የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
ከውጭ አገር የመጡም ሆኑ በአገር ውስጥ ያሉ በርካታ ቀናተኛ ወንድሞችና እህቶች በጥር ወር በጀመረው ልዩ የአገልግሎት ዘመቻ በግለት ተሳትፈዋል። በአጠቃላይ ሲታይ ከአስፋፊዎች መካከል ከ22 በመቶ በላይ የሚሆኑት በአንድ ዓይነት የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ዘርፍ ተካፍለዋል። ምሥራቹ ለብዙዎች ተሰብኳል። በርካታ አዳዲስ ክልሎች የተሸፈኑ ሲሆን ከዚህ ቀደም አስቸጋሪ እንደሆኑ ተደርገው ይታዩ በነበሩ ክልሎች ውስጥም እንኳ ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት ጀምረዋል። በዚህ የአገልግሎት ዓመት እስካሁን ድረስ 374 ሰዎች ተጠምቀዋል፤ አጠቃላይ የአስፋፊዎች ቁጥር 8,517 የደረሰ ሲሆን ይህም አዲስ ከፍተኛ ቁጥር ነው። በመሆኑም በዚህ የአገልግሎት ዓመት በአምስት ወር ውስጥ ብቻ ወደ 3 በመቶ የሚጠጋ ጭማሪ ተገኝቷል፤ ባለፈው የአገልግሎት ዓመት መጨረሻ ላይ የነበረው ጭማሪ 3.5 በመቶ ነበር። ባለፉት ወራት በተደረገው ልዩ ዘመቻም ሆነ በመታሰቢያው በዓል ሰሞን በተደረገው እንቅስቃሴ ተጨማሪ እድገት እንደምናገኝ ተስፋ እናደርጋለን።