ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች:- ሚያዝያና ግንቦት:- መጽሔቶች፤ ሰኔ:- ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? ሐምሌ:- ብሮሹሮች።
◼ የጉባኤ ጸሐፊዎች የዘወትር አቅኚነት አገልግሎት ማመልከቻ ቅጽ (S-205) እና የረዳት አቅኚነት አገልግሎት ማመልከቻ ቅጽ (S-205b) በበቂ መጠን ሊኖራቸው ይገባል። እነዚህ ቅጾች እንዲላኩላችሁ በጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ (S-14) መጠየቅ ይቻላል። ቢያንስ ለአንድ ዓመት የሚበቁ ቅጾች ይኑሯችሁ። የዘወትር አቅኚነት ማመልከቻ ቅጾችን ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው ከመላካችሁ በፊት በደንብ መሞላታቸውን ማረጋገጥ አለባችሁ።
◼ ቅርንጫፍ ቢሮው የሁሉንም ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቾችና ጸሐፊዎች ወቅታዊ አድራሻና ስልክ ቁጥር ማግኘት ይፈልጋል። የአድራሻ ለውጥ በሚኖርበት ጊዜ የጉባኤው የአገልግሎት ኮሚቴ፣ የሰብሳቢ የበላይ ተመልካች/የጸሐፊ የአድራሻ ለውጥ ማሳወቂያ ቅጽ (S-29) ሞልቶና ፈርሞ በፍጥነት ለቅርንጫፍ ቢሮው መላክ አለበት። የስልክ ቁጥር ለውጥ ሲኖርም እንደዚህ መደረግ ይኖርበታል።
◼ በማንኛውም ጊዜ ወደ ሌላ አገር ለመጓዝ ስታስቡ እዚያ በሚደረጉ የጉባኤ፣ የልዩና የወረዳ ወይም የአውራጃ ስብሰባዎች ላይ የመገኘት እቅድ ካላችሁ ስብሰባዎቹ የሚደረጉበትን ቀን፣ ሰዓት እና ቦታ ለማወቅ ጥያቄያችሁን የምትልኩት የዚያን አገር ሥራ በበላይነት ለሚከታተለው ቅርንጫፍ ቢሮ መሆን ይኖርበታል። የቅርንጫፍ ቢሮዎችን አድራሻ በቅርቡ ከወጣው የዓመት መጽሐፍ መጨረሻ ገጽ ላይ ማግኘት ይቻላል።
◼ አዲስ የደረሱን ጽሑፎች:- እንግሊዝኛ:- የ2007 የመጠበቂያ ግንብና የንቁ! መጽሔቶች ጥራዝ፤ ኦሮምኛ:- የቤተሰብ ደስታ፤ ወላይትኛ:- ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት።
◼ በድጋሚ የደረሱን ጽሑፎች:- አማርኛ:- አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባል?፣ የወጣቶች ጥያቄ፤ እንግሊዝኛ:- የይሖዋ ምሥክሮችና ትምህርት፣ ጋይዳንስ፣ ሰብሚሽን፣ ራእይ ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!፣ የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ጽሑፎች ማውጫ 1986-2000፣ ኖኅ እና ዳዊት በዲቪዲ፤ ፈረንሳይኛ:- ነቅተህ ጠብቅ!