የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
ሐምሌ 14 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 59 (139)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በገጽ 4 ላይ የሚገኙትን ሐሳቦች ወይም ለጉባኤያችሁ ክልል ተስማሚ የሆኑ ሌሎች አቀራረቦችን በመጠቀም የሰኔ 1 መጠበቂያ ግንብ እና የሰኔ 2008 ንቁ! መጽሔቶች ሲበረከቱ የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
15 ደቂቃ:- ‘በድፍረት’ የመናገር ችሎታ አለህ? በግንቦት 15, 2006 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 13-16 ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። በድፍረት የመስበክን አስፈላጊነት ጎላ አድርገህ ግለጽ።
20 ደቂቃ:- “የ2008 የይሖዋ ምሥክሮች የአውራጃ ስብሰባ።”* አንቀጽ 2 ላይ ስትደርስ ጉባኤው የተመደበበትን የአውራጃ ስብሰባ ፕሮግራም ተናገር።
መዝሙር 20 (45)
ሐምሌ 21 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 65 (152)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። አድማጮች በሚቀጥለው ሳምንት በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ለምንወስደው ክፍል የሰኔ 1 መጠበቂያ ግንብ እና የሰኔ 2008 ንቁ! መጽሔቶችን ይዘው እንዲመጡ አስታውሳቸው። እንዲሁም ክፍሉ ሲቀርብ ተሳትፎ ማድረግ እንዲችሉ ለክልላችሁ የሚስማሙ የመግቢያ ሐሳቦችን እንዲዘጋጁ ንገራቸው።
15 ደቂቃ:- “ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ በማጥናት ደስታ ማግኘት” * የዚህን ጽሑፍ ለየት ያሉ ገጽታዎች ጥቀስ። በዚህ የመንግሥት አገልግሎታችን እትም ገጽ 3 ላይ የሚገኘውን የጥናት ፕሮግራም ባጭሩ ከልስ። ሁሉም በስብሰባው ላይ አዘውትረው እንዲገኙና ጥሩ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አበረታታቸው። ለስብሰባዎች ጥሩ ዝግጅት በማድረግ ለሚታወቁ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች አጭር ቃለ ምልልስ አድርግ። እንዲህ እንዲያደርጉ የሚገፋፋቸው ምን እንደሆነ ጠይቃቸው።
20 ደቂቃ:- “ውጤታማ የሆነ ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግ ቁልፉ ዝግጅት ነው”* አንቀጽ 2ን ከተወያያችሁ በኋላ ፍላጎት ያሳየ ሰው ስናገኝ ጥሩ ማስታወሻ መያዛችን አስፈላጊ መሆኑን ጎላ አድርገህ ግለጽ። ሁኔታው ማስታወሻ ለመያዝ የማያመች ከሆነ የሌሎችን ትኩረት እምብዛም ወደማንስብበት አካባቢ ዞር ማለቱ አስፈላጊ እንደሆነ መጥቀስ ትችላለህ። አንድ አስፋፊ ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግ ሲዘጋጅ የሚያሳይ ለአራት ደቂቃ ያህል መነባንብ እንዲቀርብ አድርግ። አስፋፊው ማስታወሻውን ከተመለከተ በኋላ ቅዳሜና እሁድ ለሁለት ግለሰቦች ተመላልሶ መጠየቅ ማድረግ እንዳለበት ይወስናል። ከዚያም ከእነዚህ ሁለት ግለሰቦች ጋር ከዚህ በፊት የተነጋገሩት በምን ጉዳይ ላይ እንደነበር ያስባል፤ እንዲሁም ተመላልሶ መጠየቅ በሚያደርግበት ወቅት ግቡ ምን መሆን እንዳለበት ከወሰነ በኋላ ይህንን ግቡን እንዴት ማሳካት እንደሚችል ይዘጋጃል። ለአንደኛው ግለሰብ፣ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲያጠና እንዴት ግብዣ እንደሚያቀርብለት ይዘጋጃል። ለሌላኛው ደግሞ፣ በአንቀጽ 5 ላይ የቀረበውን ሐሳብ በመጠቀም ፍላጎቱን እንዴት ማሳደግ እንደሚችል ይዘጋጃል።
መዝሙር 70 (162)
ሐምሌ 28 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 3 (6)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የሐምሌ ወር የአገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ። በነሐሴ ወር የሚበረከተውን ጽሑፍ ከተናገርክ በኋላ ጽሑፉን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ አንድ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
15 ደቂቃ:- ምንጊዜም የጥድፊያ ስሜታችንን ጠብቀን መኖር። በታኅሣሥ 15, 2006 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 18-19 በአንቀጽ 17-21 ላይ ተመሥርቶ በግለት የሚቀርብ ንግግር።
20 ደቂቃ:- ወቅታዊ መጽሔቶችን ለማበርከት ዝግጅት አድርጉ። ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። የሰኔ 1 መጠበቂያ ግንብ እና የሰኔ 2008 ንቁ! መጽሔቶችን ይዘት በአጭሩ ከተናገርክ በኋላ በክልላችሁ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ይበልጥ የሚማርከው የትኛው ርዕስ እንደሆነና ለምን እንዲህ እንዳሉ አድማጮችን ጠይቅ። አድማጮች በአገልግሎት ላይ ሊያስተዋውቁት ባሰቡት ርዕስ ውስጥ ማራኪ ሆነው ያገኟቸውን አንዳንድ ነጥቦች እንዲናገሩ ጋብዝ። ውይይት ለመጀመር ምን ጥያቄ መጠቀም ይቻላል? በርዕሱ ውስጥ ያለ የትኛው ጥቅስ ቢነበብ ጥሩ ነው? በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የሚገኙትን የናሙና አቀራረቦች ወይም አድማጮች የሰጧቸውን ሐሳቦች በመጠቀም እያንዳንዱን መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
መዝሙር 45 (106)
ነሐሴ 4 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 100 (222)
10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ:- ልጆቻችሁ በትምህርት ቤት የሚያጋጥሟቸውን ፈተናዎች ለመቋቋም ተዘጋጅተዋል? በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ወጣት ክርስቲያኖች በትምህርት ቤት የሚገጥሟቸው አንዳንድ ተፈታታኝ ሁኔታዎች ምን እንደሆኑ ተናገር። ወላጆችና ልጆቻቸው የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ጽሑፎች ማውጫ (እንግሊዝኛ) ተጠቅመው እንዴት አንዳንድ ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን ማግኘት እንደሚችሉ አብራራ። አንዳንድ ምሳሌዎችን ስጥ። (“Schools” በሚለው ዋና ርዕስ ሥር የሚገኘውን “experiences” የሚለውን ንዑስ ርዕስ ተመልከት።) ከአድማጮች መካከል በክርስቲያን ቤተሰብ ውስጥ ያደጉ ወጣቶች፣ የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ተቋቁመው በትምህርት ቤት ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓት በሥራ ላይ ማዋል እንዲችሉ ወላጆቻቸው ያሠለጠኗቸው እንዴት እንደሆነ እንዲናገሩ ጋብዝ። በንቁ! መጽሔት ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ርዕሶችን ተጠቅመው ለትምህርት ቤት የሚቀርብ ጽሑፍ ያዘጋጁ ካሉ ተሞክሯቸውን ሊናገሩ ይችላሉ። ትምህርት ቤታቸውን እንደ ልዩ የአገልግሎት ክልል አድርገው መቁጠራቸው ጥበቃ የሆነላቸው እንዴት እንደሆነ እንዲናገሩ ጋብዝ።
20 ደቂቃ:- “ምሽግን እያፈረስን ነው።”* ከአድማጮች መካከል፣ መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት ከመጀመራቸው በፊት ከፍ አድርገው ይመለከቷቸው የነበሩትን የሐሰት ትምህርቶች እንዲተዉ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪዎቻቸው እንዴት በትዕግሥት እንደረዷቸው እንዲናገሩ ጋብዝ።
መዝሙር 62 (146)
[የግርጌ ማስታወሻዎች ]
አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው።