የ2009 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ፕሮግራም
መመሪያ
የ2009 ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት በሚከተሉት ዝግጅቶች መሠረት ይካሄዳል።
ክፍሎቹ የሚቀርቡባቸው ጽሑፎች፦ መጽሐፍ ቅዱስ [አ.መ.ት እና የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም (bi7-AM)]፣ መጠበቂያ ግንብ [W]፣ ከታላቁ አስተማሪ ተማሩ [lr] እና ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር [rs]።
ትምህርት ቤቱ ልክ በሰዓቱ አጠር ባለ ሰላምታ ከተከፈተ በኋላ ከዚህ በታች በሰፈረው መመሪያ መሠረት ይካሄዳል። እያንዳንዱ ክፍል ሲያበቃ የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ቀጣዩን ክፍል ያስተዋውቃል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ጎላ ያሉ ነጥቦች፦ 10 ደቂቃ። በመጀመሪያዎቹ አራት ደቂቃዎች ጥሩ ችሎታ ያለው ሽማግሌ ወይም የጉባኤ አገልጋይ በሳምንቱ ውስጥ እንድናነባቸው ከተመደቡልን የመጽሐፍ ቅዱስ ምዕራፎች ላይ አንዳንድ ነጥቦችን ያብራራል። ለሳምንቱ የተመደበው ንባብ የአንድን የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ የመጀመሪያ ምዕራፎች የያዘ በሚሆንበት ጊዜ ግን በመጀመሪያዎቹ አራት ደቂቃዎች የሚቀርበው ሐሳብ የሚወሰደው ከጥር 1, 2004 የመጠበቂያ ግንብ እትም ጀምሮ ከወጣው “የይሖዋ ቃል ሕያው ነው” የሚል ርዕስ ካለው ተከታታይ ዓምድ ይሆናል። ለምሳሌ ያህል፣ ጥር 5 በሚጀምረው ሳምንት የዘፍጥረትን መጽሐፍ የመጀመሪያ አምስት ምዕራፎች እናነባለን፤ ስለዚህ ክፍሉ የተሰጠው ወንድም በጥር 1, 2004 መጠበቂያ ግንብ ላይ “የይሖዋ ቃል ሕያው ነው” በሚለው ዓምድ ሥር ከሚገኙት የዘፍጥረትን መጽሐፍ ከሚያስተዋውቁት የመግቢያ አንቀጾች ውስጥ ጥቂት ቁልፍ ነጥቦችን በመምረጥ ክፍሉን ያቀርበዋል። ይህ ወንድም ትምህርቱን ጉባኤውን ሊጠቅም በሚችል መንገድ ማቅረብ ይኖርበታል። ክፍሉ የሚቀርበው ከሳምንቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ላይ የተገኙ ነጥቦችን በማብራራትም ይሁን “የይሖዋ ቃል ሕያው ነው” ከተባለው የመጠበቂያ ግንብ ዓምድ ላይ የተወሰዱ ሐሳቦችን በመጠቀም፣ የክፍሉ ዋነኛ ዓላማ ወንድሞች ትምህርቱ ለምን እና እንዴት እንደሚጠቅም እንዲገነዘቡ መርዳት ነው። ተናጋሪው ለእሱ የተመደበለትን አራት ደቂቃ ላለማሳለፍ መጠንቀቅ ይኖርበታል። ወንድሞች ከሳምንቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ልባቸውን የነካውን ሐሳብ በ30 ሴኮንድ ወይም ከዚያ ባነሰ ጊዜ ውስጥ በአጭሩ መናገር እንዲችሉ ስድስት ደቂቃ ማስተረፍ አለበት። ከዚያም የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች በሁለተኛው አዳራሽ ክፍል የሚያቀርቡ ተማሪዎች መሄድ እንደሚችሉ ያስታውቃል።
ክፍል ቁ. 1፦ በ4 ደቂቃ ወይም ከዚያ ባነሰ ጊዜ የሚቀርብ። ይህን ክፍል አንድ ወንድም በንባብ ያቀርበዋል። ተማሪው መግቢያ ወይም መደምደሚያ ማዘጋጀት ሳያስፈልገው ክፍሉን በንባብ ብቻ ያቀርበዋል። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ተማሪዎቹ ክፍሉን በሚገባ ተረድተው፣ በቅልጥፍና፣ ቁልፍ ቃላትን በተገቢው ሁኔታ በማጥበቅ፣ ድምፅን በመለዋወጥ፣ በተገቢው ቦታ ቆም በማለትና የራሳቸውን ተፈጥሯዊ አነጋገር በመጠቀም ማንበብ እንዲችሉ ለመርዳት ጥረት ያደርጋል።
ክፍል ቁ. 2፦ 5 ደቂቃ። ይህ ክፍል ለአንዲት እህት ይሰጣል። ይህን ክፍል የምታቀርበው እህት መቼት ይሰጣታል ወይም በቲኦክራሲያዊ አገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም ከተባለው መጽሐፍ ገጽ 82 ላይ ከተዘረዘሩት መቼቶች መካከል አንዱን ልትመርጥ ትችላለች። ተማሪዋ በፕሮግራሙ ላይ የሚገኘውን ጭብጥ መጠቀም ያለባት ከመሆኑም በላይ ክፍሉ በአንድ የመስክ አገልግሎት ዘርፍ ላይ የሚያጋጥም የተለመደ ሁኔታን የሚያሳይና ለጉባኤው የአገልግሎት ክልል የሚሠራ መሆን ይኖርበታል። ጭብጡ ብቻ በሚሰጥበት ጊዜ ተማሪዋ በጽሑፎቻችን ላይ ምርምር በማድረግ ለክፍሉ የሚስማሙ ነጥቦችን ማሰባሰብ ይኖርባታል። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ተማሪዋ የተሰጣትን ጭብጥ እንዴት እንደምታዳብር እንዲሁም የቤቱ ባለቤት የጥቅሶቹን ትርጉምና የክፍሉን ዋና ዋና ነጥቦች እንድትገነዘብ የምትረዳበትን መንገድ ለማየት ይፈልጋል። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች አንድ ረዳት ይመድብላታል።
ክፍል ቁ. 3፦ 5 ደቂቃ። ይህ ክፍል ለአንድ ወንድም ወይም ለአንዲት እህት ይሰጣል። ተማሪው የተሰጠውን ጭብጥ ማዳበር ይኖርበታል። ጭብጡ ብቻ በሚሰጥበት ጊዜ ተማሪው በጽሑፎቻችን ላይ ምርምር በማድረግ ለክፍሉ የሚስማሙ ነጥቦችን ያሰባስባል። ይህ ክፍል ለአንድ ወንድም በሚሰጥበት ጊዜ አድማጮቹን ግምት ውስጥ በማስገባት በንግግር መልክ ያቀርበዋል። ሆኖም ክፍሉን አንዲት እህት የምታቀርበው ከሆነ ለክፍል ቁጥር 2 በተሰጠው መመሪያ መሠረት መቅረብ ይኖርበታል። የኮከብ ምልክት ያለባቸው ክፍሎች በንግግር መልክ መቅረብ ያለባቸው ስለሆኑ ለወንድሞች ብቻ መሰጠት ይኖርባቸዋል፤ የሚቻል ከሆነ አንድ ሽማግሌ ወይም የጉባኤ አገልጋይ ቢያቀርበው ይመረጣል።
ምክር፦ 1-2 ደቂቃ። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ተማሪው የሚሠራበትን የንግግር ባሕርይ አስቀድሞ አይናገርም። ክፍል ቁ. 1፣ ቁ. 2 እና ቁ. 3 ከቀረበ በኋላ የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች የክፍሉን ገንቢ ጎኖች አንስቶ ተማሪውን ያመሰግናል። ከአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ላይ በተደጋጋሚ በመጥቀስ ክፍሉ ጥሩ የሆነበትን ምክንያት ለይቶ መናገር ያስፈልገዋል። እያንዳንዱ ተማሪ በበለጠ ሊሠራበት የሚያስፈልገውን ነገር ግምት ውስጥ በማስገባት ከስብሰባው በኋላ ወይም በሌላ ጊዜ ገንቢ የሆነ ተጨማሪ ምክር በግል መስጠት ይችላል።
ጊዜ መጠበቅ፦ ክፍል የሚያቀርቡትም ሆኑ ምክር ሰጪው የተመደበላቸውን ጊዜ ማሳለፍ አይኖርባቸውም። ክፍል ቁ. 1ን፣ ቁ. 2ን እንዲሁም ቁ. 3ን የሚያቀርቡት ተማሪዎች የተመደበላቸው ጊዜ ሲሞላ በዘዴ እንዲያቆሙ ማድረግ ያስፈልጋል። ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ የተገኙ ጎላ ያሉ ነጥቦችን የሚያቀርቡ ወንድሞች ሰዓት ካሳለፉ በግል ምክር ሊሰጣቸው ይገባል። ሁሉም ሰዓታቸውን በሚገባ መጠበቅ አለባቸው። ጠቅላላው ፕሮግራም 30 ደቂቃ ይፈጃል።
ምክር መስጫ ቅጽ፦ በአገልግሎት ትምህርት ቤት መማሪያ መጽሐፉ ውስጥ ይገኛል።
ረዳት ምክር ሰጪ፦ የሽማግሌዎች አካል፣ ከትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች በተጨማሪ ረዳት ምክር ሰጪ ሆኖ የሚያገለግል ጥሩ ችሎታ ያለው ሽማግሌ ሊመርጥ ይችላል። በጉባኤው ውስጥ በርካታ ሽማግሌዎች ካሉ በየዓመቱ ብቃት ያላቸው ሽማግሌዎች እየተቀያየሩ ይህን ኃላፊነት ሊይዙ ይችላሉ። የረዳት ምክር ሰጪው ወንድም ኃላፊነት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ጎላ ያሉ ነጥቦችን ለሚያቀርቡ ወንድሞች አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በግል ምክር መስጠት ይሆናል። ይህ ሲባል ግን እነዚህን ክፍሎች የሚያቀርቡ ሽማግሌዎች ወይም የጉባኤ አገልጋዮች ንግግራቸውን ባቀረቡ ቁጥር ምክር ይሰጣቸዋል ማለት አይደለም።
የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ፦ 20 ደቂቃ። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች በየሁለት ወሩ የሚደረገውን ክለሳ ይመራል። ክለሳው የሚደረገው የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ጎላ ያሉ ነጥቦች ከላይ በተሰጠው መመሪያ መሠረት ከቀረቡ በኋላ ይሆናል። ክለሳው፣ የክለሳውን ሳምንት ጨምሮ ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ የቀረቡትን ትምህርቶች ይሸፍናል። የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳው ጉባኤያችሁ የወረዳ ስብሰባ በሚያደርግበት ወይም የወረዳ የበላይ ተመልካች ጉባኤውን በሚጎበኝበት ሳምንት ላይ ከዋለ ክለሳው በቀጣዩ ሳምንት ይቀርባል፤ በቀጣዩ ሳምንት ይቀርቡ የነበሩት የተማሪ ክፍሎች ደግሞ (ቁ. 1፣ ቁ. 2 እና ቁ. 3) በዚህኛው ሳምንት ላይ ይቀርባሉ። በሳምንታዊው የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብም ሆነ ጎላ ያሉ ነጥቦች በሚቀርቡበት ፕሮግራም ላይ ለውጥ መደረግ አይኖርበትም።
ፕሮግራም
ጥር 5 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 1-5
ቁ. 1፦ ዘፍጥረት 3:1-15
ቁ. 2፦ ኢየሱስ ታላቅ አስተማሪ የነበረው ለምንድን ነው? (lr ምዕ. 1)
ቁ. 3፦ ከንቱ ያልሆነው ነገር ምንድን ነው? (1 ቆሮ. 15:58)
ጥር 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 6-10
ቁ. 1፦ ዘፍጥረት 9:1-17
ቁ. 2፦ በአምላክ ማመንን አስመልክቶ ለሚነሱ የተቃውሞ ሐሳቦች ምላሽ መስጠት (rs ገጽ 151 አን. 1 እስከ ገጽ 152 አን. 1)
ቁ. 3፦ ከሚወደን አምላክ የተላከ ደብዳቤ (lr ምዕ. 2)
ጥር 19 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 11-16
ቁ. 1፦ ዘፍጥረት 14:1-16
ቁ. 2፦ ሁሉንም ነገሮች የሠራው ፈጣሪ (lr ምዕ. 3)
ቁ. 3፦ ይሖዋ የሚቀርጸን እንዴት ነው? (ኢሳ. 64:8)
ጥር 26 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 17-20
ቁ. 1፦ ዘፍጥረት 17:1-17
ቁ. 2፦ የሰው ልጆች ትክክለኛ መስተዳድር ማቋቋም ያልቻሉት ለምንድን ነው? (rs ገጽ 152 አን. 2 እስከ ገጽ 153 አን. 6)
ቁ. 3፦ አምላክ ስም አለው (lr ምዕ. 4)
የካ. 2 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 21-24
ቁ. 1፦ ዘፍጥረት 22:1-18
ቁ. 2፦ “ልጄ ይህ ነው” (lr ምዕ. 5)
ቁ. 3፦ * ለሌሎች ያለንን ፍቅር ማስፋት የምንችልባቸው መንገዶች (2 ቆሮ. 6:11-13)
የካ. 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 25-28
ቁ. 1፦ ዘፍጥረት 25:1-18
ቁ. 2፦ ታላቁ አስተማሪ ሌሎች ሰዎችን አገልግሏል (lr ምዕ. 6)
ቁ. 3፦ የሰው ልጆች ከጭቆና ለመላቀቅ የሚያደርጉት ጥረት ሊሳካ የማይችለው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 154 አን. 1-6)
የካ. 16 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 29-31
ቁ. 1፦ ዘፍጥረት 29:1-20
ቁ. 2፦ ‘መጨነቃችንን መተው’ ያለብን ለምንድን ነው? (ማቴ. 6:25)
ቁ. 3፦ ታዛዥነት ይጠብቅሃል (lr ምዕ. 7)
የካ. 23 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 32-35
የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
መጋ. 2 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 36-39
ቁ. 1፦ ዘፍጥረት 39:1-16
ቁ. 2፦ ከእኛ በላይ የሆኑ አሉ (lr ምዕ. 8)
ቁ. 3፦ የሰው ልጆችን ፍላጎት ሊያሟላ የሚችለው የአምላክ መንግሥት ብቻ ነው (rs ገጽ 155 አን. 1 እስከ ገጽ 156 አን. 1)
መጋ. 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 40-42
ቁ. 1፦ ዘፍጥረት 40:1-15
ቁ. 2፦ የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች መቋቋም ያስፈልገናል (lr ምዕ. 9)
ቁ. 3፦ * በራስ የመመራት ዝንባሌ እንዳይጠናወታችሁ ተጠንቀቁ!
መጋ. 16 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 43-46
ቁ. 1፦ ዘፍጥረት 44:1-17
ቁ. 2፦ ኢየሱስ ከአጋንንት የበለጠ ኃይል አለው (lr ምዕ. 10)
ቁ. 3፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ትክክልና አስተማማኝ መሆናቸው ተረጋግጧል (rs ገጽ 156 አን. 2-5)
መጋ. 23 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 47-50
ቁ. 1፦ ዘፍጥረት 48:1-16
ቁ. 2፦ ዲያብሎስን ልንፈራው ይገባል?
ቁ. 3፦ ከአምላክ መላእክት የሚገኝ እርዳታ (lr ምዕ. 11)
መጋ. 30 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፀአት 1-6
ቁ. 1፦ ዘፀአት 1:1-19
ቁ. 2፦ ኢየሱስ እንድንጸልይ አስተምሮናል (lr ምዕ. 12)
ቁ. 3፦ በዘመናችን የሚደረገው ፈውስ በአምላክ መንፈስ እርዳታ የሚከናወን ነው? (rs ገጽ 157 አን. 2 እስከ 158 አን. 2)
ሚያ. 6 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፀአት 7-10
ቁ. 1፦ ዘፀአት 9:1-19
ቁ. 2፦ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት (lr ምዕ. 13)
ቁ. 3፦ * ገላትያ 6:2ን ከገላትያ 6:5 ጋር የምናስማማው እንዴት ነው?
ሚያ. 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፀአት 11-14
ቁ. 1፦ ዘፀአት 12:21-36
ቁ. 2፦ ይቅር ማለት ያለብን ለምንድን ነው? (lr ምዕ. 14)
ቁ. 3፦ ኢየሱስና ሐዋርያቱ ያከናውኑ በነበረው ፈውስና በዘመናችን በሚደረጉት ፈውሶች መካከል ያሉት ልዩነቶች (rs ገጽ 158 አን. 3-6)
ሚያ. 20 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፀአት 15-18
ቁ. 1፦ ዘፀአት 15:1-19
ቁ. 2፦ ከሐሰት አምልኮ መራቅ ምን ነገሮችን ይጨምራል?
ቁ. 3፦ ደግ ስለመሆን የተሰጠ ትምህርት (lr ምዕ. 15)
ሚያ. 27 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፀአት 19-22
ግን. 4 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፀአት 23-26
ቁ. 1፦ ዘፀአት 24:1-18
ቁ. 2፦ ይበልጥ አስፈላጊ የሆነው ነገር ምንድን ነው? (lr ምዕ. 16)
ቁ. 3፦ በዛሬው ጊዜ እውነተኛ ክርስቲያኖች ተለይተው የሚታወቁት በምንድን ነው? (rs ገጽ 159 አን. 1-5)
ግን. 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፀአት 27-29
ቁ. 1፦ ዘፀአት 29:1-18
ቁ. 2፦ ደስተኛ መሆን የሚቻልበት መንገድ (lr ምዕ. 17)
ቁ. 3፦ * ያለቦታው ታማኝነት ማሳየትና እንዲህ ማድረግ ያሉት አደጋዎች
ግን. 18 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፀአት 30-33
ቁ. 1፦ ዘፀአት 31:1-18
ቁ. 2፦ በመጀመሪያው መቶ ዘመን ለነበሩት ክርስቲያኖች የመፈወስ ችሎታ የተሰጣቸው ለምን ነበር? (rs ገጽ 160 አን. 1 እስከ ገጽ 161 አን. 1)
ቁ. 3፦ ለተደረገልህ ነገር አስታውሰህ ታመሰግናለህ? (lr ምዕ. 18)
ግን. 25 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፀአት 34-37
ቁ. 1፦ ዘፀአት 37:1-24
ቁ. 2፦ መጣላት ተገቢ ነው? (lr ምዕ. 19)
ቁ. 3፦ * መረን መልቀቅ ሲባል ምን ማለት ነው? መወገድ ያለበትስ ለምንድን ነው?
ሰኔ 1 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፀአት 38-40
ቁ. 1፦ ዘፀአት 40:1-19
ቁ. 2፦ ሁልጊዜ ቅድሚያ ማግኘት ትፈልጋለህ? (lr ምዕ. 20)
ቁ. 3፦ የሰው ዘር እውነተኛ ፈውስ ለማግኘት ምን ተስፋ አለው? (rs ገጽ 161 አን. 2-4)
ሰኔ 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘሌዋውያን 1-5
ቁ. 1፦ ዘሌዋውያን 4:1-15
ቁ. 2፦ ጉራ መንዛት ይኖርብናል? (lr ምዕ. 21)
ቁ. 3፦ * ክርስቲያኖች ሥልጣናቸውን እንዴት መጠቀም ይኖርባቸዋል?
ሰኔ 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘሌዋውያን 6-9
ቁ. 1፦ ዘሌዋውያን 8:1-17
ቁ. 2፦ ‘በፈውስ ታምናለህ?’ (rs ገጽ 161 አን. 5-6)
ቁ. 3፦ መዋሸት የሌለብን ለምንድን ነው? (lr ምዕ. 22)
ሰኔ 22 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘሌዋውያን 10-13
ቁ. 1፦ ዘሌዋውያን 11:29-45
ቁ. 2፦ ሰዎች የሚታመሙት ለምንድን ነው? (lr ምዕ. 23)
ቁ. 3፦ የተጠመቁ ደቀ መዛሙርት የሚያገኟቸው በረከቶች
ሰኔ 29 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘሌዋውያን 14-16
ሐምሌ 6 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘሌዋውያን 17-20
ቁ. 1፦ ዘሌዋውያን 19:1-18
ቁ. 2፦ ሁላችንም ሰው ሆነን ከመወለዳችን በፊት በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ እንኖር ነበር? (rs ገጽ 162 አን. 1 እስከ ገጽ 163 አን. 1)
ቁ. 3፦ ሌባ እንዳትሆን ተጠንቀቅ! (lr ምዕ. 24)
ሐምሌ 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘሌዋውያን 21-24
ቁ. 1፦ ዘሌዋውያን 22:17-33
ቁ. 2፦ መጥፎ ነገር የሚሠሩ ሰዎች ሊለወጡ ይችላሉ? (lr ምዕ. 25)
ቁ. 3፦ እውነተኛ ክርስቲያኖች ለድሆች እንደሚያስቡ የሚያሳዩት እንዴት ነው?
ሐምሌ 20 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘሌዋውያን 25-27
ቁ. 1፦ ዘሌዋውያን 25:39-54
ቁ. 2፦ ጥሩ ነገር መሥራት ከባድ የሆነው ለምንድን ነው? (lr ምዕ. 26)
ቁ. 3፦ አዳም ኃጢአት ባይሠራ ኖሮ በመጨረሻ ወደ ሰማይ ይሄድ ነበር? (rs ገጽ 163 አን. 2-3)
ሐምሌ 27 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኍልቍ 1-3
ቁ. 1፦ ዘኍልቍ 3:1-20
ቁ. 2፦ ገርነትን ለማንጸባረቅ ራስን መግዛት የሚያስፈልገው ለምንድን ነው?
ቁ. 3፦ አምላክህ ማን ነው? (lr ምዕ. 27)
ነሐሴ 3 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኍልቍ 4-6
ቁ. 1፦ ዘኍልቍ 4:1-16
ቁ. 2፦ ማንን መታዘዝ እንዳለብን ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው? (lr ምዕ. 28)
ቁ. 3፦ አንድ ሰው እውነተኛ ደስታ ያለበት ሕይወት እንዲያገኝ የግድ ወደ ሰማይ መሄድ ይኖርበታል? (rs ገጽ 163 አን. 4-6)
ነሐሴ 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኍልቍ 7-9
ቁ. 1፦ ዘኍልቍ 9:1-14
ቁ. 2፦ ሁሉም ዓይነት ግብዣ አምላክን ያስደስተዋል? (lr ምዕ. 29)
ቁ. 3፦ ለይሖዋ ታማኝ መሆናችንን የምናሳይባቸው መንገዶች
ነሐሴ 17 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኍልቍ 10-13
ቁ. 1፦ ዘኍልቍ 13:17-33
ቁ. 2፦ ያለብንን ፍርሃት ለማሸነፍ የሚያስችል እርዳታ (lr ምዕ. 30)
ቁ. 3፦ አንደኛ ጴጥሮስ 3:19, 20 ምን ማለት ነው? (rs ገጽ 164 አን. 1)
ነሐሴ 24 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኍልቍ 14-16
ቁ. 1፦ ዘኍልቍ 14:26-43
ቁ. 2፦ የአምላክን ሕግ መውደድ ሲባል ምን ማለት ነው? (መዝ. 119:97)
ቁ. 3፦ መጽናኛ ማግኘት የሚቻለው ከየት ነው? (lr ምዕ. 31)
ነሐሴ 31 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኍልቍ 17-21
መስ. 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኍልቍ 22-25
ቁ. 1፦ ዘኍልቍ 22:20-35
ቁ. 2፦ ኢየሱስ ጥበቃ ያገኘው እንዴት ነው? (lr ምዕ. 32)
ቁ. 3፦ የ1 ጴጥሮስ 4:6 ትርጉም ምንድን ነው? (rs ገጽ 164 አን. 2)
መስ. 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኍልቍ 26-29
ቁ. 1፦ ዘኍልቍ 27:1-14
ቁ. 2፦ የይሖዋን አስተሳሰብ በልጆች ውስጥ መቅረጽ ሲባል ምን ማለት ነው? አስፈላጊ የሆነውስ ለምንድን ነው? (ኤፌ. 6:4)
ቁ. 3፦ ኢየሱስ ሊጠብቀን ይችላል (lr ምዕ. 33)
መስ. 21 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኍልቍ 30-32
ቁ. 1፦ ዘኍልቍ 32:1-15
ቁ. 2፦ ስንሞት ምን እንሆናለን? (lr ምዕ. 34)
ቁ. 3፦ ሁሉም ክርስቲያኖች ወደ ሰማይ የመሄድ ተስፋ አላቸው? (rs ገጽ 164 አን. 3 እስከ ገጽ 165 አን. 2)
መስ. 28 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኍልቍ 33-36
ቁ. 1፦ ዘኍልቍ 33:1-23
ቁ. 2፦ ከሞት ልንነሳ እንችላለን! (lr ምዕ. 35)
ቁ. 3፦ የአምላክ መንግሥት ከየትኛውም ሰብዓዊ መንግሥት የላቀ የሆነው በምን መንገዶች ነው?
ጥቅ. 5 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘዳግም 1-3
ቁ. 1፦ ዘዳግም 2:1-15
ቁ. 2፦ “አዲስ ኪዳን” በምድር ላይ ለዘላለም ስለ መኖር ምን ይላል? (rs ገጽ 165 አን. 3 እስከ ገጽ 166 አን. 3)
ቁ. 3፦ ከሞት የሚነሱት እነማን ናቸው? የሚኖሩትስ የት ነው? (lr ምዕ. 36)
ጥቅ. 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘዳግም 4-6
ቁ. 1፦ ዘዳግም 4:15-28
ቁ. 2፦ ይሖዋንና ልጁን ማስታወስ (lr ምዕ. 37)
ቁ. 3፦ ጥቂት ነገር ይበልጣል ሊባል የሚችለው መቼ ነው? (ምሳሌ 15:16)
ጥቅ. 19 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘዳግም 7-10
ቁ. 1፦ ዘዳግም 9:1-14
ቁ. 2፦ ኢየሱስን መውደድ ያለብን ለምንድን ነው? (lr ምዕ. 38)
ቁ. 3፦ መጽሐፍ ቅዱስ ስንት ሰዎች የሰማያዊ ሕይወት ተስፋ እንዳላቸው ያሳያል? (rs ገጽ 166 አን. 4-5)
ጥቅ. 26 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘዳግም 11-13
ኅዳር 2 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘዳግም 14-18
ቁ. 1፦ ዘዳግም 15:1-15
ቁ. 2፦ አምላክን መፍራት ከምን ነገሮች ጋር ተዛማጅነት አለው?
ቁ. 3፦ አምላክ ልጁን አልረሳውም (lr ምዕ. 39)
ኅዳር 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘዳግም 19-22
ቁ. 1፦ ዘዳግም 22:1-19
ቁ. 2፦ አምላክን ማስደሰት የምንችለው እንዴት ነው? (lr ምዕ. 40)
ቁ. 3፦ አንድ መቶ አርባ አራት ሺዎቹ ከሥጋዊ አይሁዳውያን ብቻ የተውጣጡ ናቸው? (rs ገጽ 167 አን. 1-4)
ኅዳር 16 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘዳግም 23-27
ቁ. 1፦ ዘዳግም 25:1-16
ቁ. 2፦ አምላክን የሚያስደስቱ ልጆች (lr ምዕ. 41)
ቁ. 3፦ * ቅዱስ አድርገን ልንመለከታቸው የሚገቡ ነገሮች የትኞቹ ናቸው?
ኅዳር 23 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘዳግም 28-31
ቁ. 1፦ ዘዳግም 30:1-14
ቁ. 2፦ ሥራ መሥራት የሚያስፈልገን ለምንድን ነው? (lr ምዕ. 42)
ቁ. 3፦ መጽሐፍ ቅዱስ “እጅግ ብዙ ሕዝብ” ስላላቸው ተስፋ ምን ይላል? (rs ገጽ 167 አን. 5 እስከ ገጽ 168 አን. 2)
ኅዳር 30 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘዳግም 32-34
ቁ. 1፦ ዘዳግም 32:1-21
ቁ. 2፦ “ታላቁ የይሖዋ ቀን” ምንድን ነው? (ሶፎ. 1:14 NW)
ቁ. 3፦ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እነማን ናቸው? (lr ምዕ. 43)
ታኅ. 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢያሱ 1-5
ቁ. 1፦ ኢያሱ 5:1-15
ቁ. 2፦ ጓደኞቻችን አምላክን የሚወዱ መሆን ይኖርባቸዋል (lr ምዕ. 44)
ቁ. 3፦ የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? እንደምንፈልገው የምናሳየውስ እንዴት ነው? (lr ምዕ. 45)
ታኅ. 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢያሱ 6-8
ቁ. 1፦ ኢያሱ 8:1-17
ቁ. 2፦ ዓለም በውኃ ጠፋ—ዳግመኛ በውኃ ይጠፋ ይሆን? (lr ምዕ. 46)
ቁ. 3፦ በመክብብ 7:21, 22 ላይ የሚገኘው ምክር ጠቃሚ ነው የምንለው ለምንድን ነው?
ታኅ. 21 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢያሱ 9-11
ቁ. 1፦ ኢያሱ 9:1-15
ቁ. 2፦ አርማጌዶን እንደቀረበ ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው? (lr ምዕ. 47)
ቁ. 3፦ አምላክ በሚያመጣው ሰላማዊ አዲስ ዓለም ውስጥ መኖር ትችላለህ (lr ምዕ. 48)
ታኅ. 28 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኢያሱ 12-15
[የግርጌ ማስታወሻዎች ]
ለወንድሞች ብቻ የሚሰጥ፤ ሽማግሌዎች ወይም የጉባኤ አገልጋዮች ቢያቀርቡት ይመረጣል።