ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች፦ ጥቅምት፦ መጽሔቶች እና ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ይበልጥ ማወቅ ትፈልጋለህ? (ትራክት ቁጥር 26)፤ ኅዳር፦ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? ታኅሣሥ፦ ታላቅ ሰው ወይም ከታላቁ አስተማሪ ተማር፤ ጥር፦ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
◼ የኅዳር ወር አምስት ቅዳሜና እሁዶች ስላሉት ረዳት አቅኚ ለመሆን አመቺ ነው።
◼ ለሰብሳቢ የበላይ ተመልካችና ለቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት የበላይ ተመልካች የተሰጠ ማሳሰቢያ፦ አዲሱ የጉባኤ ስብሰባ ፕሮግራም ተግባራዊ መሆን የሚጀምረው ታኅሣሥ 29, 2008 በሚጀምረው ሳምንት ውስጥ ሲሆን በታኅሣሥ 2008 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ ከዚህ ማስተካከያ ጋር የተያያዘ ፕሮግራም ይወጣል። በዚያ ሳምንት ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ ስታደርጉ በ2009 የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም ላይ ያለውን መመሪያ በጥብቅ ተከተሉ። በዚያ ምሽት የንግግር ባሕርይ አይቀርብም።
◼ ደም አልወስድም—የሕክምናው መስክ መፍትሔ አስገኝቷል የተባለው ቪዲዮ በጥር ወር ውስጥ በአገልግሎት ስብሰባ ላይ ውይይት ይደረግበታል። ፊልሙን ማግኘት የምትፈልጉ ከሆነ በተቻለ ፍጥነት በጉባኤያችሁ በኩል ማዘዝ ይኖርባችኋል።
◼ አዲስ የደረሱን ጽሑፎች፦ አማርኛ፦ “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው [bsi08-2-AM]፤ እንግሊዝኛ፦ ዎርኒንግ ኤግዛምፕልስ/ሪስፔክት ኦቶሪቲ በዲቪዲ።
◼በድጋሚ የደረሱን ጽሑፎች፦ እንግሊዝኛ፦ ኮንኮርዳንስ፤ የወጣቶች ጥያቄ—ሕይወቴን እንዴት ብጠቀምበት ይሻላል? በዲቪዲ፤ ኦሮምኛ፦ የአምላክ ወዳጅ መሆን፤ ትግርኛ፦ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?