ግንቦት 25 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ግንቦት 25 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 73 (166)
❑ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bh ምዕ. 16 አን. 11-12፤ ተጨማሪ ክፍል ገጽ 222-223
❑ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘፀአት 34-37
ቁ. 1፦ ዘፀአት 37:1-24
ቁ. 2፦ መጣላት ተገቢ ነው? (lr ምዕ. 19)
ቁ. 3፦ መረን መልቀቅ ሲባል ምን ማለት ነው? መወገድ ያለበትስ ለምንድን ነው?
❑ የአገልግሎት ስብሰባ፦
መዝሙር 86 (193)
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ የሰኔ 1 መጠበቂያ ግንብ እና የሰኔ ንቁ! መጽሔቶችን ለማበርከት ዝግጅት አድርጉ። የመጽሔቶቹን ይዘት በአጭሩ ከተናገርክ በኋላ አድማጮች የትኞቹን ርዕሶች ለማስተዋወቅ እንዳሰቡ እንዲናገሩ ጋብዝ። እንዲህ ያሉበትን ምክንያት እንዲናገሩም ጠይቃቸው። ርዕሶቹን ለማስተዋወቅ ምን ጥያቄዎች ማንሳት እንዲሁም የትኞቹን ጥቅሶች ማንበብ ይቻላል? በክልላችሁ ውስጥ እያንዳንዱን መጽሔት እንዴት ማበርከት እንደሚቻል የሚያሳዩ ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ ስለ ኢየሱስ መመሥከር። በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 275 ላይ ከሚገኘው ‘ስለ ኢየሱስ መመሥከር’ ከሚለው ርዕስ ጀምሮ እስከ ገጽ 276 አንቀጽ አንድ ድረስ ባለው ክፍል ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር።
10 ደቂቃ፦ “ጽሑፎቻችንን ጥሩ አድርጋችሁ ተጠቀሙባቸው።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ ውይይት። ጉባኤው በሚያዝዘውና ተበርክቷል ተብሎ ሪፖርት በሚደረገው ጽሑፍ ቁጥር መካከል ያለውን ልዩነት ተናገር።
መዝሙር 50 (123)