ነሐሴ 24 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 17 (38)
❑ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
❑ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኍልቍ 14-16
ቁ. 1፦ ዘኍልቍ 14:26-43
ቁ. 2፦ የአምላክን ሕግ መውደድ ሲባል ምን ማለት ነው? (መዝ. 119:97)
ቁ. 3፦ መጽናኛ ማግኘት የሚቻለው ከየት ነው? (lr ምዕ. 31)
❑ የአገልግሎት ስብሰባ፦
መዝሙር 98 (220)
5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች።
10 ደቂቃ፦ የመስከረም 1 መጠበቂያ ግንብ እና የመስከረም ንቁ! መጽሔቶችን ለማበርከት ዝግጅት አድርጉ። የመጽሔቶቹን ይዘት በአጭሩ ከተናገርክ በኋላ መጽሔቶቹን ለማስተዋወቅ ምን ጥያቄ ለማንሳት እንዲሁም የትኛውን ጥቅስ ለማንበብ እንዳሰቡ አድማጮችን ጠይቅ። አንድ ወይም ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
20 ደቂቃ፦ “ለወንዶች ለመመሥከር ጥረት አድርጉ።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። በአንቀጽ 9 ላይ ከተወያያችሁ በኋላ ለአንድ ሽማግሌ ቃለ ምልልስ አድርግ። በጉባኤ ውስጥ የተለያዩ የአገልግሎት መብቶች ላይ ለመድረስ እንዲጣጣር የረዳው ምንድን ነው? ምን ሥልጠና አግኝቷል? ሥልጠናውን ያገኘውስ ከማን ነው?
መዝሙር 90 (204)