የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
በአገራችን በተደረጉት 20 የአውራጃ ስብሰባዎች ላይ በአጠቃላይ 14,281 ተሰብሳቢዎች ተገኝተዋል፤ እንዲሁም 296 ሰዎች ተጠምቀዋል። የዘወትር አቅኚዎች ቁጥር 1,204 የደረሰ ሲሆን ይህም አዲስ ከፍተኛ ቁጥር ነው። እውነቱን ማወቅ ትፈልጋለህ? የተባለውን አዲስ ትራክት ለማሰራጨት በተካሄደው ዘመቻ ጉባኤዎች ጥሩ ተሳትፎ አድርገዋል። በአጠቃላይ 85,823 ተመላልሶ መጠየቆች የተደረጉ ሲሆን ይህም ብዙ ሰዎችን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር እንደሚቻል ያሳያል።