ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች፦ ኅዳር፦ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? ታኅሣሥ፦ ታላቅ ሰው ወይም ከታላቁ አስተማሪ ተማር፤ ጥር፦ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የካቲት፦ ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? ወይም መጽሐፍ ቅዱስ—የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው?
◼ እስካሁን ድረስ የሕክምና መመሪያ ካርድ ያልሞሉ አስፋፊዎች በሙሉ ካርዱን በተሟላ ሁኔታ እንዲሞሉ ልናሳስባቸው እንወዳለን። ይህ ካርድ በሕክምና ወቅት ደም ያለመውሰድ መብታችሁን ያስጠብቅላችኋል። ሽማግሌዎች እንደ አስፈላጊነቱ በግለሰብ ደረጃ እገዛ ማበርከት ይችላሉ።—የኅዳር 2006 የመንግሥት አገልግሎታችንን አባሪ ተመልከት።
◼ ከጥር 1, 2009 ጀምሮ “ሰብሳቢ የበላይ ተመልካች” በሚለው መጠሪያ አንጠቀምም። ከዚህ በኋላ በዚህ የኃላፊነት ቦታ የሚያገለግል ወንድም “የሽማግሌዎች አካል አስተባባሪ” ተብሎ ይጠራል።