ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች፦ የካቲት፦ ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? ወይም መጽሐፍ ቅዱስ—የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው? መጋቢት፦ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? እና ሚያዝያና ግንቦት፦ መጽሔቶች።
◼ ከመጋቢት ወር የመጀመሪያ ሳምንት አንስቶ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች የሚያቀርቡት አዲሱ የሕዝብ ንግግር “ዓለማዊ ቅዠቶችን አስወግዳችሁ የመንግሥቱን እውነቶች ተከታተሉ” የሚል ጭብጥ ይኖረዋል።
◼ በመታሰቢያው በዓል ሰሞን የሚቀርበው የ2009 ልዩ የሕዝብ ንግግር ሚያዝያ 26, 2009 ይቀርባል። የንግግሩ ርዕስ “ሁሉም ሃይማኖቶች በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት አላቸው?” የሚል ነው። በዚያ ሳምንት የወረዳ የበላይ ተመልካች ጉብኝት ወይም የወረዳ አሊያም የልዩ ስብሰባ ያላቸው ጉባኤዎች ልዩ የሕዝብ ንግግሩን በቀጣዩ ሳምንት ማቅረብ ይችላሉ። በየትኛውም ጉባኤ ልዩ የሕዝብ ንግግሩ ከሚያዝያ 20 በፊት መቅረብ አይኖርበትም።
◼ እንደገና የደረሱን ጽሑፎች፦ አማርኛ፦ ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ! አምላክ ከእኛ የሚፈልገው፣ ስንሞት ምን እንሆናለን?፣ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፣ T-19፣ T-20፣ T-22፣ T-27፤ አረብኛ፦ ጋይዳንስ፣ Bi-12፤ እንግሊዝኛ፦ ከታላቁ አስተማሪ ተማር፣ ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች—1፣ ጠለቅ ብሎ ማስተዋል፣ የውዳሴ መዝሙር በ8 ሲዲዎች፣ ፐርሱ ጎልስ በዲቪዲ፤ ፈረንሳይኛ፦ የኢሳይያስ ትንቢት—1፣ የኢሳይያስ ትንቢት—2፣ አምላክ ስለ እኛ ያስባልን?፣ አወር ፕሮብለምስ፣ የሙታን መናፍስት፤ ኦሮምኛ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፣ አምላክ ስለ እኛ ያስባልን?
◼ በእጃችን የሚገኙ ጽሑፎች፦ አማርኛ፦ የውይይት አርዕስት፣ ነቅተህ ጠብቅ!፣ የይሖዋ ምሥክሮች እና ትምህርት ቤት፤ እንግሊዝኛ፦ የ2007 የዓመት መጽሐፍ፣ የ2005 የመጠበቂያ ግንብ ጥራዝ፤ በካሴት፦ ታላቁ አስተማሪ፣ ወደ ይሖዋ ቅረብ፣ ሄሪቴጅ (ድራማ)፤ በቪዲዮ ካሴት፦ ፐርፕል ትራያንግልስ፣ ዘ ባይብል—አኪዩሬት ሂስትሪ፣ ዘ ባይብል—ኦልደስት ሞደርን ቡክ፣ ዘ ባይብል—ኢትስ ፓወር፣ ቱ ዚ ኤንድስ ኦቭ ዚ ኧርዝ፣ ስታንድ ፈርም፣ አሶሲየሽን ኦቭ ብራዘርስ፣ ፌዝፉል አንደር ትራያልስ።