ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች:- ሰኔ:- ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?፤ ሐምሌ እና ነሐሴ:- ብሮሹሮች፤ መስከረም:- ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
◼ የነሐሴ ወር አምስት ቅዳሜና እሁዶች ስላሉት ረዳት አቅኚ ሆኖ ለማገልገል አመቺ ነው።
◼ እንግሊዝኛ ወይም ሌላ የውጭ አገር ቋንቋ የሚናገሩ ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን ተከታትሎ መርዳት እንዲቻል በአዲስ አበባ ለሚገኙ ጉባኤዎች አነስተኛ መጠን ያለው S-43 ቅጽ ይላክላቸዋል። አስፋፊዎች፣ እንግሊዝኛ ወይም ሌላ የውጭ አገር ቋንቋ ተናጋሪ የሆነ የይሖዋ ምሥክር ተመልሶ እንዲጠይቃቸው ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎችን ካገኙ ይህንን ቅጽ መሙላት እንዳለባቸው ለማስታወስ እንወዳለን። ለእነዚህ ሰዎች ተገቢውን ክትትል ማድረግ እንዲቻል የጉባኤው ጸሐፊ የተሞሉትን ፎርሞች ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው ይልካቸዋል። ተጨማሪ S-43 ቅጾች ካስፈለጓችሁ በጽሑፍ ማዘዣ ቅጽ (S-14) ማዘዝ ትችላላችሁ።
◼ በአማርኛ ቋንቋ የሚካሄዱ የጉባኤ መጽሐፍ ጥናት ቡድኖች መስከረም 8 እስከሚጀምረው ሳምንት ድረስ ራእይ ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል! የተባለውን መጽሐፍ ማጥናታቸውን ይቀጥላሉ። መስከረም 15 ከሚጀምረው ሳምንት አንስቶ በጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት ላይ የሚጠናው ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለው መጽሐፍ ይሆናል።
◼ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ የመረጠው አንድ ወንድም የመጋቢትን፣ የሚያዝያንና የግንቦትን የጉባኤ ሒሳብ መመርመር ይኖርበታል። የሒሳብ ምርመራው ውጤት የሚቀጥለው የሒሳብ ሪፖርት ከቀረበ በኋላ ለጉባኤው መነበብ አለበት።—ለጉባኤ ሒሳብ አያያዝ የወጣ መመሪያ (S-27) የሚለውን ተመልከት።
◼ ለዘወትር አቅኚነት የሚቀርብ ማመልከቻ፣ አስፋፊው አቅኚነት መጀመር ከሚፈልግበት ቀን ቢያንስ ከ30 ቀናት በፊት ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው መላኩ አስፈላጊ ነው። የጉባኤው ጸሐፊ የማመልከቻ ቅጾቹ በሚገባ መሞላታቸውን ማረጋገጥ ይኖርበታል። አመልካቾች የተጠመቁበትን ትክክለኛ ቀን ማስታወስ ካልቻሉ ቀኑን ገምተው ለማወቅ መጣርና ይህን ቀን መዝግበው መያዝ ይኖርባቸዋል። የጉባኤው ጸሐፊ ይህን ቀን የጉባኤ አስፋፊ ካርድ (S-21) ላይ ሊመዘግበው ይገባል።
◼ ከጥር 2008 ጀምሮ በእንግሊዝኛና በስፓንኛ ቋንቋ በድምፅ የተዘጋጁ የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔቶች www.pr2711.com በሚለው ድረ ገጽ ላይ መውጣት ጀምረዋል። በርካታ ወንድሞች በሲዲና በMP3 የተዘጋጁት የእነዚህ ጽሑፎች ቅጂ ወደ ጉባኤያቸው ከመድረሱ በፊት ጽሑፎቹን ከዚህ ድረ ገጽ ላይ መውሰድ ወይም ዳውንሎድ ማድረግ ይፈልጋሉ። አንድ ሰው እነዚህን ጽሑፎች ከኢንተርኔት ላይ ዳውንሎድ ሲያደርግ ድርጅቱ ተጨማሪ ገንዘብ ይከፍላል። ያም ሆኖ፣ ይህ ወጪ ሲዲዎችን ለማምረትና ወደ ተለያዩ አካባቢዎች ለመላክ ከሚወጣው ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ ነው። በመሆኑም ከድረ ገጹ ላይ መጽሔቶችን ዳውንሎድ የሚያደርጉ አስፋፊዎች የሲዲና የMP3 ትእዛዛቸውን እንዲሰርዙ እናበረታታቸዋለን። ወደፊት በሌሎች ቋንቋዎች በድምፅ የተዘጋጁ ጽሑፎች www.pr2711.com በሚለው ድረ ገጽ ላይ ይወጣሉ።