ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች፦ ሰኔ፦ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? ሐምሌ እና ነሐሴ፦ ብሮሹሮች፤ መስከረም፦ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
◼ በዚህ የአገልግሎት ዓመት ዓለም አቀፍ ሪፖርት ላይ በስም ወዳልተጠቀሰ አገር ወይም በቅርብ በወጣው የዓመት መጽሐፍ የመጨረሻ ገጽ ላይ አድራሻው ወዳልተጠቀሰ አገር የመሄድ እቅድ በሚኖራችሁ ጊዜ ሁሉ ልታደርጉት የሚገባችሁን ጥንቃቄ ለማወቅ ወይም አስፈላጊውን መመሪያ ለማግኘት ቅርንጫፍ ቢሯችሁን እንድታነጋግሩ እናበረታታችኋለን። በዚያ አገር በመንግሥቱ ሥራ ላይ አንዳንድ እገዳዎች ተጥለው ሊሆን ይችላል። (ማቴ. 10:16) በአንዳንድ አገሮች ከሌላ አገር የመጡ እንግዶች በዚያ ከሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች ወይም ጉባኤዎች ጋር ግንኙነት ማድረጋቸው ጥሩ ላይሆን ይችላል። ቅርንጫፍ ቢሮውን ስታማክሩ መደበኛ ባልሆነ መንገድ ስለ መመሥከር ወይም ጽሑፎችን ይዞ ስለመሄድ አንዳንድ መመሪያዎችን ልታገኙ ትችላላችሁ። የሚሰጣችሁን መመሪያ ተግባራዊ በማድረግ ትብብር ማሳየታችሁ በራሳሁም ሆነ በመንግሥቱ ሥራ ላይ አላስፈላጊ ችግር እንዳይፈጠር ያደርጋል።—1 ቆሮ. 14:33, 40