የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
በዚህ የአገልግሎት ዓመት መጀመሪያ ላይ 1,192 የሚያህሉ የዘወትር አቅኚዎች ሪፖርት ያደረጉ ሲሆን ይህም ለአገራችን አዲስ ከፍተኛ ቁጥር ነው። ሪፖርት የተደረገው አጠቃላይ ሰዓት (219,098) ካለፈው ዓመት 8 በመቶ ይበልጣል። ባለፈው ዓመት በአገራችን ባሉ ጉባኤዎች ውስጥ 27 ሰዎች ማንበብና መጻፍ ተምረዋል። ከዚህም በተጨማሪ በአሁኑ ጊዜ 162 ጉባኤዎችና 39 ቡድኖች ያሉን መሆኑ ያስደስተናል። ባለፉት ወራት በዱከም፣ በአላዎአርኬ (ቱላ አካባቢ)፣ በወልዲያ እና በየረር (አዲስ አበባ) የመንግሥት አዳራሽ ግንባታ ተጠናቋል። በአሁኑ ጊዜ እነዚህን ጨምሮ በአገራችን ውስጥ 118 የመንግሥት አዳራሾች አሉ። እነዚህን የመሰሉ ግሩም ውጤቶች በማግኘታችን የተደሰትን ሲሆን ወደፊት ደግሞ በአገራችን ስለተካሄዱት የአውራጃ ስብሰባዎችና ስለ ልዩ የትራክት ዘመቻው አስደሳች ሪፖርቶችን ለመስማት በጉጉት እንጠባበቃለን።