የቲኦክራሲያዊ አገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ሰኔ 30, 2008 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከግንቦት 5 እስከ ሰኔ 30, 2008 ድረስ ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል። [ማሳሰቢያ:- ከጥያቄው ቀጥሎ መልሱ የሚገኝበት ጽሑፍ ካልተጠቀሰ መልሱን ለማግኘት በግልህ ምርምር ማድረግ ይኖርብሃል።—የአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 36-37ን ተመልከት።]
የንግግር ባሕርይ
1. አድማጮች የምንነግራቸውን ምሳሌ እንዲረዱት ምን ማድረግ እንችላለን? [be ገጽ 242 አን. 3 እስከ ገጽ 243 አን. 1]
2. የተለመዱ ነገሮችን ምሳሌ አድርጎ መጠቀም ውጤታማ የሆነው ለምንድን ነው? [be ገጽ 245 አን. 2-4]
3. በሚታዩ ነገሮች አስደግፎ ማስተማር ምን ያህል አስፈላጊ ነው? ይሖዋስ በሚታዩ ነገሮች ተጠቅሞ አስፈላጊ ትምህርቶችን የሰጠው እንዴት ነው? (ዘፍ. 15:5፤ ኤር. 18:6፤ ዮናስ 4:10, 11) [be ገጽ 247 አን. 1-2]
4. የማስተማር ችሎታችንን ለማሻሻል በሚታዩ ነገሮች መጠቀም የምንችለው እንዴት ነው? [be ገጽ 248 አን. 1-3]
5. የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎችን ስናስተምር ካርታዎችን ውጤታማ በሆነ መንገድ መጠቀም የምንችለው እንዴት ነው? [be ገጽ 248 አን. 4]
ክፍል ቁ. 1
6. በአምላክ ቅዱስ መንፈስ በመታገዝ መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናታችን ምን ነገር እንድናስተውል ይረዳናል? [be ገጽ 32 አን. 3-4]
7. የአንድን ጥቅስ ትርጉም ለመረዳት ራሱን መጽሐፍ ቅዱስን መጠቀም የምንችለው እንዴት ነው? [be ገጽ 34 አን. 4 እስከ ገጽ 35 አን. 2]
8. ኢየሱስ መላው የሰው ዘር የይሖዋን በረከት የሚያገኝበት መሥመር በመሆን የሚጫወተው ሚና በዮሐንስ ወንጌል ውስጥ ጎላ ተደርጎ የተገለጸው እንዴት ነው? [bsi08-1 ገጽ 13 አን. 32]
9. የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍን የጻፈው ሐኪሙ ሉቃስ ነው እንድንል የሚያስችለን ቅዱስ ጽሑፋዊ ምክንያት ምንድን ነው? [bsi08-1 ገጽ 14 አን. 3, 5 እስከ ገጽ 15 አን. 7]
10. የንግግር አስተዋጽኦ ስታዘጋጅ አብዛኛውን ጊዜ ምን ማድረግ ይኖርብሃል? [be ከገጽ 39 እስከ 41]
ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. ‘ለመሥራት አርባ ስድስት ዓመት የፈጀው’ ቤተ መቅደስ የትኛው ነው? (ዮሐ. 2:20) [w08 4/15 “የይሖዋ ቃል ሕያው ነው—የዮሐንስ መጽሐፍ ጎላ ያሉ ነጥቦች”]
12. ‘ከሞት ወደ ሕይወት የተሻገሩት’ እነማን ናቸው? (ዮሐ. 5:24, 25) [w08 4/15 “የይሖዋ ቃል ሕያው ነው—የዮሐንስ መጽሐፍ ጎላ ያሉ ነጥቦች”]
13. ኢየሱስ ለታማኝ ተከታዮቹ ‘ስፍራ የሚያዘጋጅላቸው’ እንዴት ነው? (ዮሐ. 14:2) [w08 4/15 “የይሖዋ ቃል ሕያው ነው—የዮሐንስ መጽሐፍ ጎላ ያሉ ነጥቦች”]
14. ኢየሱስ መግደላዊት ማርያምን አትንኪኝ ያላት ለምን ነበር? (ዮሐ. 20:17) [w08 4/15 “የይሖዋ ቃል ሕያው ነው—የዮሐንስ መጽሐፍ ጎላ ያሉ ነጥቦች”]
15. ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲያርግ በነበረው ‘በዚያው ሁኔታ’ ተመልሶ ይመጣል ሲባል ምን ማለት ነው? (ሥራ 1:9-11) [rs ገጽ 342 አን. 4፤ it-1 ገጽ 186 አን. 8]