የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ጥቅምት 27, 2008 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከመስከረም 1 እስከ ጥቅምት 27, 2008 ድረስ ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ30 ደቂቃ ክለሳ ይመራል።
የንግግር ባሕርይ
1. ሰዎች በአንድ ነገር ላይ እንዲያምኑ ያደረጋቸው ምን እንደሆነ መረዳት የምንችለው እንዴት ነው? [be ገጽ 259 አን. 1, 2]
2. አንድ ሰው ጥላቻንና ወገናዊነትን ከልቡ ነቅሎ እንዲያወጣ እንዴት ልንረዳው እንችላለን? [be ገጽ 260 አን. 2]
3. የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎቻችን በመንፈሳዊ እድገት የማድረግ ግብ በመያዝ ልባቸውን እንዲመረምሩ እንዴት ልንረዳቸው እንችላለን? [be ገጽ 261 አን. 2]
4. የአድማጮቻችንን ልብ ለመንካት ስንጥር ምን ነገር መዘንጋት አይኖርብንም? [be ገጽ 262 አን. 3]
5. በጉባኤ ስብሰባ ላይ የተመደበልንን ሰዓት መጠበቅን በተመለከተ ትኩረት መስጠት የሚገባን ለምንድን ነው? [be ገጽ 263 አን. 1, 3 እና ሣጥኑ]
ክፍል ቁ. 1
6. ጳውሎስ፣ ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች የመጀመሪያውን ደብዳቤ እንዲጽፍላቸው ያነሳሳው ምንድን ነው? [bsi08-1 ገጽ 20 አን. 3]
7. ጳውሎስ፣ ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ሁለተኛውን ደብዳቤ እንዲጽፍ ያነሳሱት አንዳንድ ምክንያቶች ምንድን ናቸው? [bsi08-1 ገጽ 22 አን. 1-2]
8. ክርስቲያኖች ለአገልግሎት ምን ዓይነት አመለካከት ሊኖራቸው ይገባል? [bsi08-1 ገጽ 23 አን. 18]
9. በዛሬው ጊዜ በፊልጵስዩስ እንደነበሩት ወንድሞች የአምላክን ሞገስ ማግኘትና ለወንድሞቻችን የደስታ ምንጭ መሆን የምንችለው እንዴት ነው? [bsi08-1 ገጽ 29 አን. 12]
10. ጳውሎስና የእምነት ባልንጀሮቹ በተሰሎንቄ በሚገኘው ጉባኤ ላይ ምን በጎ ተጽዕኖ አሳድረዋል? [bsi08-2 ገጽ 4 አን. 13]
ሳምንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
11. ክፉ ድርጊት የፈጸመው ሰው “ሥጋው ጠፍቶ መንፈሱ [“የጉባኤው መንፈስ፣” NW] . . . [ይድን] ዘንድ፣ እንደዚህ ዐይነቱ ለሰይጣን ይሰጥ” ሲባል ምን ማለት ነው? (1 ቆሮ. 5:5) [w08 7/15 “የይሖዋ ቃል ሕያው ነው—ለቆሮንቶስ ሰዎች የተጻፉት ደብዳቤዎች ጎላ ያሉ ነጥቦች”]
12. የኢየሱስ ሞት መታሰቢያ መከበር ያለበት በየስንት “ጊዜ” ነው? ይህ በዓል መከበር ያለበትስ እስከ መቼ ድረስ ነው? (1 ቆሮ. 11:26) [w08 7/15 “የይሖዋ ቃል ሕያው ነው—ለቆሮንቶስ ሰዎች የተጻፉት ደብዳቤዎች ጎላ ያሉ ነጥቦች”]
13. በ2 ቆሮንቶስ 12:2-4 ላይ ምን ራእይ ተገልጿል? ይህን ራእይ ያየውስ ማን መሆን አለበት? [w04 10/15 ገጽ 8 አን. 4፤ ገጽ 10 አን. 9]
14. ጳውሎስ የሙሴን ሕግ ‘ወደ ክርስቶስ ከሚያደርስ ሞግዚት’ ጋር ያመሳሰለው ለምን ነበር? (ገላ. 3:24) [w08 3/1 ገጽ 18-21]
15. ጳውሎስ፣ የወንድሞች ‘መንፈስ፣ ነፍስና አካል ተጠብቆ እንዲቆይ’ ያቀረበው ጸሎት ምን ትርጉም አለው? (1 ተሰ. 5:23) [w08 9/15 “የይሖዋ ቃል ሕያው ነው—ለተሰሎንቄ ሰዎችና ለጢሞቴዎስ የተጻፉት ደብዳቤዎች ጎላ ያሉ ነጥቦች”]