የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
የየካቲት ወር፣ ገለልተኛ ክልሎችን ለመሸፈን ያደረግነው ልዩ ዘመቻ የተካሄደበት ሁለተኛው ወር ነው። በዚህ ወር ያገኘነው ውጤት ረጅም ከነበረው ከጥር ወር በጣም የተሻለ ነው። ከ24 በመቶ በላይ የሚሆኑ አስፋፊዎች በአንድ ዓይነት የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ተካፍለዋል! አዲሱ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር 8,537 ደርሷል። በተጨማሪም 1,223 የሚያህል አዲስ ከፍተኛ የዘወትር አቅኚዎች ቁጥር አግኝተናል። እንዲሁም አዳዲስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ለማግኘት በወር አንድ ጊዜ የምናደርገው እንቅስቃሴ ጥሩ ውጤት እያስገኘ ነው፤ በአሁኑ ጊዜ 6,558 የሚያክሉ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ እያጠኑ ሲሆን ይህ ቁጥር የዛሬ አምስት ዓመት ገደማ ተመዝግቦ ወደነበረው ከፍተኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ቁጥር ይጠጋል። ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት እንዲጀምሩ መጋበዛችሁን ቀጥሉ! በልዩ ዘመቻው የመጨረሻ ወር ያደረግነው እንቅስቃሴ እንዲሁም ሰዎች በመታሰቢያው በዓል ላይ እንዲገኙ ለመጋበዝ የተደረገው ዘመቻ የሚያስገኙትን ውጤት ለመስማት በጉጉት እንጠባበቃለን።