የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
በገለልተኛ አካባቢዎች የሚገኙ ክልሎችን ለመሸፈን በአገራችን ለሁለተኛ ጊዜ የተካሄደው ልዩ ዘመቻ በመጋቢት ወር አስደሳች በሆነ መንገድ ተጠናቅቋል። ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎች በመታሰቢያው በዓል ላይ እንዲገኙ መጋበዝ የጀመርነውም በዚሁ ወር መጨረሻ አካባቢ ነበር። በዚህ ወር 8,597 የሚያህል አዲስ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ላይ የደረስን ሲሆን በሰዓት፣ በተመላልሶ መጠየቅና በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ረገድም አዲስ ከፍተኛ ቁጥር ተመዝግቧል። ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ጋር በተያያዘ 7,077 ጥናቶች ተመርተዋል! በዚህ ወር 1,093 ረዳት አቅኚዎች ነበሩን፤ ይህም ከጠቅላላው አስፋፊዎች መካከል ወደ 30 በመቶ የሚጠጉት በአንድ ዓይነት የሙሉ ጊዜ አገልግሎት እንደተካፈሉ ያሳያል።
ለዘመቻው ድጋፍ ለመስጠት ከሰባት አገሮች 42 ወንድሞችና እህቶች መጥተዋል፤ ከአገራችን ደግሞ 500 አስፋፊዎች በዘመቻው የተካፈሉ ሲሆን በመላው አገሪቱ የሚገኙ ከ200 የሚበልጡ ገለልተኛ ክልሎች ተሸፍነዋል። ከእነዚህ ክልሎች መካከል ቢያንስ 86 የሚያህሉት ምሥራቹ ተሰብኮባቸው የማያውቁ ናቸው። በእነዚህ መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች በቅንዓት ስለተካፈላችሁ ልናመሰግናችሁ እንወዳለን። የመታሰቢያው በዓልና ከዚያ ጋር በተያያዘ የተደረጉትን እንቅስቃሴዎች ሪፖርት ለመስማት በጉጉት እንጠባበቃለን።