መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ሐምሌ 1
“ሁላችንም ብንሆን የምንወደውን ሰው በሞት ስናጣ በሐዘን እንደቆሳለን። እንዲህ ያለ ሁኔታ ሲያጋጥመን መጽሐፍ ቅዱስ የሚረዳን ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም መዝሙር 55:22ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ሐዘንን ለመቋቋም ስለሚረዱ አንዳንድ ጠቃሚ ዘዴዎች ይናገራል።”
ንቁ! ሐምሌ 2008
“በትዳር ውስጥ የሚያጋጥመው ውጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ከመምጣቱ የተነሳ ብዙ ጋብቻዎች በፍቺ ያከትማሉ። በዚህ ጥቅስ ላይ የሚገኘውን ምክር መከተላችን ትዳርን የሠመረ ለማድረግ አስተዋጽኦ የሚኖረው ይመስልዎታል? [ምሳሌ 12:18ን አንብብ። ከዚያም መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት፣ ባለትዳሮች በመካከላቸው ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር የሚረዷቸውን ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች ያብራራል።”
መጠበቂያ ግንብ ሐምሌ 1
“ፍጽምና የሚጎድለን ሰዎች ሁሉን ቻይ ከሆነው አምላክ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት መመሥረት የምንችል ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም የሐዋርያት ሥራ 17:27ን አንብብ።] ይህ ርዕስ፣ አምላክ ወደ እሱ እንድንቀርብ እንደሚፈልግ እርግጠኞች መሆን የምንችለው ለምን እንደሆነ ያብራራል።” ገጽ 10 ላይ የሚገኘውን ርዕስ አስተዋውቀው።
ንቁ! ሐምሌ 2008
“በዛሬው ጊዜ የመዝናኛው ዓለም ለመናፍስታዊ ድርጊቶች የበለጠ ትኩረት እየሰጠ ነው። በመናፍስታዊ ድርጊት መካፈል ምንም ጉዳት እንደሌለው ይሰማዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም ዘዳግም 18:10-12ን አንብብ።] ይህ ርዕስ በመናፍስታዊ ድርጊቶች መካፈል የሚያስከትለውን አደጋ በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ይገልጻል።” ገጽ 10 ላይ የሚገኘውን ርዕስ አስተዋውቀው።