መጋቢት 16 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
መጋቢት 16 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 45 (106)
❑ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
❑ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፍጥረት 43-46
ቁ. 1፦ ዘፍጥረት 44:1-17
ቁ. 2፦ ኢየሱስ ከአጋንንት የበለጠ ኃይል አለው (lr ምዕ. 10)
ቁ. 3፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ትክክልና አስተማማኝ መሆናቸው ተረጋግጧል (rs ገጽ 156 አን. 2-5)
❑ የአገልግሎት ስብሰባ፦
መዝሙር 53 (130)
5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ ይሖዋ የሚለው ስም ባለቤት የሆነው አምላክ። በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ላይ በገጽ 274 አንቀጽ 2-5 ላይ ተመሥርቶ በግለት የሚቀርብ ንግግር።
10 ደቂቃ፦ የ2009ን የዓመት መጽሐፍ በጥሩ ሁኔታ ተጠቀሙበት። በንግግርና ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። “ከበላይ አካል የተላከ ደብዳቤ” የሚለውን ተወያዩበት። ከዓመት መጽሐፉ ላይ በተለይ ለእነሱ አበረታች ሆኖ ያገኙትን ተሞክሮ በአጭሩ እንዲናገሩ ጥቂት አስፋፊዎችን አስቀድመህ አዘጋጅ። በተጨማሪም አድማጮች ከዓለም አቀፉ ሪፖርት ላይ ያስደነቃቸውን ነገር በተመለከተ ሐሳብ እንዲሰጡ ጋብዝ። ሁሉም የዓመት መጽሐፉን ከዳር እስከ ዳር እንዲያነቡ በማበረታታት ክፍሉን ደምድም።
10 ደቂቃ፦ “‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’ የተባለውን መጽሐፍ ጥናት ለመምራት ልንጠቀምበት የምንችለው እንዴት ነው?” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳብ ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው።
መዝሙር 49 (114)