የቲኦክራሲያዊ አገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ሚያዝያ 27, 2009 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከመጋቢት 2 እስከ ሚያዝያ 27, 2009 ድረስ ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ20 ደቂቃ ክለሳ ይመራል።
1. ዮሴፍ በየዕለቱ ያጋጥመው የነበረውን ፈተና መቋቋም የቻለው እንዴት ነው? (ዘፍ. 39:7-12) [lv ገጽ 105 አን. 18 እስከ ገጽ 106 አን. 20]
2. መጽሐፍ ቅዱስ የልደት ቀንን ስለ ማክበር ምን ይላል? (ዘፍ. 40:20-22) [lv ገጽ 150 አን. 9 እስከ ገጽ 151 አን. 11]
3. ዮሴፍ ለበደሉን ሰዎች ይቅርታ በማድረግ ረገድ ግሩም ምሳሌ የሚሆነው እንዴት ነው? (ዘፍ. 45:4, 5) [w99 1/1 ገጽ 31 አን. 2-3]
4. ዮሴፍ “ዐፅሜን ከዚህ አገር ይዛችሁ እንድትወጡ” በማለት የተናገረው ሐሳብ በእስራኤላውያን ላይ ምን በጎ ተጽዕኖ አሳድሯል? (ዘፍ. 50:25) [w07 6/1 ገጽ 28 አን. 10]
5. አስቸጋሪ የሆነ ተልእኮ ሲሰጠን ይህን ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስችለንን የመተማመን ስሜት ለማግኘት ምን ይረዳናል? (ዘፀ. 4:10, 13) [w04 3/15 ገጽ 25 አን. 4]
6. ይሖዋ ከፈርዖን ጋር በተያያዘ ያከናወናቸው ነገሮች ምን ውጤት አስገኝተዋል? እነዚህ ክንውኖች በእኛ ላይ ምን ስሜት ሊያሳድሩ ይገባል? (ዘፀ. 9:13-16) [w05 5/15 ገጽ 21 አን. 8]
7. በዘፀአት 14:30, 31 ላይ የሚገኘው ሐሳብ በዘመናችን ምን ትርጉም አለው? [w04 3/15 ገጽ 26 አን. 5]
8. ከዘፀአት 16:1-3 መመልከት እንደሚቻለው ማጉረምረም ምን አደጋዎች አሉት? [w93 3/15 ገጽ 21 አን. 1-3]
9. በዘፀአት 19:5, 6 ላይ ከተገለጸው የሕጉ ቃል ኪዳን ጋር በሚስማማ መልኩ እስራኤላውያን “የመንግሥት ካህናት [እና] የተቀደሰ ሕዝብ” ነበሩ ሊባል የሚችለው እስከ ምን ድረስ ነው? [w95 7/1 ገጽ 16 አን. 8]
10. መመኘትን በተመለከተ የተሰጠው አሥረኛው ትእዛዝ ሰዎች ከሚያወጧቸው ሕጎች የላቀ የሆነው በምን መንገድ ነው? (ዘፀ. 20:17) [w06 6/15 ገጽ 23-24 አን. 16]