ሐምሌ 13 የሚጀምር ሳምንት
ሐምሌ 13 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 18 (42)
❑ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
❑ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘሌዋውያን 21-24
ቁ. 1፦ ዘሌዋውያን 22:17-33
ቁ. 2፦ መጥፎ ነገር የሚሠሩ ሰዎች ሊለወጡ ይችላሉ? (lr ምዕ. 25)
ቁ. 3፦ እውነተኛ ክርስቲያኖች ለድሆች እንደሚያስቡ የሚያሳዩት እንዴት ነው?
❑ የአገልግሎት ስብሰባ፦
መዝሙር 67 (156)
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ በአገልግሎታችሁ ላይ መጽሐፍ ቅዱስን ተጠቀሙ። በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 145 ላይ ተመሥርቶ ከአድማጮች ጋር በሚደረግ ውይይት የሚቀርብ። ይሖዋ የሚለው የአምላክ የግል ስም ያለበትን የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም በአገልግሎት ላይ መጠቀም ምን ጥቅም እንዳለው የሚያሳይ አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር። ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲጀምሩ ለመጋበዝ ልዩ የአገልግሎት እንቅስቃሴ በምናደርግበት ቀን ጉባኤው ምን እንዳከናወነ የሚገልጹ ተሞክሮዎች ተናገር ወይም ይህን በተመለከተ ለአስፋፊዎች ቃለ ምልልስ አድርግላቸው።
10 ደቂቃ፦ “አገልግሎታችሁን ማስፋት ትችላለችሁ?” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ።
መዝሙር 89 (201)