ቤተሰብህ ለመዳን እየተዘጋጀ ነው?
1 ፍጻሜያቸውን ያገኙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች የዚህ ክፉ ዓለም መጨረሻ በፍጥነት እየቀረበ እንዳለ አሳማኝ ማስረጃ ይሰጡናል። የምንኖረው የጥፋት ውኃ ከመምጣቱ በፊት ከነበረው ሁኔታ ጋር በሚመሳሰል ወሳኝ ጊዜ ውስጥ ነው። (ማቴ. 24:37-39) ኖኅ ‘አካሄዱን ከአምላክ ጋር በማድረጉ’ በዚያን ወቅት የነበረው ዓለም ሲጠፋ በሕይወት ተርፏል። (ዘፍ. 6:9) በሕይወት የተረፉት ቤተሰቡም ጭምር በመሆናቸው ኖኅ ስለ ይሖዋ መንገዶች አስተምሯቸው መሆን አለበት። እኛስ ከዚህ ክፉ ሥርዓት ፍጻሜ በሕይወት ለመትረፍ በቤተሰብ ደረጃ ዝግጅት ማድረግና ኖኅን መምሰል የምንችለው እንዴት ነው?
2 የጽድቅ ሰባኪ:- ኖኅ “የጽድቅ ሰባኪ” በመሆን ከ40 እስከ 50 ለሚሆኑ ዓመታት በጽናት አገልግሏል። (2 ጴጥ. 2:5) በአካባቢው ይኖሩ የነበሩ ሰዎች፣ ሥጋ የለበሱ ዓመጸኛ መላእክት ተጽዕኖ አሳድረውባቸው ይሁን አይሁን ኖኅ በሚሰብክበት ጊዜ አፊዘውበት መሆን አለበት። እኛም በአገልግሎታችን ላይ ብዙ ጊዜ ግድ የለሽና ፌዘኛ የሆኑ ሰዎች የሚያጋጥሙን ሲሆን ይህም የዚህ ሥርዓት መጥፊያ እንደቀረበ ያረጋግጣል። (2 ጴጥ. 3:3, 4) ይሁን እንጂ ከኖኅ ዘመን በተለየ መልኩ ብዙ ሰዎች ለምናደርገው ጥረት ምላሽ እየሰጡና ወደ ይሖዋ አምልኮ እየጎረፉ ነው። (ኢሳ. 2:2) ‘ራሳችንንም ሆነ የሚሰሙንን ልናድን’ የምንችለው በስብከቱ ሥራ ከጸናን ብቻ ነው። (1 ጢሞ. 4:16) ወላጆች፣ የስብከቱ ሥራ አጣዳፊ መሆኑን በቃልም ይሁን በተግባር ለልጆቻቸው ማስተማራቸው ምንኛ አስፈላጊ ነው!—2 ጢሞ. 4:2
3 ‘እንደታዘዘው’ አደረገ:- የኖኅና የቤተሰቡ መዳን የተመካው የይሖዋን ትእዛዝ በጥንቃቄ በመከተላቸው ላይ ነበር። (ዘፍ. 6:22) በዛሬው ጊዜም፣ መጽሐፍ ቅዱስና ታማኙ ባሪያ የሚሰጡንን መመሪያዎች “ለመታዘዝ ዝግጁ” መሆናችን አስፈላጊ ነው። (ያዕ. 3:17 NW) የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ትልልቅ ልጆች፣ አባታቸው ከይሖዋ ድርጅት የሚያገኛቸውን ሐሳቦች እንዴት ተግባራዊ ያደርግ እንደነበር አሁንም ድረስ እንደሚያስታውሱ ተናግረዋል። ለምሳሌ ይህ አባት ሁላችንም እንደምንበረታታው፣ በየሳምንቱ የቤተሰብ ጥናት ይመራ የነበረ ሲሆን በሳምንቱ መጨረሻ ላይም ቤተሰቡን አገልግሎት ይዞ ይወጣል። በየሳምንቱ ተራ በተራ ከሁሉም ልጆቹ ጋር ለማገልገል ጥረት ያደርግ ነበር። ይህ አባት ‘እንደታዘዘው’ ለማድረግ ያሳየው ቆራጥነት የልጆቹን ልብ የነካ ሲሆን ስድስቱም የይሖዋ ታማኝ አገልጋዮች ሆነዋል።
4 የዚህ ሥርዓት መጨረሻ በድንገት ይመጣል። (ሉቃስ 12:40) የኖኅን ምሳሌ የምንኮርጅና ለመዳን የሚያበቃንን እምነት ከወዲሁ የምናዳብር ከሆነ እኛም ሆን ቤተሰባችን ለዚህ ቀን ዝግጁ እንደምንሆን ምንም ጥርጥር የለውም!—ዕብ. 11:7