የካቲት 23 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 58 (138)
❑ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
❑ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 32-35
የቲኦክራሲያዊ አገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
❑ የአገልግሎት ስብሰባ፦
መዝሙር 7 (19)
5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በመጋቢት ወር የሚበረከተው ጽሑፍ ምን እንደሆነ ተናገር።
10 ደቂቃ፦ የመጋቢት 1 መጠበቂያ ግንብ እና የመጋቢት ንቁ! መጽሔቶችን ለማበርከት ዝግጅት አድርጉ። መጽሔቶቹን በአጭሩ ካስተዋወቅህ በኋላ በክልላችሁ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ይበልጥ የሚማርኩት የትኞቹ ርዕሶች እንደሆኑና ለምን እንዲህ እንዳሉ አድማጮችን ጠይቅ። መጽሔቶቹን ከማበርከታቸው በፊት ውይይት ለመጀመር ምን ጥያቄዎችን ሊያነሱ እንደሚችሉና የትኞቹን ጥቅሶች ለማንበብ እንዳሰቡ አድማጮችን ጋብዝ። በክፍሉ መደምደሚያ ላይ ሁለቱንም መጽሔቶች እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
10 ደቂቃ፦ ቅዱሳን መጻሕፍትን በየዕለቱ መመርመር የተባለውን ቡክሌት እየተጠቀማችሁበት ነው? ቅዱሳን መጻሕፍትን በየዕለቱ መመርመር—2009 በተባለው ቡክሌት መቅድም ላይ ተመሥርቶ በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። በየቀኑ፣ ጊዜ መድበን የዕለቱን ጥቅስና በዚያ ላይ የተሰጠውን ሐሳብ ማንበባችን ያለውን ጠቀሜታ ተናገር። የዕለቱን ጥቅስ ስለሚያነቡበት ፕሮግራምና እንዲህ ማድረጋቸው ስላስገኘላቸው ጥቅም እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።
መዝሙር 69 (160)