የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 9/08 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
  • ንዑስ ርዕሶች
  • መስከረም 8 የሚጀምር ሳምንት
  • መስከረም 15 የሚጀምር ሳምንት
  • መስከረም 22 የሚጀምር ሳምንት
  • መስከረም 29 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥቅምት 6 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
km 9/08 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

ማሳሰቢያ፦ የመንግሥት አገልግሎታችን የአውራጃ ስብሰባ በሚደረግባቸው ወራት በእያንዳንዱ ሳምንት በአገልግሎት ስብሰባ ላይ የሚቀርቡ ክፍሎችን ፕሮግራም ይዞ ይወጣል። ጉባኤዎች “በአምላክ መንፈስ መመራት” በተሰኘው የአውራጃ ስብሰባ ላይ ለመገኘት እንደ አስፈላጊነቱ ማስተካከያዎችን ማድረግ ይችላሉ። የሚቻል ከሆነ የአውራጃ ስብሰባው ሊደረግ አንድ ሳምንት ሲቀረው በምታደርጉት የአገልግሎት ስብሰባ ላይ በዚህ ወር የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ከወጡት ምክሮችና ማሳሰቢያዎች ውስጥ ጉባኤያችሁን የሚመለከቱትን ለመወያየት 15 ደቂቃ መመደብ ትችላላችሁ። የአውራጃ ስብሰባውን ካደረጋችሁ ከአንድ ወይም ከሁለት ወር በኋላ ደግሞ አስፋፊዎች ከስብሰባው ለአገልግሎት ጠቃሚ ሆኖ ያገኟቸውን ሐሳቦች ለመከለስ እንዲችሉ በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ከ15 እስከ 20 ደቂቃ መድቡ። (ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት የሚለውን ክፍል መጠቀም ትችላላችሁ።) ክለሳውን ማቅረብ የሚኖርበት የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ነው። ወንድሞች በአውራጃ ስብሰባው ላይ ያገኙትን ትምህርት በአገልግሎታቸው ተግባራዊ እያደረጉ ያሉት እንዴት እንደሆነ ወይም ተግባራዊ ለማድረግ ምን ዝግጅት እንዳደረጉ ጠይቃቸው።

መስከረም 8 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 90 (204)

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በቅርብ ከደረሷችሁ መጽሔቶች መካከል በክልላችሁ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ይበልጥ የሚማርኩት የትኞቹ ርዕሶች እንደሆኑ አድማጮችን ጠይቅ። ርዕሶቹን ለማስተዋወቅ ምን ጥያቄዎች እንደተጠቀሙና የትኞቹን ጥቅሶች እንዳነበቡ ጠይቅ። እያንዳንዱን መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።

15 ደቂቃ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች የአምላክ ቃል አስተማሪዎች እንዲሆኑ እርዳ። በጥር 15, 2007 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 29-30 አንቀጽ 14-20 ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። አንድ አስፋፊ ለአዲስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቱ ስለ ሕዝብ ንግግርና ስለ መጠበቂያ ግንብ ጥናት አጠር ያለ መግለጫ ከሰጠው በኋላ በስብሰባዎቹ ላይ እንዲገኝ ሲጋብዘው የሚያሳይ አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።

20 ደቂቃ፦ በአገልግሎት ላይ የሚያጋጥመንን ጭፍን ጥላቻ መቋቋም። ሰዎች ያላቸው ጭፍን ጥላቻ በአገልግሎታችን ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ በተመለከተ በጽሑፎቻችን ላይ በወጡ ሐሳቦች ተመሥርቶ በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። እንዲህ ያለውን ጥላቻ እንዴት መቋቋም እንደሚቻል ግለጽ። አንዳንድ ጊዜ በመስክ አገልግሎት ላይም ሆነ በዕለት ተዕለት ሕይወታችን የምናሳየው ምግባር ሰዎች ያላቸው ጥላቻ እንዲረግብ ብሎም እውነትን ለመስማት ፈቃደኞች እንዲሆኑ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ሊያበረክት ይችላል። በመሆኑም ሁልጊዜ ስለምንናገራቸው ነገሮች እንዲሁም ስለምግባራችን ጠንቃቆች መሆን አለብን። (1 ጴጥ. 2:12፤ 3:1, 2) ጭፍን ጥላቻን እንዴት መቋቋም እንደሚቻል የሚያሳዩ ከአካባቢው የተገኙ ወይም ጽሑፍ ላይ የወጡ ጥቂት ተሞክሮዎችን ተናገር።

መዝሙር 51 (127)

መስከረም 15 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 13 (33)

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።

20 ደቂቃ፦ ያለፈው ዓመት የአገልግሎት እንቅስቃሴያችን ምን ይመስል ነበር? የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ወይም ብቃት ያለው ሌላ ሽማግሌ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት ያቅርበው። ጉባኤው ባከናወናቸው መልካም ነገሮች ላይ ትኩረት በማድረግ ያለፈውን የአገልግሎት ዓመት እንቅስቃሴ ይከልሳል። ለተደረጉት መልካም ነገሮች አመስግናቸው። ያገኟቸውን ግሩም ተሞክሮዎች የሚናገሩ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች አስቀድመህ አዘጋጅ። በያዝነው የአገልግሎት ዓመት ጉባኤው ትኩረት ሊያደርግባቸው የሚገቡ አንድ ወይም ሁለት ነጥቦችን ጥቀስ፤ እንዲሁም ማሻሻያ ለማድረግ የሚረዱ ተግባራዊ ሐሳቦችን ተናገር።

15 ደቂቃ፦ በፍጥረት እንደማምን በደንብ ማስረዳት የምችለው እንዴት ነው? በጽሑፎቻችን ላይ በወጡ ሐሳቦች ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። አድማጮች በትምህርት ቤት፣ በሥራ ቦታ ወይም በሌላ ቦታ በፍጥረት እንደሚያምኑ ማስረዳት የቻሉት እንዴት እንደሆነ እንዲናገሩ ጋብዝ። ሐሳብ የሚሰጡ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎችን አስቀድመህ ማዘጋጀት ትችላለህ።

መዝሙር 24 (50)

መስከረም 22 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 23 (48)

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ። የግንቦትን የአገልግሎት ሪፖርትና የጉባኤውን የመስክ አገልግሎት እንቅስቃሴ በሚመለከት ጎላ ብለው የሚታዩ አንዳንድ ነጥቦችን ተናገር።

20 ደቂቃ፦ የድካማችሁን ዋጋ ታገኛላችሁ። በሚያዝያ 15, 2005 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 28 አንቀጽ 6 እስከ ገጽ 29 መጨረሻ ድረስ ባሉት ሐሳቦች ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። ይሖዋ ቁሳዊ ወይም ስሜታዊ ፍላጎታቸውን ያሟላላቸው እንዴት እንደሆነ እንዲናገሩ ከአንድ ወይም ከሁለት ቀናተኛ አስፋፊዎች ጋር አጭር ቃለ ምልልስ አድርግ።

15 ደቂቃ፦ የነሐሴ 1 መጠበቂያ ግንብ እና የነሐሴ ንቁ! መጽሔቶችን ለማበርከት ዝግጅት አድርጉ። መጽሔቶቹን በአጭሩ ካስተዋወቅህ በኋላ በክልላችሁ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ይበልጥ የሚማርኩት የትኞቹ ርዕሶች እንደሆኑ ጠይቅ። ርዕሱን ለማስተዋወቅ ምን ጥያቄ እንደሚጠቀሙና የትኞቹን ጥቅሶች እንደሚያነቡ ጠይቅ። በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ከሚገኙት የናሙና መግቢያዎች መካከል አንዱን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። አንድ የጉባኤ ሽማግሌ ለክልሉ ተስማሚ በሆነ አንድ ርዕስ ላይ ተመሥርቶ የተዘጋጀውን አጭር መግቢያ በሠርቶ ማሳያ መልክ እንዲያቀርብ አድርግ።

መዝሙር 84 (190)

መስከረም 29 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 20 (45)

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የመስከረም ወር የአገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። ባለፉት ወራት እረፍት ላይ እያሉ ወይም በሌሎች አጋጣሚዎች መደበኛ ባልሆነ መንገድ ሲመሰክሩ ያገኙትን ተሞክሮ እንዲናገሩ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎችን አስቀድመህ አዘጋጅ።

15 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

20 ደቂቃ፦ “ከጥቅምት 20 እስከ ኅዳር 16 የሚካሄድ ልዩ የትራክት ዘመቻ!”* ትራክቱ ደርሷችሁ ከሆነ ለተሰብሳቢዎች አንድ አንድ ቅጂ እንዲታደል አድርግ። አንቀጽ 2ን ስትወያዩ የትራክቱን ይዘት በአጭሩ ተናገር። አንቀጽ 4ን ስትወያዩ ደግሞ ትራክቱን እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። በአንቀጽ 5 ላይ ስትወያዩ አንድ አስፋፊ በተመላልሶ መጠየቅ ወቅት ትራክቱን ተጠቅሞ እንዴት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር እንደሚችል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።

መዝሙር 33 (72)

ጥቅምት 6 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 100 (222)

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።

15 ደቂቃ፦ የጥያቄ ሣጥን። ከአድማጮች ጋር የሚደረግ ውይይት። ከሰኔ 15, 2005 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 20-22 አንቀጽ 10-16 ላይ አንዳንድ ሐሳቦችን ጨምረህ አቅርብ።

20 ደቂቃ፦ “ሌሎች ሰዎች ይሖዋን እንዲወዱ አስተምሯቸው።”* ጊዜ በፈቀደልህ መጠን አድማጮች ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ በተጠቀሱ ጥቅሶች ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ።

መዝሙር 54 (132)

[የግርጌ ማስታወሻ]

አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ