ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች:- ግንቦት:- መጽሔቶች፤ ሰኔ:- ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? ሐምሌ እና ነሐሴ:- ብሮሹሮች።
◼ የሽማግሌዎች አካላት አደጋ ከመከሰቱ በፊት ሊደረግ ስለሚገባው ቅድመ ዝግጅት የሚናገረውን የሐምሌ 6, 2006 ደብዳቤ እንደገና በማንበብ የእያንዳንዱ አስፋፊ ወቅታዊ መረጃ ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል። ለአደጋ በተጋለጡ አካባቢዎች ያሉ ጉባኤዎች ድንገተኛ ሁኔታ ሲያጋጥም ወንድሞችን ቶሎ ለማግኘት የሚረዱ ተጨማሪ መረጃዎችን ማሰባሰብ አለባቸው። እርግጥ ነው፣ አስፋፊዎች አደጋ በሚከሰትበት ጊዜ ብቻ ሳይሆን ለእረፍት፣ ለሥራ፣ ለሕክምናና ለመሳሰሉት ጉዳዮች ረዘም ላሉ ጊዜያት ከአካባቢያቸው ርቀው ሲሄዱ ሁኔታውን ለመጽሐፍ ጥናት የበላይ ተመልካቻቸው ወይም ለሌላ ሽማግሌ ማሳወቃቸው ጠቃሚ ነው።
◼ አዲስ የደረሱን ጽሑፎች:- እንግሊዝኛ:- የ2008 የዓመት መጽሐፍ፣ የ2007 ዎችታወር ላይብረሪ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ድራማዎች በmp3፤ ፈረንሳይኛ:- የ2008 የዓመት መጽሐፍ፣ የ2007 ዎችታወር ላይብረሪ።
◼ በድጋሚ የደረሱን ጽሑፎች:- አማርኛ:- ነቅተህ ጠብቅ!፣ ትራክቶች ቁ. 13, 14, 26, 27፤ እንግሊዝኛ:- የአዲስ ዓለም ትርጉም (bi-12)፤ ፈረንሳይኛ:- ክርኤሽን፣ ማመራመር፤ ኦሮምኛ:- ነቅተህ ጠብቅ!፣ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?፣ ትራክቶች ቁ. 26 እና 27፤ ስፓንኛ:- የአዲስ ዓለም ትርጉም (bi-12)፤ ትግርኛ:- ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ፣ አምላክ ስለ እኛ በእርግጥ ያስባል?፣ የወጣቶች ጥያቄ።