2008 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።

መዝሙር 59 (139)

መጋቢት 3 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 57 (136)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። “የመታሰቢያውን በዓል የሚመለከቱ ማሳሰቢያዎች” ከሚለው ሣጥን ውስጥ ዋና ዋና ነጥቦችን አቅርብ።

20 ደቂቃ:- በመጋቢት ወር ጥናት ማስጀመር ትችላላችሁ? ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። በመጋቢት ወር ጥናት የማስጀመር ግብ ይዘን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ እናበረክታለን። የመጽሐፉን አንዳንድ ጎላ ያሉ ገጽታዎች ጥቀስ። የመታሰቢያውን በዓል የመጋበዣ ወረቀት ስንሰጠው ፍላጎት ላሳየ ሰው ወይም መጽሔት ላበረከትንለት ሰው ተመላልሶ መጠየቅ ስናደርግ አሊያም ከመጋቢት 22 በኋላ ከቤት ወደ ቤት ስናገለግል መጽሐፉን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል ተወያዩ። ጥሩ ማስታወሻ የመያዝን አስፈላጊነት ግለጽ። (የመንግሥት አገልግሎታችን 8/07 ገጽ 6፤ የመንግሥት አገልግሎታችን 3/06 ገጽ 1, አን. 3፤ የመንግሥት አገልግሎታችን 1/06 ገጽ 3-6ን ተመልከት።) አንድ ወይም ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።

15 ደቂቃ:- ለጥያቄዎች መልስ ስትሰጡ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጠቀሙ። በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 143-144 ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። አንድ አስፋፊ በክልሉ ውስጥ በተደጋጋሚ ለሚነሳ አንድ ጥያቄ መልስ ለመስጠት መጽሐፍ ቅዱስን ሲጠቀም የሚያሳይ አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።

መዝሙር 54 (132)

[የግርጌ ማስታወሻዎች ]

አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ