የቲኦክራሲያዊ አገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ሚያዝያ 28, 2008 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከመጋቢት 3 እስከ ሚያዝያ 28, 2008 ድረስ ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል።
የንግግር ባሕርይ
1. ንግግራችንን በተመደበልን ጽሑፍ ላይ ተመርኩዘን ማዳበራችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? እንዲህ ማድረግ የምንችለውስ እንዴት ነው? [be ገጽ 234 አን. 1 እስከ ገጽ 235 አን. 1]
2. በምናስተምርበት ወቅት በጥያቄዎች መጠቀማችን በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? [be ገጽ 236 አን. 1-5]
3. ጥያቄዎችን መጠቀም አድማጮቻችን ስለ አንድ ጉዳይ እንዲያመዛዝኑ የሚረዳቸው እንዴት ነው? [be ገጽ 237 አን. 3 እስከ ገጽ 238 አን. 1]
4. በምናስተምርበት ወቅት ጥያቄዎችን በጥሩ ሁኔታ መጠቀማችን ሰዎች ስሜታቸውን እንዲገልጹ ያበረታታቸዋል የምንለው ለምንድን ነው? (ምሳሌ 20:5፤ ማቴ. 16:13-16፤ ዮሐ. 11:26) [be ገጽ 238 አን. 3-5]
5. በምናስተምርበት ጊዜ በተነጻጻሪ ዘይቤ መጠቀማችን ምን ጥቅም አለው? (ዘፍ. 22:17፤ ኤር. 13:11) [be ገጽ 240 አን. 1-3]
ክፍል ቁ. 1
6. በማርቆስ መጽሐፍ ውስጥ ጎላ ተደርገው የተገለጹ በአምላክ መንግሥት ውስጥ ሕይወት እንድናገኝ የሚረዱን አንዳንድ መሠረታዊ ሥርዓቶች የትኞቹ ናቸው? [bsi08-1 ገጽ 8 አን. 32]
7. መንፈስ ቅዱስ በዛሬው ጊዜ የሚገኙ የአምላክ አገልጋዮችን የሚረዳቸው እንዴት ነው? (ዮሐ. 14:25, 26) [be ገጽ 19 አን. 1-2]
8. ማንበብ የሚያስገኘው ከሁሉ የላቀ ጥቅም ምንድን ነው? [be ገጽ 21 አን. 3]
V9. ጥናት ምንን ይጨምራል? [be ገጽ 27 አን. 3 እስከ ገጽ 28 አን. 1]
10. የሉቃስ ወንጌል በመንፈስ አነሳሽነት በተጻፉት የዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ላይ ያለን እምነት ይበልጥ እንዲጠናከር የሚያደርገው እንዴት ነው? [bsi08-1 ገጽ 10 አን. 30-31]
ሳምንታዊው የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. ኢየሱስ “ቸር [“ጥሩ፣” NW] መምህር” በማለት የጠራውን ሰው ያረመው ለምንድን ነው? (ማር. 10:17, 18) [w08 2/15 “የይሖዋ ቃል ሕያው ነው—የማርቆስ መጽሐፍ ጎላ ያሉ ነጥቦች”]
12. ኢየሱስ ከእስራኤል ብሔር ጋር በተያያዘ የበለስን ዛፍ ምሳሌ አድርጎ የተጠቀመው ምን ለማስተማር ነው? (ማር. 11:12-14, 20, 21) [w03 5/15 ገጽ 26 አን. 2-3]
13. መልአኩ ገብርኤል፣ ማርያም መንፈስ ቅዱስ ወደ እሷ ሲመጣና የአምላክ ኃይል ሲጸልልባት ‘እንደምትፀንስ’ ነግሯታል። መልአኩ ገብርኤል ይህን ሲል ምን ማለቱ ነበር? (ሉቃስ 1:30, 31, 34, 35) [w08 3/15 “የይሖዋ ቃል ሕያው ነው—የሉቃስ መጽሐፍ ጎላ ያሉ ነጥቦች”፤ it-2 ገጽ 56 አን. 2]
14. የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት “በሰንበት ቀን ሊደረግ ያልተፈቀደውን” ነገር በእርግጥ አድርገዋል? (ሉቃስ 6:1, 2) [gt 31]
15. ኢየሱስ ለማርታ ከሰጣት ምክር ምን ትምህርት እናገኛለን? (ሉቃስ 10:40-42) [w99 9/1 ገጽ 31]