የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 10/08 ገጽ 1
  • አዲስ የጉባኤ ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አዲስ የጉባኤ ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ውጤታማ የሆነ የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2015
  • የጥያቄ ሣጥን
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
  • በአክብሮት ተጋብዘሃል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ‘ለፍቅርና ለመልካም ሥራዎች የሚያነቃቁ’ ስብሰባዎች
    የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
km 10/08 ገጽ 1

አዲስ የጉባኤ ስብሰባ ፕሮግራም

1, 2. ከጥር 2009 ጀምሮ በስብሰባዎች ላይ ምን ለውጦች ይደረጋሉ?

1 ከሚያዝያ 21-27, 2008 በነበረው ሳምንት ውስጥ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ጉባኤዎች የሚከተለው አስደሳች ማስታወቂያ ተነብቦ ነበር፦ “ከጥር 1, 2009 ጀምሮ የጉባኤ መጽሐፍ ጥናት ከቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት እና ከአገልግሎት ስብሰባ ጋር አንድ ላይ ይወሰዳል። የጉባኤ መጽሐፍ ጥናት የቀድሞ ስያሜ ተለውጦ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ይባላል።”

2 የዚህ ሳምንታዊ ስብሰባ ፕሮግራም፦ መዝሙሮችንና ጸሎቶችን ጨምሮ ይህ ስብሰባ በጠቅላላ የሚወስደው ጊዜ 1 ሰዓት ከ45 ደቂቃ ይሆናል። ስብሰባው በመዝሙርና በጸሎት (5 ደቂቃ) ከተከፈተ በኋላ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት (25 ደቂቃ) ይደረጋል። ቀጥሎ የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ስብሰባ (30 ደቂቃ) ይቀርባል። ከዚያም የአገልግሎት ስብሰባ (35 ደቂቃ) በመዝሙር (5 ደቂቃ) ይጀመራል። ስብሰባው በመዝሙርና በጸሎት (5 ደቂቃ) ይደመደማል። ለእነዚህ ስብሰባዎች ዝግጅት እንድታደርጉ ለመርዳት ሲባል የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤትና የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ በየወሩ ይወጣል።

3. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚመራው እንዴት ነው?

3 የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ ይህ ስብሰባ የሚመራበት መንገድ ከመጠበቂያ ግንብ ጥናት ጋር ተመሳሳይ ይሆናል። በስብሰባው መግቢያ ላይ ያለፈውን ሳምንት ጥናት መከለስ አስፈላጊ አይደለም። ከዚህ ይልቅ መግቢያው እጥር ምጥን ያለ መሆን ይኖርበታል። ይህ ደግሞ በስብሰባው ላይ የተገኙ ሁሉ አጠር አጠር ያሉ ሐሳቦችን እንዲሰጡ የሚያስችል በቂ ጊዜ ያስገኛል። ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ የጉባኤ ሽማግሌዎች ስብሰባውን ተራ በተራ እንዲመሩ የሚያስችል ፕሮግራም ያወጣል፤ በየሳምንቱ የተለያየ ሽማግሌ መምራት ይኖርበታል።

4. በአገልግሎት ስብሰባ ላይ የተደረገው ለውጥ ምንድን ነው?

4 የአገልግሎት ስብሰባ፦ በአገልግሎት ስብሰባ ይዘት ላይ ለውጥ አይደረግም፤ ይሁን እንጂ ክፍሎቹ አጫጭር ይሆናሉ። የጉባኤ ማስታወቂያዎች አብዛኛውን ጊዜ በአምስት ደቂቃ ይቀርባሉ። ይህ ደቂቃ አስፈላጊ የሆኑ ማስታወቂያዎችንና ከቅርንጫፍ ቢሮ የሚላኩ አንዳንድ ደብዳቤዎችን ለማንበብ በቂ ነው። የመስክ አገልግሎት ዝግጅቶችን፣ ጽዳትንና የሒሳብ ሪፖርትን አስመልክተው እንደሚወጡት ያሉ ማስታወቂያዎች እንዲሁም ቅርንጫፍ ቢሮው በየጊዜው የሚልካቸው ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው ደብዳቤዎች ከመድረክ መነበብ አያስፈልጋቸውም። ከዚህ ይልቅ ወንድሞች እንዲያነቧቸው በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ይለጠፋሉ። ክፍል እንዲያቀርቡ የተመደቡ ሁሉ በሚገባ መዘጋጀት፣ መመሪያዎችን በጥብቅ መከተልና ሰዓታቸውን መጠበቅ ይገባቸዋል።

5. የወረዳ የበላይ ተመልካቹ በሚጎበኝበት ሳምንት ስብሰባዎች የሚካሄዱት እንዴት ነው?

5 የወረዳ የበላይ ተመልካች ጉብኝት፦ የወረዳ የበላይ ተመልካቹ በሚጎበኝበት ሳምንት የሚኖረው ፕሮግራም ለውጥ አይደረግበትም። ማክሰኞ ዕለት ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤትና የአገልግሎት ስብሰባ ከተደረገ በኋላ መዝሙር ይዘመራል። ከዚያም የወረዳ የበላይ ተመልካቹ የ30 ደቂቃ ንግግር ያቀርባል። በአሁኑ ጊዜ እንደሚደረገው በጉብኝቱ ሳምንት አንድ ሌላ የስብሰባ ቀን ይኖራል፤ በዚህ ቀን ምሽት ላይ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ከተደረገ በኋላ መዝሙር ተዘምሮ የወረዳ የበላይ ተመልካቹ የአገልግሎት ንግግር ያቀርባል። ስብሰባው በመዝሙርና በጸሎት ይደመደማል።

6. የቡድን የበላይ ተመልካቾች ኃላፊነት ምንድን ነው?

6 የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎች፦ የቡድን የበላይ ተመልካቾች በጉባኤው የሽማግሌዎች አካል ተመድበው የመስክ አገልግሎት ቡድኖችን በኃላፊነት ይከታተላሉ እንዲሁም በቡድኑ ውስጥ ለሚገኙ አስፋፊዎች እረኝነት ያደርጋሉ። ይህን ኃላፊነት ለአንድ የጉባኤ አገልጋይ መስጠት አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ወንድም “የቡድን አገልጋይ” ተብሎ ይጠራል።

7. አዲሱ የጉባኤ ስብሰባ ፕሮግራም ምን ውጤት ያስገኛል ብለን መጠበቅ እንችላለን?

7 ከጉባኤ ስብሰባዎች ጋር በተያያዘ የተደረገውን አዲስ ዝግጅት አስመልክቶ የተሰጠው ሐሳብ እንደሚጠቁመው ትምህርት ሰጪና ገንቢ የሆነ መንፈሳዊ ግብዣ ተዘጋጅቶልናል። ይህ ዝግጅት ይበልጥ ፍሬያማ አገልግሎት ለማከናወን የሰለጠንን ውጤታማ ሰባኪዎችና አስተማሪዎች እንድንሆን ያስችለናል።—ኤፌ. 4:13, 14፤ 2 ጢሞ. 3:17

8. በግለሰብ ደረጃ አስቀድመን መዘጋጀታችን ራሳችንንም ሆነ ሌሎችን የሚጠቅመው እንዴት ነው?

8 ለእነዚህ ስብሰባዎች አስቀድመን ጥሩ ዝግጅት ማድረጋችን በእያንዳንዱ ስብሰባ ወቅት በሚብራሩት ዋና ዋና ነጥቦች ላይ እንድናተኩር ይረዳናል። ሁላችንም ሐሳብ የመስጠት አጋጣሚ ይኖረናል፤ ይህ ደግሞ እርስ በርስ ለመበረታታት ያስችለናል። (ሮሜ 1:11, 12፤ ዕብ. 10:24) ግባችን ‘የእውነትን ቃል በትክክል በማስረዳት’ ‘እድገታችን እንዲታይ’ ማድረግ መሆን ይኖርበታል።—1 ጢሞ. 4:15፤ 2 ጢሞ. 2:15

9. ቁርጥ ውሳኔያችን ምን መሆን ይኖርበታል? ለምንስ?

9 የጉባኤ ስብሰባዎችን በተመለከተ አዲስ ዝግጅት በመደረጉ በጣም ተደስተናል። ሁላችንም ‘ታማኝና ልባም ባሪያ’ የሚሰጠንን መመሪያ መከተላችንን በመቀጠል በቅርብ ለሚመጣው ታላቅ “መከራ” ወደሚያዘጋጀን ታላቁ እረኛችን ይበልጥ እንቅረብ።—ማቴ. 24:21, 45፤ ዕብ. 13:20, 21፤ ራእይ 7:14

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ