ሚያዝያ 20 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ሚያዝያ 20 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 4 (8)
❑ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
❑ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፀአት 15-18
ቁ. 1፦ ዘፀአት 15:1-19
ቁ. 2፦ ከሐሰት አምልኮ መራቅ ምን ነገሮችን ይጨምራል?
ቁ. 3፦ ደግ ስለመሆን የተሰጠ ትምህርት (lr ምዕ. 15)
❑ የአገልግሎት ስብሰባ፦
መዝሙር 38 (85)
5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ መሪነት የተጻፈ መሆኑን የሚያሳዩ ማስረጃዎች። ከማመራመር መጽሐፍ ገጽ 58-63 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ።
10 ደቂቃ፦ የግንቦት 1 መጠበቂያ ግንብ እና የግንቦት ንቁ! መጽሔቶችን ለማበርከት ዝግጅት አድርጉ። በክልላችሁ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ይበልጥ የሚማርከው የትኛው ርዕስ እንደሆነና ለምን እንዲህ እንዳሉ አድማጮችን ጠይቅ። እያንዳንዱን መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ። አንደኛው ሠርቶ ማሳያ በተመላልሶ መጠየቅ ወቅት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዴት ማስጀመር እንደሚቻል የሚያሳይ ይሁን።—የነሐሴ 2007 የመንግሥት አገልግሎታችን ገጽ 6ን ተመልከት።
10 ደቂቃ፦ “ጥሩ የማንበብ ችሎታ የሌላቸውን ሰዎች አስተምሩ።” አንቀጽ 3ን ስትወያዩ አንድ አቅኚ በማስጠኛ ጽሑፉ ላይ የሚገኝን አንድ ሥዕል በጥሩ ሁኔታ ተጠቅሞ ሲያስተምር የሚያሳይ አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
መዝሙር 21 (46)