የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/08 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ነሐሴ 11 የሚጀምር ሳምንት
  • ነሐሴ 18 የሚጀምር ሳምንት
  • ነሐሴ 25 የሚጀምር ሳምንት
  • መስከረም 1 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
km 8/08 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

ነሐሴ 11 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 30 (63)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከወቅታዊ መጽሔቶች ውስጥ በክልላችሁ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን የሚማርከው የትኛው ርዕስ እንደሆነ ሐሳብ እንዲሰጡ አድማጮችን ጠይቅ። አድማጮች በአገልግሎት ላይ ሊያስተዋውቁት ባሰቡት ርዕስ ውስጥ ማራኪ ሆነው ያገኟቸውን አንዳንድ ነጥቦች እንዲናገሩ ጋብዝ። ውይይት ለመጀመር ምን ጥያቄ መጠቀም ይቻላል? በርዕሱ ውስጥ ያለ የትኛው ጥቅስ ቢነበብ ጥሩ ነው? አድማጮች የሰጧቸውን ሐሳቦች እንዴት በአገልግሎት ላይ መጠቀም እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።

15 ደቂቃ:- ትኩረታችሁ ሳይከፋፈል የአምላክን ፈቃድ አድርጉ። በመጋቢት 1, 1998 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 30 አንቀጽ 4 እና 5 ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። በተጨማሪም ካም ቢ ማይ ፎሎወር (እንግሊዝኛ) የተባለውን መጽሐፍ ገጽ 93-94 አንቀጽ 12-13 መመልከት ትችላለህ።

20 ደቂቃ:- “ሙሉ በሙሉ እየተጠቀምክበት ነው?”* በሚበረከተው የመጠበቂያ ግንብ እትም ውስጥ ከሚገኙት አዳዲስ ዓምዶች መካከል አንዱን በመጠቀም ተሞክሮ ላገኘ አንድ አስፋፊ ቃለ ምልልስ አድርግ። ተሞክሮውን በሠርቶ ማሳያ መልክ ማቅረብ ይቻላል። በተጨማሪም በአንቀጽ 2 መሠረት በነሐሴ 1 መጠበቂያ ግንብ ላይ የሚገኘውን “ከኢየሱስ ምን እንማራለን” የሚለውን ዓምድ በመጠቀም እንዴት ጥናት ማስጀመር እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።

መዝሙር 9 (26)

ነሐሴ 18 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 56 (135)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች። አድማጮች በሚቀጥለው ሳምንት በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ለምንወስደው ክፍል በቅርብ የደረሱንን የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔቶችን ይዘው እንዲመጡ አስታውሳቸው። እንዲሁም ክፍሉ ሲቀርብ ተሳትፎ ማድረግ እንዲችሉ ለክልላችሁ የሚስማሙ የመግቢያ ሐሳቦችን እንዲዘጋጁ ንገራቸው።

20 ደቂቃ:- አለባበሳችንና አጋጌጣችን ለይሖዋ ክብር ያመጣል። በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። ይሖዋ ቅዱስ አምላክ በመሆኑ ሕዝቦቹ አካላዊ ንጽሕናቸውን መጠበቃቸው ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው። (ዘፀ. 30:17-21፤ 40:30-32) በተለይ አገልግሎት ስንወጣ በአለባበሳችንና በአጋጌጣችን ለሌሎች ጥሩ ምሳሌ በመሆን ይሖዋን ማስደሰት የምንችል ከመሆኑም በላይ ክብር እናመጣለታለን። (1 ጴጥ. 2:12) በሌላ በኩል ግን እንዲህ አለማድረጋችን ‘የአምላክ ቃል እንዲሰደብ’ ሊያደርግ ይችላል። (ቲቶ 2:5) አንድ አስፋፊ ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን አለባበስ ያለው መሆኑ እንዴት ምሥክርነት ለመስጠት እንዳስቻለው የሚያሳይ ከጉባኤያችሁ አሊያም ከድርጅቱ ጽሑፎች ያገኘኸውን ተሞክሮ ተናገር።

15 ደቂቃ:- ከፍተኛ ምሥክርነት የሚሰጡ ወጣቶች። ወላጆችንና በቅርቡ ትምህርት የሚጀምሩ ልጆቻቸውን አስመልክቶ የሚቀርብ አበረታች ንግግር። ወጣቶች፣ ምሥክርነት ለመስጠት የሚያስችሉ አጋጣሚዎችን እንዲጠቀሙ አበረታታቸው። ጊዜ በፈቀደልህ መጠን አድማጮች በትምህርት ቤት ውስጥ በመመሥከራቸው ያገኙት ተሞክሮ ካለ እንዲናገሩ ጋብዝ።

መዝሙር 24 (50)

ነሐሴ 25 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 85 (191)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ።

20 ደቂቃ:- ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

15 ደቂቃ:- ወቅታዊ መጽሔቶችን ለማበርከት ዝግጅት አድርጉ። ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። በቅርብ የደረሷችሁን የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔቶች ይዘት በአጭሩ ከተናገርክ በኋላ በክልላችሁ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ይበልጥ የሚማርከው የትኛው ርዕስ እንደሆነ አድማጮችን ጠይቅ። ርዕሰ ጉዳዩን ለማስተዋወቅ ምን ጥያቄ እና የትኛውን ጥቅስ መጠቀም ይቻላል። በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የሚገኘውን የናሙና አቀራረብ እንዴት ልንጠቀምበት እንደምንችል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። አንድ የጉባኤ ሽማግሌ ለክልሉ ተስማሚ በሆነ አንድ ርዕስ ላይ ተመሥርቶ የተዘጋጀውን አጭር መግቢያ በሠርቶ ማሳያ መልክ እንዲያቀርብ አድርግ።

መዝሙር 6 (13)

መስከረም 1 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 47 (112)

10 ደቂቃ:- የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የነሐሴ ወር የአገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው።

20 ደቂቃ:- “በመንፈሳዊ የምንመገብበትና የምንደሰትበት ዝግጅት።”*

15 ደቂቃ:- በመስከረም ወር፣ ሰዎችን በምታነጋግሯቸው በመጀመሪያው ዕለት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አስጀምሩ። ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። በመስከረም ወር የምናበረክተው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ ሲሆን የቤቱን ባለቤት በምናነጋግርበት በመጀመሪያው ዕለት ከግለሰቡ ጋር ጥቂት አንቀጾችን ለመወያየት ጥረት እናደርጋለን። በጥር 2006 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ላይ የወጡትን ሐሳቦች ከልስ፤ በተጨማሪም ሰዎችን በምናነጋግርበት በመጀመሪያው ዕለት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዴት ማስጀመር እንደሚቻል የሚያሳዩ አንድ ወይም ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።

መዝሙር 34 (77)

[የግርጌ ማስታወሻ]

አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ