የካቲት 9 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
መዝሙር 4 (8)
❑ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
❑ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 25-28
ቁ. 1፦ ዘፍጥረት 25:1-18
ቁ. 2፦ ታላቁ አስተማሪ ሌሎች ሰዎችን አገልግሏል (lr ምዕ. 6)
ቁ. 3፦ የሰው ልጆች ከጭቆና ለመላቀቅ የሚያደርጉት ጥረት ሊሳካ የማይችለው ለምንድን ነው? (rs ገጽ 154 አን. 1-6)
❑ የአገልግሎት ስብሰባ፦
መዝሙር 93 (211)
5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
8 ደቂቃ፦ አዲስ የጉባኤ ስብሰባ መጋበዣ ወረቀት። አዲሱ የስብሰባ መጋበዣ ወረቀት ያሉትን ገጽታዎች የሚያስተዋውቅና እንዴት እንደምንጠቀምበት የሚያብራራ ንግግር። የመጋበዣ ወረቀቱ መጠነኛ ፍላጎት ለሚያሳዩ ሰዎች ሁሉ መሰጠት ይኖርበታል። የመጋበዣ ወረቀቱን ከቤት ወደ ቤት ስናገለግልም ሆነ ተመላልሶ መጠየቅ በምናደርግበት ወቅት እንዴት ልንጠቀምበት እንደምንችል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን በማስጀመር ረገድ የተገኙ ተሞክሮዎች። ባሳለፍነው ወር ውስጥ ጉባኤው በመረጠው ቀን ላይ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያጠኑ ግብዣ በማቅረብ ረገድ ምን ውጤት እንደተገኘ ተናገር። ሁሉም በዚህ ልዩ ቀን ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያጠኑ በመጋበዙ ሥራ እንዲካፈሉ አበረታታ።
12 ደቂቃ፦ “ሰዎች በመታሰቢያው በዓል ላይ እንዲገኙ ለመጋበዝ የሚደረግ ልዩ ዘመቻ!” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። የመታሰቢያው በዓል መጋበዣ ወረቀት አንድ ቅጂ ለአድማጮች እንዲታደል አድርግ፤ ከዚያም ስለ ይዘቱ በአጭሩ ተናገር። በመጋበዣ ወረቀቱ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 40 (87)