የቲኦክራሲያዊ አገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
የካቲት 23, 2009 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከጥር 5 እስከ የካቲት 23, 2009 ድረስ ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ20 ደቂቃ ክለሳ ይመራል።
1. ብርሃን ሰጪ አካላት የተፈጠሩት በአራተኛው ቀን ከሆነ አምላክ በመጀመሪያው ቀን ብርሃን እንዲኖር እንዴት ማድረግ ይችላል? (ዘፍ. 1:3, 16) [w04 1/1 ገጽ 28 አን. 5]
2. በፋሌቅ ዘመን ምድሪቱ ‘የተከፈለችው’ እንዴት ነበር? (ዘፍ. 10:25) [w04 1/1 ገጽ 31]
3. የአብርሃም ቃል ኪዳን ተግባራዊ የሆነው ከመቼ ጀምሮ ነው? ቃል ኪዳኑ የሚጸናውስ ለምን ያህል ጊዜ ነው? (ዘፍ. 12:1-4) [w04 1/15 ገጽ 26 አን. 4፤ w01 8/15 ገጽ 17 አን. 13]
4. ናምሩድና የእሱን አመራር የተከተሉት ሰዎች እንዳሰቡት ‘ስማቸውን ማስጠራት’ እንዳልቻሉ የሚያሳየው ምንድን ነው? (ዘፍ. 11:4) [w98 3/15 ገጽ 25]
5. ሎጥ በ2 ጴጥሮስ 2:7 ላይ ‘ጻድቅ’ ሰው ተብሎ ተጠርቶ እያለ ሴቶች ልጆቹን ለሰዶም ሰዎች ለመስጠት ያሰበው ለምን ሊሆን ይችላል? (ዘፍ. 19:8) [w05 2/1 ገጽ 26 አን. 15-16፤ w04 1/15 ገጽ 27 አን. 3]
6. ባልና ሚስቶች፣ አብርሃም ከእስማኤል ጋር በተያያዘ በአጋርና በሣራ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ከፈታበት መንገድ ምን ትምህርት ማግኘት ይችላሉ? (ዘፍ. 21:10-14፤ 1 ተሰ. 2:13) [w06 4/15 ገጽ 6 አን. 5-8]
7. ኤሊዔዘር ለይስሐቅ ሚስት ለመፈለግ በሄደበት ወቅት ነገሮችን በይሖዋ መንገድ ለማከናወን ካደረገው ጥረት ምን እንማራለን? (ዘፍ. 24:14, 15, 17-19, 26, 27) [w97 1/1 ገጽ 31 አን. 2]
8. ያዕቆብ፣ መላእክት ‘በመሰላል ሲወጡና ሲወርዱ’ ያየው ሕልም ትርጉሙ ምንድን ነው? (ዘፍ. 28:10-13) [w03 10/15 ገጽ 29 አን. 1፤ it-2 ገጽ 189]
9. ራሔል፣ የልያን ልጅ እንኮይ ለማግኘት በጣም የፈለገችው ለምን ነበር? (ዘፍ. 30:14, 15) [w04 1/15 ገጽ 28 አን. 7]
10. የዲና ምሳሌ ራስን ለአደገኛ ሁኔታዎች ማጋለጥ መጥፎ ውጤት እንደሚያስከትል የሚያስተምረን እንዴት ነው? (ዘፍ. 34:1, 2, 19) [w04 10/15 ገጽ 21 አን. 6፤ ገጽ 22 አን. 5]