የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 10/08 ገጽ 2
  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ጥቅምት 13 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥቅምት 20 የሚጀምር ሳምንት
  • ጥቅምት 27 የሚጀምር ሳምንት
  • ኅዳር 3 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2008
km 10/08 ገጽ 2

የአገልግሎት ስብሰባ ፕሮግራም

ጥቅምት 13 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 77 (174)

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ጉባኤው ከጥቅምት 20 ጀምሮ ለሚካሄደው ልዩ የትራክት ዘመቻ ምን ዝግጅት እንዳደረገ ተናገር፤ እንዲሁም አስፋፊዎች እስካሁን ትራክቱን ካልወሰዱ የተወሰነ መጠን እንዲወስዱ ሁሉንም አበረታታ። የመስከረም 1 መጠበቂያ ግንብ እና የመስከረም ንቁ! መጽሔቶችን ለማበርከት የሚያስችሉትን በገጽ 4 ላይ የሚገኙትን የናሙና አቀራረቦች በአጭሩ ከልስ። በርካታ አስፋፊዎች ባለፉት ጥቂት ሳምንታት እነዚህን መጽሔቶች ሲያበረክቱ ስለቆዩ ያገኙትን ተሞክሮ እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።

35 ደቂቃ፦ “አዲስ የጉባኤ ስብሰባ ፕሮግራም።”* ጊዜ በፈቀደልህ መጠን ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ የተጠቀሱ ጥቅሶችን አንብብ፤ እንዲሁም አድማጮች በጥቅሶቹ ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ።

መዝሙር 39 (86)

ጥቅምት 20 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 48 (113)

5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።

20 ደቂቃ፦ በአገልግሎት የምታገኙትን ደስታ ጠብቃችሁ ኑሩ። በሐምሌ 1, 2005 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 24-25 አንቀጽ 11-17 ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ የሚያበረታታ ንግግር። ይሖዋን ለረጅም ዓመታት በታማኝነት ላገለገሉ አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች ቃለ መጠይቅ አድርግ። ሰዎች በጎ ምላሽ በማይሰጡበት ጊዜም እንኳ ደስታቸውን ጠብቀው እንዲኖሩ የረዳቸው ምንድን ነው?

20 ደቂቃ፦ የመስከረም 1 መጠበቂያ ግንብ እና የመስከረም ንቁ! መጽሔቶችን ለማበርከት ዝግጅት አድርጉ። መጽሔቶቹን በአጭሩ ካስተዋወቅህ በኋላ በክልላችሁ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ሰዎችን ሊማርኩ ይችላሉ የሚሏቸውን ርዕሶች እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ። እንዲህ ያሉበትን ምክንያት እንዲናገሩ ጠይቃቸው። ውይይት ለመጀመር ያስችላል የሚሉትን ጥያቄ እንዲሁም መጽሔቱን ከማበርከታቸው በፊት ከርዕሱ ውስጥ ለማንበብ ያሰቡትን ጥቅስ እንዲናገሩ ጋብዝ። ተናጋሪው ገጽ 4 ላይ የቀረቡትን የመግቢያ ሐሳቦች ወይም በአገልግሎት ክልሉ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን ሊማርክ የሚችል ሌላ መግቢያ ተጠቅሞ እያንዳንዱን መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ በማቅረብ ክፍሉን ይደመድማል።

መዝሙር 63 (148)

ጥቅምት 27 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 71 (163)

5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርትና ጉባኤው ላደረገው መዋጮ ቅርንጫፍ ቢሮው የላከውን ምስጋና አንብብ።

10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።

30 ደቂቃ፦ “የግልና የቤተሰብ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በጣም አስፈላጊ ናቸው!”* ጊዜ በፈቀደልህ መጠን ምዕራፍና ቁጥራቸው ብቻ የተጠቀሱ ጥቅሶችን አንብብ፤ እንዲሁም አድማጮች በጥቅሶቹ ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ።

መዝሙር 87 (195)

ኅዳር 3 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 23 (48)

10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። አስፋፊዎች የጥቅምት ወር የአገልግሎት ሪፖርታቸውን እንዲሰጡ አስታውሳቸው። የጉባኤውንና የአገሪቱን የመስክ አገልግሎት እንቅስቃሴ በሚመለከት ጎላ ብለው የሚታዩ አንዳንድ ነጥቦችን ተናገር።

20 ደቂቃ፦ የ2009 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች በ2009 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም ላይ የሚገኘውን “መመሪያ” መሠረት በማድረግ በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ የተደረገውን ማስተካከያ ከአድማጮች ጋር ይወያይበታል። በዋነኝነት በተደረጉት ማስተካከያዎች ላይ አተኩር። ክፍል ሲሰጣቸው ተገኝተው በማቅረብ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጎላ ያሉ ነጥቦች ላይ ሐሳብ ለመስጠት በመዘጋጀት እንዲሁም የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም በተባለው መጽሐፍ መሠረት በየሳምንቱ የሚሰጠውን ምክር ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ትጉዎች እንዲሆኑ ሁሉንም አበረታታ።

15 ደቂቃ፦ ‘የማስተማር ጥበባችሁን’ አዳብሩ። የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ወይም ብቃት ያለው ሌላ ሽማግሌ ጥር 15, 2008 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 9-12 በአንቀጽ 5-18 ላይ የሚገኙትንና ውጤታማ አስተማሪ ለመሆን የሚያስችሉትን አምስት ቁልፍ ነጥቦች ነጥሎ በማውጣት አጠር ያለ ሐሳብ ይሰጥባቸዋል። በመጠበቂያ ግንቡ ላይ የቀረበው ሐሳብ የማስተማር ችሎታቸውን ለማሻሻል እንደረዳቸው ለሚሰማቸው አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች ቃለ ምልልስ አድርግ።

መዝሙር 36 (81)

[የግርጌ ማስታወሻዎች ]

አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ